የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር፣ የመገናኛና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ” የፌስ ቡክም ሆነ የቲውተር አካውንት የለኝም፤ በስሜ የተከፈቱትን አይቻቸዋለሁ፤ ….. ወንጀል ነው፤ ሊዘጉ የግባል ሲሉ ተናገሩ። 

ተቀማጭነቱ አሜሪካ አትላንታ ከሆነው ጽናት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ” ይህ ካንተ አይጠበቅም” በሚል እሳቸው እንዳላደረጉት የሚረዱ ጭምር እንደሚጠይቋቸው በማስረዳት በስማቸው በተከፈተ የፌስ ቡክ አካውንት የተለያዩ አስተያየቶች መለጠፋቸውን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ለምን እስካሁን ሊያዘጉት እንዳልሞከሩ አላብራሩም።

ድርጊቱን ተመሽጎ የመታገል የወረደ አስተሳሰብ ውጤት አድርገው የገለጹት ሚኒስተሩ፣ ድርጊቱን ” የኪራይ ሰብሳቢ አስተያየት” ሲሉ ፈርጀውታ። ያልተባለ፣ የሌለ፣ ያለተነገረ ነገርን በስማቸው በማሰራጨት ስም የማቆሸሽ አላማ ያለው ዘመቻ እንደሆነም አመልክተዋል። አገሪቱ ውስጥ አሁን የተፈጠረውን ችግር ” የሌብነት” ወጤት እንደሆነ ባስረዱበትና ስለ ኤርትራ በስፋት ባብራሩበት ቃለ ምልልሳቸው ከጠያቂያቸው ከፍተኛ ምስጋና በየመካከሉ ሲቀርብላቸው ነበር። 

” ላማጋጨት፣ የሰውን፣ የፓርቲንና የመንግስትን ክብር ለምንካት፤ እንዲሁም ከዚህ ትርፍ እናገኛለን በሚል የተደረገ ” በማለት ያወገዙት ዶክተር ደብረጽዮን፣ ጉዳዩን ማጨበርበር ብለውታል። አያይዘውም አካውንቱ ሊዘጋ እንደሚገባ ተናግረዋል። እሳቸው እንዳሉት በስማቸው በማይታወቁ አካላት የተከፍተ የተባለው የፌስ ቡክ ገጽ ረጅም ጊዜ የቆየ መሆኑ፣ ካላቸው ሙያና ከሚመሩት ተቋም ልዩ የስራ ተግባር አንጻር እስካሁን ሳይዘጋ እንዲቆይ መደረጉ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ የቆየ ነው። በህወሃት ውስጥ ልዩ ተወዳጅነት ለማግኘት ሲሉ የሚተቀሙበት እንደሆነም ሲገለጽ ነበር። እሳቸው እንዳሉት ግን ድርጊቱ ስም የማጠልሸት ጉዳይ ነው።

 

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *