በሁከቱ ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች መኖራቸውን ማወቅ የተቻለ ቢሆንም፤ ስለ ሟቾቹ ማንነት በክልሉ የሚነገርው መረጃና ሌሎች የመረጃ ምንጮች እርስ በእርስ የሚጋጩ በመሆኑ፤ ቢቢሲ ከሶስተኛ አካል ማረጋገጥ አልቻለም። Via – BBC Amharic 

Image copyright ADDISU AREGA/FACEBOOK

ከዕሁድ ጀምሮ በኦሮምያ ክልል ነቀምት ከተማ የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ወቅት በተፈጠረ ሁከት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ከሟቾች ማንነት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨ መረጃ የተሳሰተ እንደሆነ የክልሉ መንግስት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የአከባቢው ፖሊስ ቆሞ እያየ በሚያሳይ ፎቶ ተደግፎ በነቀምት ከተማ ሦስት የትግራይ ተወላጆች በድንጋይ ተደብድበው መገደላቸው በማህበራዊ ሚድያ ሲሰራጭ የነበር ሲሆን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መረጃው ከእውነት የራቀ መሆኑ ገልፆ የማጣራት ሥራ እያከናወንኩ ነው ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሓላፊ ከአከባቢው ፖሊስ ጣብያ አጣርቼ አገኘሁት ባሉት መረጃ መሰረት፤ የሟቾችን ማንነት በተመለከት ከትናንት ጀምሮ በማህበራዊ ሚድያ ሲሰራጭ የነበረው ይሄው መረጃ የተሳሰተ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አቶ አዲሱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በዚሁ በነቀምት ከተማ የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ወቅት በተነሳ ሁከት ከሞቱት ሦስት ሰዎች በተጨማሪ በሌሎች አስር ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ አረጋግጠዋል።

የከተማዋ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ኢታና፤ ለግጭቱ መንስኤ ነው የተባለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በግለሰቦች ቤት ተከማችቶ ተገኘ የሚለው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን ለአካባቢው ሬዲዮ ተናግረዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ግጭቱን መነሻ በማድረግ የግለሰቦችን ሱቅ እና መጋዘኖች መዝረፋቸውንም ጨምረው ገልፀዋል። ይህንን ሁከት በመቀስቀስና በማነሳሰት የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን አቶ አዲሱ ጨመረው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የነቀምት ሪፈራል ሆስፒታል ሓላፊ ኣቶ አብርሃም ለቢቢሲ እንደገለፁት፤ ብድብደባውና በግጭቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ዘጠኝ ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተዋል።

አራቱ ውድያውኑ የህክምና እርዳታ አግኝተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፤ የተቀሩተ ግን አሁንም የህክምና አገልግሎት በማግኘት ላይ መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

በሁከቱ ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ ተወላጆች መኖራቸውን ማወቅ የተቻለ ቢሆንም፤ ስለ ሟቾቹ ማንነት በክልሉ የሚነገርው መረጃና ሌሎች የመረጃ ምንጮች እርስ በእርስ የሚጋጩ በመሆኑ፤ ቢቢሲ ከሶስተኛ አካል ማረጋገጥ አልቻለም።

በተያያዘ ዜና የትግራይ ክልል መንግሥት በተለይ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) በቅርቡ አንድ ግለስብ “ዶላር ይዞ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል” በሚል ብሄር ጠቅሶ ያቀረበው ዘገባ አደጋኛና በአስቸኳይ መታረም ያለበት ዘር ተኮር ዘገባ በሚል ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም ላይ ደብዳቤ ፅፏል።

ክልሉ በደብዳቤው ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ላቀረበው ቅሬታ የተጠቀሰው ተቋም አወንታዊ ምላሽ አለመስጠቱንም ይገልፃል።

“በትግራይ ህዝብና በኦሮሞ ህዝብ መካከል ልዩነት መፍጠር አይቻልም” የሚሉት አቶ ኣዲሱ ኣረጋ፤ በበኩላቸው ቀደም ሲል ኦቢኤን በጥርጣሬ የተያዙ ግሰቦችን ከትግራይ ህዝብ ጋር አገናኝቶ መዘገቡ የተሳሳተ መሆኑን አምነዋል።

የክልሉ የሚድያ ቦርድ በትናንትናው ዕለት ጉዳዩን ገምግሞ በሚድያው አዘጋገብ ላይ ከፍተኛ ስህተት መሰራቱን አመኖ ለሁለተኛ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ጥፋት እንዳይደገም ማስተካከያ እያደረጉ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ጉዳዩን በዘገበው ጋዜጠኛም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ መደረጉን አክለው ተናግረዋል። “ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ስህተት ተሰርቶ ከሆነ ገና እንገመግማለን” ሲሉ ተናግረዋል።

መቱን ጨምሮ በአንዳንድ ሥፍራዎች ብሄርን መሰረት ያደረጉ እስራትንና ማዋከብን በተመለከተ ስለሚነገረውም ክልሉ ተገቢውን ማጣራት እያደረገ መሆኑን አቶ አዲሱ ገልፀዋል።

 

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *