“ከአሁን በሁዋላ የምንደብቀው ነገር አይኖርም። ያለውን እውነት አንደብቅም። እውነት እውነት ነው …” ሲሉ ያልተለመደ የቁጭት ምላሽ የሰጡት የአምቦ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ኃላፊ፣ ቀይ ኮፊያ ያደረጉ፣ ከወሊሶም የመጡ እንደሆኑ በመናገር የ ” መከላከያ አባላት” ሲሉ የጠሩዋቸውን ” አናቃቸውም ። ያስፈራሉ” ነው ያሉዋቸው ። አያይዘውም ” ሌሎችም አሉበት” ሲሉም ተደምጠዋል። ሌሎች ሲሉ እነማን? ማን? ከየት የመጡ? የሚለውን ግን አላብራሩም።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

እኚሁ የኦህዴድ ሰው ስኳር በህገውጥ መንገድ እየተዘዋወረ ነው በሚል ለተቃውሞ የወጡ ላይ “ተኩሰው ገደሏቸው” ብለዋል። እሳቸው እስከሚያውቁት አስር ሲገደሉ፣ አስራ አምስት ቆስለዋል። ” ይህን ጉዳይ ክልሉ አያውቀውም” ሲሉም ድርጊቱን ነቅፈዋል። አነጋገራቸው ፍጹም የሆነ ምሬትና ቁጭት እንዳለባቸው መደበቅ በማይችሉበት ደረጃ ሲናገሩ የተሰሙት አቶ ጋዲሳ፣ ንግግራቸው ኦህዴድና ህወሃት የደረሱበትን ሁለት ጫፍ አመላካች ይመስላል።

“ይህ ለልዩ ተግባር የተዘጋጀና ማንኛውንም አካል እንዳይሰማ ተደርጎ የተሰራ ሰራዊት ሚዳቆ እንዳየ የራበው ነብር በተኮሰና በገደለ ቁጥር ይቅበጠበጣል። ጥላውን እንኳን አያምንም። እጁን ቃታ ላይ አድርጎ ሲገላመጥና በአይኑ ግንባር ሲጋረፍ፣ ሲቅበጠበጥና ሲወራጭ ለሚያየው ወገን አይመስልም…” ሲሉ ነዋሪዎች ትዝብታቸውን ይገልጻሉ።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

በአምቦ ይህ ግድያ በተፈጸመበት እለት አቶ ሃይለማርያም በማርላማ አዳራሽ ለኢህአዴግ አባለት ችግሩን ” ኪራይ ሰብሳቢዎች” የፈጠሩት ችግር እንደሆነ ሲናገሩ ነበር። የአምቦ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ኃላፊ አቶ ጋዲሳ እና ነዋሪዎችን በማናገር ቪኦኤ ይህንን ዘገባ አቅርቧል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ በዛሬውዕለት በፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ “በእጅጉ የሚረብሽ ሁከትና ግድያዎች በአምቦ ከተማ ዛሬ መከሰታቸውን በዘገባዎች ሰምተናል። በኢትዮጵያ ዜጎች በሰላምና በፍጹም ነጻነት ሐሳባቸውን እንዲገልጹ ማበረታታት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እድል እንደሚፈጥር ልናሰምርበት እንወዳለን።” ብሏል።

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *