በሳዑዲ የተከፈተውን የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ በቁጥትር ስር ከዋሉት የሉዑላዊያን ቤተሰቦችና ሃብታም ነጋዴዎች ጋር አብረው የታሰሩት ዶክተር ሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲንን ጨምሮ የባንክ ሂሳባቸው ታገደ። እግዱ ግን በውጪ ያላቸውን ንብረት ያካት አያካት በግልጽ አልተነገረም።
ሪዝ ካርተን ሆቴል በእስር ላይ የሚገኙት ሼክ መሀመድ ያሉበትን ሁኔታ አስመልክቶ ከሚድሮክ ኢትዮጵያም ሆነ ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው በገሃድ የተሰጠ መግለጫ ወይም መልዕክት የለም። ከቅርብ ሰዎቻቸው ተገኘ በሚል የሚሰራጩ ዜናዎች እንደሚያስረዱት ከቤተሰቦቻቸው አንዱን በስልክ ያገኛሉ።
ዋዜማ ምንጮች እንደነገሩት ጠቅሶ እንዳለው ከአዲስ አበባ ሚድሮክ ግሩፕ አካባቢ ሊጠይቋቸው የሄዱ አካላት አሉ። የገዢው ፓርቲ ሚዲያዎች ጉዳዩን አስመልከተው እስካሁን ያሉት ነገር የለም። 
Related stories   የህወሃት የመሪነት ሚና በኦህዴድ ሊነጠቅ ይችላል ተባለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *