“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል – አቻምየለህ ታምሩ

ወደ ስልጣን ለመምጣት ሓውዜንን በቦንብ አስደብድቦ 2500 ንጹሐንን ያስጨፈጨፈው ፋሽስት ወያኔ በግፍ ስልጣኑ ላይ ለመቆየት ሲል በነቀምቴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ትግሬዎችን በመግደል [እውነት ትግሬዎች ከተገደሉ] በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ እንደሆነ ለማሳየት የተካነበትን ድራማ ለመስራት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል።

ራሱ በሚገድላቸውና በሚያስገድላቸው የትግራይ ሰዎች ነፍስ ሌሎች ንጹሐንን በዘር ማጥፋት ለመወንጀልና የአፓርታይድ አገዛዙን ቀንበር ለመጫን ይጠቀምበታል። ደርግን በዘር ማጥፋት የከሰሰው በሓውዜኑ ጭፍጨፋ ነው። የሓውዜኑን ጭፍጨፋ ግን ያቀነባበረው ራሱ ወያኔ ነበር። ባለፈው ሰሞንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ጎንደር የሚኖሩ ትግሬዎችን የማድ ቤት ብረት ድስት ሳይቀር አስጭኖ ወደ ትግራይ አጓጉዞ ነበር። ከዚያ «ትምክሕተኞች በትግሬ ላይ ባነጣጠሩ ጥቃት ተፈናቀሉ» ያላቸውን ሙሉ የቤት እቃ የሸከፉ ተዋንያንን በቴሌቭዥን መስኮት እያሳየ ድራማ ሰራ።

አደጋ ተጥሎበት የሚያመልጥ ሙሉ የቤት እቃውን ተሸክሞ አይንገዛገዝም። ቲያትረኛው ወያኔ ራሱ ያፈናቀላቸውን ትግሬዎች በትግሬነታቸው የተሰነዘረ ጥቃት ለማምለጥ እንደተፈናቀሉ አድርጎ በማቅረብ የደረሰውን ኮሜዲ «ትምክሕተኞች» ባላቸው አላክኮ ትራጄዲ አደረገው። ትግሬ በትግሬነቱ ከጎንደር ቢፈናቀል ኖሮ ከ20ሺ በላይ ጎንደር ውስጥ የሚኖር ትግሬ ሁሉ ይፈናቀል ነበር።

ትናንትና ነቀምቴ ውስጥ የሆነውም ከዚህ የተለየ አይደለም። ባገራችን ያለወያኔ ፍቃድ ሰጪነት የሚካሄድ ግድያ እስካሁን አላየንም። ትግሬዎች ተገደሉ እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል ነው።

የሆነው ሆኖ ትናንትና በነቀምቴ ከተማ በፋሽስት ወያኔ የተገደሉ ወገኖቻችን ነፍስ ይማር!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የተላላኪው ጠበቃዎች
0Shares
0