Image result for king haile selassie of ethiopia in norway” በግርማዊነትዎ ግብዣ ወብ ወደ ሆነችው አገርዎ በመምጣቴ ደስ ብሎኛል። እናንተም እንደኛው የጦርነትንና የመወረርን አሰቃቂነትን አውቃችሁታል። የወራሪን ጦር በመከላከል ግርማዊነትዎ ራስዎ ያደረጉትን ጀግንነትና ተጋድሎ ዓለም በሰፊው አድንቆታል። ህርማዊነትዎ ለሕዝብዎ አባትም ጭምር እንጂ ንጉስ ብቻ አይደሉም። የወራሪውን ጦር በአርበኞቻችን በኩል መከላከልን ሳናቋርጥ እንግሊዝ አገር መገናኘታችንን አስታውሳለሁ። አገሮቻችን ነጻነታቸውን ካስመለሱ በሁዋላ በተባበሩት መንግስታት ጉባዔ ዘንድ በታወቀው ጉባኤ በፍጹም መቀራረብ እየተረዳዱ ሰርተዋል።  የኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ እንዲያገኝ ግርማዊነትዎ ላደረጉት ጥረትና እርዳታ ኢትዮጵያ በተለየ ባለውለታ ናት….

በኢትዮጵያ በልዩ ልዩ የመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ፣ በዚህም ብቻ ሳይሆን በንግድ ስራ ተጠቅመው የሚሰሩ የግርማዊነትዎ ዜጎች ይገኛሉ። ካለፉት አምስት ዓመታትፕች ወዲህ በኢትዮጵያና በኖርዌይ መካከል ያለው ንግድ እያደገ መሄዱን ስንመለከት ደስ ይለናል። ይህንን የደስታ ቀን ምክንያት በማድረግ ለግርማዊ የኖርዌይ ንጉስ፣ ለልዑል አልጋወራሽና ቤተሰቦች ጤና በሁለቱ ሕዝቦቻችን ያለው ግንኙነት ወደፊት እየጠነከረ እንዲሄድ እየተመኘሁ ጽዋዬን አነሳለሁ ” ግርማዊ ሃይለስላሴ በኖርዌይ ጉብኝት ያደረጉት ንግግር ፤ቪዲዮውን እዚህ ላይ አድምጡ

የኖርዌይ ልዑል ሀከን እና ልዕልት ሜቴ ማሪት በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ። በልዑሉ ጉብኝት የኖርዌይ የቢዝነስ ልዑክም መካተቱን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የንጉሳውያኑ ቤተሰቦች ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉብኝታቸው ወቅትም በጤና፣ ትምህርት፣ በዓየር ንብረት እና በስደተኝነት ዙሪያ አገራቱ ተባብረው የሚሰሩበት ሁኔታ ይመከራል ተብሏል። በተጨማሪም በግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ተሳትፎም ዙሪያ አገራቱ ይወያያሉ።

የኢትዮ ኖርዌይ የቢዝነስ ፎረምም በዚሁ የጉብኝት ወቅት ይካሄዳል። የኖርዌይ መንግስት በያዝነው ዓመት 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የልማት ድጋፍ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ቃል ገብቷል።

አገሪቱ ባለፈው ዓመት 47 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የልማት ድጋፍን ለኢትዮጵያ ሰጥታ እንደነበረም ነው የተመለከተው። ልዑል ሀከን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት በአፍሪካ ህብረት እና በኖርዌይ መካከል ባለው ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ዙሪያ ከህብረቱ የስራ ሀላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኖርዌይ ልዑል በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ይፋዊ ጉብኝት በውጭ አገር የሚያደርጉ ሲሆን፥ የ2017 ይፋዊ ጉብኝት መዳረሻ ኢትዮጵያ ሆናለች። ሁለቱ አገራት ለ75 ዓመታት የቆየ ግንኙነት አላቸው።

ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 1947 ላይ በኦስሎ ኤምባሲዋን ስትከፍት፥ ኖርዌይ ደግሞ በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር 1992 ላይ በአዲስ አበባ ከፍታለች።

ፋና

File- mCAN694 KING OF NORWAY VISITS HAILE SELASSIE

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *