ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በተጀመረው ፀረ ሙስና ዘመቻ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ ኢህአዴግ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር እየተደራደረ መሆኑንን ሪፖርተር ” ምንጮቼ ነገሩኝ” ሲል ጠቆመ። የሚድሮክ ኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ግራ መጋባታቸውን ከመግለጽ ውጪ የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ተጠቁሟል። የፈለገውን እንዲያደርግ ፈቃድ የተሰጠውና አዲስ የተቋቋመውን የሙስና ኮሚሽን መሪ ” ፖለቲካዊ” እንደምታ እንዳለው በተነገረለት ዘመቻ የታሳሪዎችን ንብረት እንደሚያግድ፣ ያለ አገብብ ተከማቸ የተባለውም ሃብት የሳዑዲ ህዝብ እንደሚሆን፣ ዘመቻው ማንንም እንደማይፈራና እንደማይለይ ለህዝብ ይፋ አድርጓል።

ሼህ መሐመድ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው መደናገጥ መፍጠሩን ያመለከተው ዜና ድርድሩ “ተስፋ ሰጪ” መሆኑንን ከመጠቆም ውጪ በምን መልኩና እንዴት እንደሆነ አላብራራም። ተስፋ ሰጪነቱም በምን ደረጃ ደረጃ እንደሚለካ አልተጠቆመም። ዜናው አላሙዲን ካሉበት ሆነው ከአንድ የቤተሰባቸው አባል ጋር በስልክ እንደሚገናኙ ጠቁሟል። ሪፖርተር ይህንን ቢልም ጉዳዩ የድርድር ጉዳይ እንዳልሆነ፣ የታሰሩት በሙሉ በዋስ ቢፈቱ እንኳን በቁም እስር እንደሚቆዩ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።

 

ሪፖርተር በዜናው ቀደም ሲል ባለሃብቱን አስመልክቶ ዋጋ  እስከመክፈል ያደረሰውን ዜና ለዓመታት ሲዘግብ መቆየቱን አላስታወሰም።  አግባብ እንዳልሆኑ በመጥቀስ መሟገቱን፣በዚሁም ሳቢያ የጋዜጣው ባልደርቦች ስለከፈሉት ዋጋ፣ በተለይም አቶ አማረ ላይ በግል ስለተፈጸመው ወንጀል ያለው ነገር አላመላከተም። ሪፖርተር ” ሰጋሁ” በሚል ባለሃብቱ በኢትዮጵያ ያላቸው ኢንቨስትመንት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ሊያዝ እንደሚገባው፣ በተለይም ” ጠንቀቅ እንበል” ሲል ባለሃብቱ ካላቸው ሰፊ ኢንቨስትመንት አንጻር አንድ ነገር ቢፈጠር  ወይም ቢገጥማቸው ሰራተኞች ሊበተኑ እንደሚችሉ፣ ኢኮኖሚ ሊያናጉ የሚችሉ ጉዳዮች እንደሚያጋጥሙ፣  ከፍተኛ መንገራገኝጭ እንደሚፈጠር… ወዘተ በተደጋጋሚ መዘገቡ የዛጎል ዝግጅት ክፍል ማስታወስ ይወዳል። የማይረሱና ሊካዱ የማይችሉ የመፍትሄ ሃሳቦችን ሲሰነዘር የነበረው ሪፖርተር ባለሃብቱን ” የፊለፊት ሰው the front man” መሆናቸውን በማስረጃ ሲያሳይም ነበር።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ቢዝነስ ኢንሳይደር ኖርዲክ ባቀረበው ሰፊ ዘገባ አላሙዲ በስዊዲን ያላቸውን ሰፊ ኢንቨስትመንት ከመዘርዘር ውጪ የሲውዲን መንግስት ከሳዑዲ ጋር እስሩን በተመለከተ ድርድር ስለማሰቡ ያለው ነገር የለም።

 

 

Al amudi. 2 ፎቶ – ዴይሊ ሜይል – በቁጥጥር ስር የሆኑት ” ቱጃሮች በባለ አምስቱ ኮከብ ሆቴል ፍራሽ ላይ ሆነው የሚያሳይ ፎቶ

“አነ አላሙዲ በሳዑዲ ቂሊንጦ “  ሲል የዘገባውና ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነው ጎልጉል የድረ ገጽ  “ ከሳዑዲ መንግሥት ምንጮች የተገኘ በማለት ዴይሊ ሜይል የለቀቀው ይህ ፎቶ እንደሚያሳየው አይነኬዎቹ እነ ልዑል አልዋሊድ (የእኛን ጉድ አላሙዲንን ጨምሮ) በሥሥ ፍራሽ ላይ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል መሬት ላይ ተኝተው ይታያል። ጋዜጣው ሲያላግጥም “የሳዑዲ ልዑላን ባለ አምስት ኮከብ እስርቤት ውስጥ” በማለት ለዘገባው ርዕስ ሰጥቶታል። ጋዜጣው ሁኔታውን “የሚያሳፍር” በማለት የጠቀሰው ሲሆን በትንሽ ብርድልብስ ተጠቅልለው ለዚህ ውርደት መብቃታቸው ቢፈቱ እንኳን ውርደቱን ተቀብለው ለመኖር የሚያቅታቸው እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቶበታል” ሲል ሂደቱን ያስረዳል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ዴይሊ ሜይል ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ ባይታወቅም ምርመራው እየተካሄደ ያለው በዚህ መልኩ እንደሆነ፣ምርመራው ለሳምንታት ሊቆይ እንደሚችል ያሰባሰበውን መረጃ በመንተራስ ግምት ይሰጣል። (የጋዜጣው ሙሉ መረጃ እዚህ ላይ ይገኛል)

በሌላ በኩል ግን ሰኞ ዕለት የሳዑዲ መንግሥት እንዳስታወቀው የግለሰቦቹ የባንክ ሒሳብ እንዳይንቀሳቀስ ይደረጋል፤ ሃብታቸውም የሳዑዲ መንግሥት ንብረት ይሆናል ብሏል።

ማንኛውንም የማሰር፣ የመያዝ፣ ወዘተ ሥልጣን የተሰጠውን አዲሱን የጸረ ሙስና ኮሚቴ አስመልክተው ንጉሥ ሳልማን በሳዑዲ ቲቪ ላይ እንደተናገሩት፤ ማንንም አንምርም፣ ማንንም አንፈራም ሲሉ ነበር ያስጠነቀቁት።  “የሕዝብን ገንዘብ በነካ፣ በመዘበረ፣ ወይም እንዳይሰረቅ ባልተከላከለ ወይም ሥልጣኑን ተጠቅሞ (ይህንን ዓይነት ተግባር በፈጸመ) በማንኛውም ግለሰብ ላይ ሕጉ በጽናት ተግባራዊ ይደረጋል። ይህ የሚፈጸመው በትልልቆቹም ሆነ በትንንሾቹም ላይ ይሆናል” ሲሉ ነው የተደመጡት።

ዜናውን ከተለያዩ ጉዳዮችና ከዲፕሎማት ምንጮች ካገኘው መረጃ ጋር በማያያዝ ጎልጉል ”

ይህ “ኃያላንን” በቁጥጥር ሥር የማዋል ዘመቻ በተወሰነ መልኩ ከአሜሪካ የውስጥ ፖለቲካ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ጎልጉል ያገኘው መረጃ ያስረዳል። ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሆኖ የተዘገበው መረጃ እንደሚያመለክተው በቅርቡ የዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ ባለቤት ያሬድ ኩሽነር ከዕድሜ አቻው አልጋወራሽ ልዑል ሳልማን ጋር በሳዑዲ ያካሄደው ውይይት እንደ አስረጅነት ይጠቀሳል። ኩሽነር የፕሬዚዳንቱ አማካሪ እንደመሆኑ ጉብኝቱ በምሥጢር መያዙና ከስድስት ቀናት በፊት ይፋ መሆኑ በርካታ መላምት እንዲሰጥበት አድርጓል። ከዚህ ሌላ ዶናልድ ትራምፕ ለምርጫ በሚወዳደሩበት ወቅት ከይነኬው ባለሃብት ልዑል አልዋሊድ ቢን ጣላል (በሲቲግሩፕ፣ ኧፕል፣ ትዊተር፣ ሊፍት ወዘተ ውስጥ ከፍተኛ የባለቤትነት ድርሻ አላቸው) ጋር የነበራቸውን ቁርሾ የሚያነሱ አሉ። በምርጫው ውድድር ወቅት ልዑሉ ዶናልድ ትራምፕን “ለሪፓብሊካን ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ለመላው አሜሪካ ኃፍረት (ውርደት) ነህና በጭራሽ ስለማታሸንፍ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ራስህን አግልል” በማለት የትዊተር መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

ጣላል በአባቱ ገንዘብ የአሜሪካንን ፖለቲከኞች ለመቆጣጠር ይፈልጋል። እኔ ስመረጥ ይህንን ማድረግ አይችልም” ብለው ነበር። በበቀለኝነታቸውና ጠላቶቻቸውን ጊዜ ጠብቀው በማዋረድ፣ ድባቅ በመምታት የሚታወቁት ትራምፕ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ያለፈውን ቁርሾ አሁን በተግባር ፈጽመውታል የሚሉ አሉ። ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን አስቀድመው የተመለከቱት ልዑል አልዋሊድ የትራምፕ መመረጥ ይፋ እንደሆነ ወዲያውኑ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት እንዲህ የሚል የአጸፋ ምላሽ ሰጥተው ነበር፤ “ያለፈው ልዩነታችን ምንም ይሁን የአሜሪካ ሕዝብ ተናግሯል፤ እንኳን ደስ አለዎት፤ በፕሬዚዳንታዊ ዘመንዎ መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ።”

ዜናው እንዲህ ባሉ ጉዳዮች የተተበተበና የፖለቲካም ጉዳይ ያለበት በመሆኑ በድርድርም ሆነ በምልጃ የሚሆን ነገር እንደማይኖር ለመገምት ቀላል ይሆናል። በዚህ መነሻ ኢህአዴግ ምን ብሎ ሊደራደር እንድሚችል መላምት እንኳን መስጠት እንደማይቻል ብዙዎች ይስማማሉ።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *