በድጋሚ እንዲካሄድ በፍርድ ቤት የታዘዘው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ዝቅተኛ የመራጮች ቁጥር የተሳተፉበት ሲሆን ለሁለት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነ ግጭትንም አስተናግዷል። ምርጫ ያልተካሄደባቸው ቦታዎችም አሉ።[…] Continue reading

via ያልተቋጨው የኬንያ ምርጫ  BBC Amharic

የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ሃሙስ ተደረገው ምርጫ ተሳታፊዎችን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ከተመዘገቡት ኬንያውያውን መካካል ከ35 በመቶ ያነሱ በምራጮች እንደተሳተፉ አሳወቀ።

ነሐሴ ላይ በተደረገው ቀዳሚ ምርጫ የመራጮች ተሳትፎ 80 በመቶ የነበረ ሲሆን በድጋሚ በተደረገው በዚህ ምርጫ ቁጥሩ ክፉኛ አሽቆልቁሏል። የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቻቸው በምርጫው እንዳይሳተፉ ጥሪ አድርገው ነበር። በአራት አካባቢዎች በምርጫው ዕለት የተቃዋሚ ደጋፊዎች ከፖሊስ ጋር በመጋጨታቸው ምረጫው እስከ ቅዳሜ ድረስ እንዲዘገይ ተደርጓል።

የተቃዋሚው ናሳ ፓርቲ ጠንጋራ ድጋፍ በሚያገኝበት ኪሱሙ በተከሰተ ግጭት አንድ ታዳጊን ጨምሮ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። ምንም እንኳን የተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቻቸው ከምርጫ ጣቢያዎች እንዲርቁ ጥሪ ቢያድርጉም አንዳንድ ደጋፊዎቻቸው ሌሎች እንዳይመርጡ ሲከለክሉ ነበር።

የምርጫ ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት ይፋ ለማድረግ ሰባት ቀናት አሉት። ፕሬዝዳንት ኬንያታ ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ እንደተናገሩት ”በሃገራችን ከምርጫ ጋር በተያያዘ መሰላቸት ተፈጥሯል፤ አሁን ጊዜው ከዚህ የምንወጣበት ነው” ብለዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችImage copyrightAFP/GETTY IMAGES

በምርጫው ላይ የጎሳዎች ሚና?

የቢቢሲ የኬንያ ጉዳዮች ተንታኝ ዲከንስ ኦሌዌ እንዳለው ፕሬዝዳንቱ ኬንያታ የወጡበት የኪኩዩ እና ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶ የወጡበት የካሌንጂን ማኅበረሰቦች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የመራጮች ቁጥር ከፍተኛ ነበር።

በተቃራኒው ደግሞ የተቃዋሚው መሪ ኦዲንጋ የወጡበት ማህበረሰብ በሚገኝባቸው የምዕራባዊው ኬንያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ለማለት በቀረበ ሁኔታ መራጮች አልወጡም።

ጎሳን መሰረት ያደረገ ፖለቲካ በኬንያ ውስጥ ስር የሰደደ ሲሆን፤ ከአንዱ ወገን የተመረጠ ሰው ወደ ሥልጣን ከወጣ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል በሚል እሳቤ ድጋፍ ያገኛል ይላል ኦሌዌ።

ከነሐሴ ጀምሮ ምን አጋጠመ?

በመጀመሪያው የነሐሴ ምርጫ ኡሁሩ ኬንያታ አሸናፊ ናቸው ተብሎ ከታወጀ በኋላ በተቀሰቀሱ ግጭቶች 50 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል።

ራይላ ኦዲንጋ የድጋሚ ምርጫው ዘግይቶ እንዲካሄድ ፈልገው የነበረ ሲሆን፤ አቤቱታውም ከምረጫው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር።

ነገር ግን ከሰባቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች መካከል ሁለቱ ብቻ በመገኘታቸው ጉዳዩ ሳይሰማ ቀርቷል።

የአንደኛዋ ዳኛ የግል ጠባቂ ከችሎቱ ቀደም ብሎ በነበረው ዕለት ባልታወቁ ታጣቂ ተተኩሶበት ከቆሰለ በኋላ ነው ችሎት ሳይገኙ የቀሩት።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *