ቀድሞውንም የመሐመድ ሁሴን አላሙዲ ጉዳይ ” ሆድ ይፍጀው” የሆነባቸው በርካቶች ነበሩ። አንዳንዶች በግብር በሚያዩዋቸው ጉዳዮች ሳቢያ ሃብታቸውን ይጠራጠሩ ነበር። ሪፖርተር ” የፊትለፊቱ ሰው” ሲል ሃብታቸው የእሳቸው አለመሆኑን፣ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ፣ ዞሮ በርካታ ጉዳዮች አገር እንደሚጎዱ አትሞ ነበር። አቶ መለስን የሚያመልኩ ሁሉ ” እንዴት መለስ ዝም አለ?” እያሉ ይጠይቁም ነበር። መጠርጠር ወንጀል ባይሆንም ዛሬ ክቡር ፣ ዶክተር፣ ባለሃብት፣ ኢንዜስተር፣ የድሃ አባት፣ መመኪያችን… በሚል የሚቆለጳጰሱት አላ ሙዲ የመተሰራቸው ዜና ብቻ የሚፈጥረው መደናበር ቀላል አይሆንም።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

ይህንን ዓለምን ያናኘና የ”ምርጦቹ” እጅ ያለበትን ዘመቻ ታላላቅ የሚባሉት የዓለም ሚዲያዎች ተቀባብለውታል። ካሳዑዲ የወጣው ዜና ዓለምን ሲያነጋግር በአገራችን ግን ከማህበራዊ ገጽ ዜና አላለፈም። ጥርጣሬው ይዞት የሚመጣውን ዜና ሁሉንም ወገኖች በጉጉት ይጠብቁታል። የጀርመን ድምጽ ሮይተርስን ጠቅሶ ይህንን ዘግቧል።

መሐመድ አል-አሙዲን ጨምሮ ሳዑዲ አረቢያ 38 ሰዎችን አሰረች

ሳዑዲ አረቢያ በጸረ-ሙስና ዘመቻ 11 ልዑላን፣ አራት በሥልጣን ላይ ያሉ ምኒስትሮች እና በርካታ የቀድሞ ሹማምንትን አሰረች። ሮይተርስ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የሳዑዲ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው መሐመድ አል-አሙዲ ከታሰሩት መካከል አንዱ ናቸው። ኪንግደም ሖልዲንግ የተባለው የመዋዕለ-ንዋይ ኩባንያ ባለቤት ልዑል አልዋሊድ ቢን ታላል ከአስራ አንዱ ልዑላን መካከል ይገኙበታል። የሳዑዲ አረቢያ ብሔራዊ ዘብ አዛዥ የነበሩት ልዑል ሚተብ ቢን አብዱላሕ ታስረው ከሥልጣናቸው ሲሻሩ በልዑል ኻሊድ ቢን አያፍ ተተክተዋል። 38 ልዑላን፣ ሚኒሥትሮች እና እውቅ ባለወረቶች ትናንት ቅዳሜ የታሰሩት ንጉስ ሰልማን በልጃቸው ልዑል መሐመድ የሚመራ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ካስታወቁ በኋላ ነው። ኮሚቴው የእስር ማዘዣ የመቁረጥ፣ የተጠርጣሪዎችን ሐብት እንዳይንቀሳቀስ የማገድ እና የጉዞ ማዕቀብን የመጣል ጨምሮ በርካታ ስልጣኖች ተሰጥተውታል። የ32 አመቱ አልጋወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን አልሳዑድ ሙስናን ለመታገል ቃል ገብተው ነበር።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ጀርመን ድምጽ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *