በየትኛውም አጋጣሚ የሚሰጡት መግለጫና አስተያየት የግላቸው ሳይሆን የወከሉት መንግሥትን አቋምን የሚያንፀባርቅ እንደሆነ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ።

Via- BBC Amharic በተለያዩ ስፍራዎች ያጋጠሙ ግጭቶችን ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ያቀረቧቸው ዘገባዎች መረጋጋት የሚያመጡ አልነበሩም፤ ስለዚህም መንግሥት አስፈላጊው ማጣራት ካደረገ በኋላ እርምጃ ይወስዳል ሲሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለንደን በሚገኘው የቢቢሲ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው በሰጡት ቃለ-ምልልስ ገልዋል።

”ስለሆነም የሕዝብም ይሁን የግል መገናኛ ብዙሃን ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ጥፋት ውስጥ ገብተው ከተገኙ መጠየቃቸው አይቀርም” ብለዋል ሚኒስትሩ።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

ከተከሰቱት ግጭቶች አንፃር የመገናኛ ብዙሃን የሃገሪቱን ሰላምና የሕዝቡን አብሮ የመኖር ልምድ የሚንድ ደርጊት ውስጥ መሳተፍ የለባቸውም ያሉት ዶ/ር ነገሪ፤ ሕዝብን የሚያጋጭ ሥራ የሚሰሩ የመንግሥትም ሆነ የግል የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሕግን እየጣሱ መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል።

ይህም የግል አስተያየታቸው እንደሆነ የተጠየቁት ዶክተር ነገሪ ”በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም ሁኔታ መንግሥትን ወክዬ ነው የምናገረው፤ የመንግሥት ሃላፊነትን ከተረከብኩ ጊዜ ጀምሮ የማንፀባርቀው የመንግሥትን አቋም ነው” ብለዋል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት ”ጋዜጠኞችን የምንጠራው የግል አስተያየታችንን ልንሰጥ አይደለም። ጉዳዩም የህዝብ ጉዳይ ነው። አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ህዝብን ከህዝብ ሊያጋጭ ሚችል ዘገባዎችን ሲያስተላልፉ ነበር። የግል አስተያየቱን ነው የሰጠው ብለው የሚያምኑ የራሳቸው ስህተት ለመሸፈን ወይም ከተጠያቂነት ለመሸሸ ያደረጉት ከሆነ ወደፊት አጣርተን የምንደርስበት ጉዳይ ነው የሚሆነው” ብለዋል።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ተደጋጋሚ ግጭቶች ቢስተዋሉም መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያወጣ የሚያስገድድ ሁኔታ እንደሌለ የተናገሩት ዶክተር ነገሪ፤ “መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሃገሪቱን የመምራት ፍላጎት የለውም። በአሁኑ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ እንዲታወጅ የሚያደርግ ችግር የለም” ብለዋል።

በሃገሪቱ እየታዩ ያሉ ግጭቶቹና አለመረጋጋቶች ከመደበኛው የፀጥታ ኃይል ቁጥጥር ውጪ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ክልሎች በራሳቸው ሊወጡት የሚችሉትና ካስፈለገም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በጋራ የሚቆጣጠሩት ጉዳይ ነው ብለዋል። ስለዚህም አሁን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈልግበት ጊዜ አይደለም ሲሉ አስረግጠዋል።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

ከተቃውሞዎችና ከግጭቶች ጀርባ ኪራይ ሰብሳቢዎችና በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ናቸው ተብለው የተጠቀሱት እነማን እንደሆኑ የተጠየቁት ዶክተር ነገሪ፤ ማንነታቸውን ለመለየትና ወደ ህግ ለማቅረብ ክልሎችና የፌደራል መንግሥቱ በጋራ እየሰሩ ነው፤ ማንነታቸውም በሂደት የሚገለፅ ይሆናል ብለዋል።

መንግሥት በውጪ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር እየተደራደረ ነው ስለሚባለው በሰጡት ምላሽ ”እየተደረገ ያለ ምንም ዓይነት ድርድር የለም” በማለት ነገር ግን የመንግሥት በር ለድርድር ዝግ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *