– ዝዋይ ሐይቅ የዝዋይ ሀይቅ 50 ሜትር ስፋት እና ከ1 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የውሃ ክፍል ላይ አረሙ

– ቆቃ ሀይቅ ከ800 ሄክታር መሬት በላይ የውሃ ክፍል በአረሙ ተወሯል 

– የቦዬ ወንዝ  50 ሄክታር ክፍል ሸፈነ – የቦዬ ወንዝ ጉማሬ የሚገኝበት ነው 

የእምቦጭ አረም ከጣና ሀይቅ ውጭ በዝዋይ እና ቆቃ ሀይቆች እና በጅማ ከተማ የሚገኘው የቦዬ ወንዝ ላይ በአሳሳቢ ደረጃ መከሰቱ ተነገረ። ሀይቆቹ እና ወንዙ ከግብርና በተጨማሪ ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ እንደመሆናቸው የአረሙ መከሰት ስጋት ፈጥሯል።

የኦሮሚያ ክልል የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የብዝሃ ህይወት ዳይሬክተሩ አቶ ብርሀኑ ኢደቲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የቆቃ ሀይቅ ከ800 ሄክታር መሬት በላይ የውሃ ክፍል በአረሙ ተወሯል። እንዲሁም የዝዋይ ሀይቅ 50 ሜትር ስፋት እና ከ1 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የውሃ ክፍል ላይ አረሙ መከሰቱንም አስታውቀዋል።

Related stories   በምናለሽ ተራ ገበያ – ከሰኞ እስከ እሁድ

በተመሳሳይ በጅማ ከተማ የሚገኘው የቦዬ ወንዝም ለእምቦጭ አረም የተጋለጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲቱዩት አስታውቋል። አረሙ የወንዙን 50 ሄክታር ክፍል የሸፈነ መሆኑን እና ወንዙን ለመታደግ እየተሰራ መሆኑን የኢንስቲቱዩቱ የደን፣ የግጦሽ መሬት እና እፅዋት ዳይሬክተር ዶክተር ዴቢሳ ለሜሳ አስታውቀዋል።

የኦሮሚያ ክልል የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የብዝሃ ህይወት ዳይሬክተሩ አቶ ብርሀኑ ኢደቲ በበኩላቸ፥ የውሃ አካላቱን በፍጥነት እየወረረ ያለውን የእምቦጭ አረም ለመቀነስ በሰው ሀይል ለመስራት መታሰቡንም ተናግረዋል። በውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የኢኮ ሀይድሮሎጅ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ዮሀንስ ዘሪሁን፥ የእምቦጭ አረም በቆቃ እና ዝዋይ ሀይቆች ላይም መከሰቱን አረጋግጠዋል።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ስጋት ከስሩ ለመንቀል ስራዎችን መጀመሩንም አቶ ዮሃንስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል። በመፍትሄነት ከያዛቸው ሁለት መንገዶች አንዱ አረሙን ከስሩ እስከ ደለሉ መንቀል የሚያስችል መሳሪያ ከውጭ ሀገር ማስመጣት ነው።

ይህ መሳሪያ አረሙን የመንቀል፣ ለአረሙ ምቹ የሆኑ ደለሎችን የማፅዳተ እና አረሙን ወደ ተፈጥሮ ማዳበሪያነት የመለወጥ አቅም ያለው መሆኑን ነው አቶ ዮሀንስ የሚናገሩት። መሳሪያውን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት አረሙን ወደ ማዳበሪያነት ቀይሮ ለገበያ ከሚያቀርብ ኢቲሲ ከተሰኘ የሴኔጋል ኩባንያ ጋር የስምምነት ሰነድ መፈራረሙን አቶ ዮሃንስ ገልፀዋል።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

መሳሪያው ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን እስከ 2 ሚሊየን ዩሮ በላይ ወጪ እንደሚጠይቅም ተናግረዋል። መሳሪያውን በፍጥነት ወደ ሀገር በማስገባት አረሙ በሚታይባቸው ሀይቆች እና ወንዞች ላይ የማስወገድ ስራ እንደሚሰራም አቶ ዮሃንሰ ገልፀዋል።

በተጨማሪ አረሙ ወደ ውሃ እንዳይገባ የመከላከል አቅም ካላቸው ተክሎች ውስጥ ዋነኛ የሆነውን የደንገል ተክል የማልማት ስራ መስራትን በሌላ መፍትሄንት ይዟል። የዚህን ተክል የማልማት ስራዎች ለመጀመር እና በሀይቆች ዙሪያ ተክሉ እንዲተከል ለማድረግ ፕሮጀክት መቀረፁንም አቶ ዮሃንስ ተናግረዋል።

ሀይቆች ራሳቸውን ከመሰል ችግሮች የመከላከል አቅም እንዲኖራቸው ለማድረግም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ጥናቶችን ለማካሄድ ስምምነት እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በዙፋን ካሳሁን –  (ኤፍ.ቢ.ሲ) 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *