የባለፈው የሶማሊላንድ ምርጫImage copyrightALI MUSA

Via BBC  የዓይን ብሌንን በመጠቀም ማጭበርበርን መቆጣጠር ይቻል ይሆን?

አጠቃላይ ስለ ምርጫው ማወቅ ያለባችሁ አምስት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።

1.የዓይን ብሌንን በመጠቀም ማጭበርበርን መቆጣጠ

ሶማሊላንድ የዓይን ብሌን ልኬት (ባዮሜትሪክን) በመጠቀም የምርጫ ስርዓት በመዘርጋት በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር እንደሆነች የምርጫው ቃል አቀባይ ሰይድ አሊ ሙሴ ተናግረዋል።

ማጭበርበርን ከመከላከል በተጨማሪ ሶማሊላንድ በአፍሪካ የመጀመሪያ ግልፅ የሆነ ምርጫ ታደርጋለች ብለዋል።

3.5 ሚሊዮን ከሚገመተው ህዝቧ ውስጥ 704 ሺ መራጮች ተመዝግበዋል።

ሶማሊላንድ የዓይን ብሌንን በመጠቀም የምርጫ ማጭበርበርን መቆጣጠር
Image copyrightDR MICHAEL WALLS

2.ከፊንላንድ ጋር ያለ ግንኙነት

ከሶስቱ ተመራጮች ሁለቱ አብዱራህማን መሀመድ ኢሮና ፋይሳል አሊ ዋራቢ የፊንላንድ ዜግነት አላቸው።

ሶስተኛው ተወዳዳሪ ሙሴ ቢሂ አብዲ የቀድሞ ወታደር የነበሩ ሲሆን ሩሲያ ሄደውም በአውሮፓውያኖቹ 1970ዎቹም ስልጠና ወስደዋል።

ሶስቱም ምርጫው ተራዝሞላቸው በፕሬዚዳንትነት በስልጣን ላይ ያሉትን አህመድ ሲልያኖን ለመተካት እየተወዳደሩ ነው። አህመድ ሲልያኖ ከሁለት አመታት በፊት ከአምስት አመት የስልጣን ጊዜያቸው በኋላ ስልጣን ይለቃሉ ተብለው ቢጠበቁም የሶማሊላንድ ፓርላማ ሀገሪቷን ከድርቅ እንዲታደጉዋት በሚል ለሁለት ዓመታት አስረዝመውታል።

3.የዳላይ ላማ ምልክቶች

ሶማሊላንድ ወደ 100% የሚጠጋው ህዝቧ ሙስሊም ቢሆንም በምርጫው ዘመቻ ላይ የዳላይ ላማና ቡድሂዝም ስም ተጠቅሷል። ፋይሳል አሊ ዋራቤ ” የዋዳኒ ፓርቲ ደጋፊዎች ብርቱካናማ ቀለማቸው የቡድሀ ተከታይ መነኩሴዎች የሚያስመስላቸው ሲሆን መሪያቸው ደግሞ ዳላይ ላማን ይመስላሉ ብለዋል። ይህ አስተያየታቸው በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ ከፍተኛ ትችት እያሰነዘረባቸው ሲሆን አንዳንዶችም በዕምነት ላይ ያነጣጠረ ስድብ ነው ብለውታል።

የዋዳኒ ፓርቲ ደጋፊዎች በከተማው ብርቱካናማ ቀለም ያለው ልብስና ሰውነታቸውንም በብርቱካናማ ቀለም በመቀባት ታይተዋል።

ብርቱካናማ ቀለም ለባሾቹ የዋዳኒ ፓርቲ ደጋፊዎችአጭር የምስል መግለጫብርቱካናማ ቀለም ለባሾቹ የዋዳኒ ፓርቲ ደጋፊዎች

4.በቀጥታ በቴሌቪዥን በሚተላለፉ ክርክሮች

ተወዳዳሪዎች በቀጥታ በሚተላለፍ የቴሌቪዥን ክርክር ሲቀርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የመጀመሪያው የተዘጋጀው ክርክር ‘ኢንስፓየር’ በሚባል የወጣቶች ቡድን ሲሆን በትዊተር ድረ-ገፅ ብቻ ከሁለት ሚሊዮኖች በላይ የተሳተፉበት ነው።

አንደኛው አነጋጋሪ ጉዳይም ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ጋር በበርበራ ወደብ የወታደር ማዕከል ለመገንባት የተደረጉ ስምምነቶች ናችው።

ፋይሳል አሊ ዋራቤና ሙሴ ቢሂ አብዲ ይህንን ስምምነት ዕውቅና የሌላት ሶማሊላንድ አለም አቀፍ እውቅና እንድታገኝ ይረዳታል በሚል ስምምነቱን ደግፈውታል።

ነገር ግን አብድራህማን መሀመድ ኢሮ ትክክለኛ ስምምነት አይደለም በሚል ተቃውመውታል። ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ ተቀናቃኝ ተወዳዳሪዎቹን ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ ገንዘብ ወስደዋል በሚል የሚተቹ ሲሆን አነሱ ግን ሙሉ በሙሉ ክደውታል።

በቴሌቪዥን በቀጥታ የሚደረጉ ክርክሮች

5.ዕውቅና የማይገኝ ካልሆነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ እርዳታ

ምንም እንኳን ሶማሊላንድ ዓለም አቀፍ እውቅና ባይኖራትም ከ24 ሀገራት ምርጫውን ለመቆጣጠር ይመጣሉ።

የተቆጣጣሪዎቹ መልዕክተኛ ዳይሬክተሩ ከለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የመጡት ሚካኤል ዋልስ ሲሆኑ የገንዘብ ድጋፍም የሚያገኙትም ከእንግሊዝ መንግስት ነው።

ለምርጫው የሚሆነወን 20 ሚሊዮን ዶላር አስተዋፅኦ ካደረጉት መካካል አሜሪካ፣ኖርዌይ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ሲሆኑ አንድም አፍሪካዊ ሀገር አስተዋፅኦ አላደረገም

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *