ህወሀት ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ሲደቁሳት የቆየውና አሁንም እየደቆሳት ያለው ብአዴን በተባለ ወኪሉ ደንደስ ነው፡፡ ብአዴን (በፊት ኢህዴን) የተቀረውን ኢትዮጵያ በአማርኛ እያግባባ ከትግሬ ካድሬዎች ጋር አገናኝቶ በህወሀት አገዛዝ ስር ያስገባ ድርጅት ነው፡፡

ለብአዴንነት የሚመለመሉ ሰዎች በባህርያቸው ተልመጥማጭ፣ ከግላዊ ፍላጎታቸው ውጭ ለህዝብ ደንታቢስ እና ለእውነት ለመቆም እንዳይችሉ እውነትን ራሱን ማወቅ የማይችሉ ናቸው፡፡ ህወሀት አንድ ነገሩ ሊደነቅ ካስፈለገ የብአዴን አባላትን ሲመለምል ለህዝብ ስሜት አልባ መሆናቸውን የሚያጠናበት መንገድ ነው፡፡ ከዛ ውጭ በኑሮ ግዴታ የሚገቡት ይሄንን የደንታ ቢስነት መስፈርት ስለማያሟሉ ጠቃሚ የሆነ ስፍራ አያገኙም፡፡ ስለሆነም በብአዴን ውስጥ የህዝብ ልጅ ጠቃሚ ስፍራ የለውም፡፡

ብአዴን ከሩቅ ሲያዩት አማሮች ያሉበት ቢመስልም እያንዳንዱ ጠቃሚ ስፍራ የያዘ ቀረብ ተብሎ ሲጠና ከተለያዩ ዘውጎች የሚወለድ ነው፡፡ በዛም ምክንያት ለአማራ ህዝብ ወይ ክዳት ወይ ግማሽ ፍቅር ብቻ ነው የሚኖረው፡፡

ብአዴን አማራን እየረገመ፣ እየሰደበ፣ እያሰረ፣ እያደኸየ፣ እየገደለ፣ እያሸማቀቀ ለትግራይ ቅኝ ግዛት ያመቻቸ የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላት ድርጅት ነው፡፡

አብዛኛው የብአዴን አባላት ለግል ፍላጎታቸው ወይም ለኑሮ ሁኔታ ተገደው የገቡ እንጅ አላማ ኑሯቸው ለትግል የገቡ አይደሉም፡፡ ስለሆነም ከጅምሩም የማያምኑበትን የትግል ጥሪ ልናደርግላቸው አንችልም፡፡

የአማራ ህዝብ ነጻ የሚወጣው በብአዴን መስመር ሳይሆን በትክክለኛ የአማራነት መስመር ነው፡፡ ትክክለኛ የአማራነት መስመር ደግሞ ከብአዴን መስመር ጋር ቀጥተኛ ተቃራኒ ነው፡፡ ስለሆነም የብአዴን መስመር እና የትክክለኛው የአማራ መስመር እርስ በእርሳቸው የሚጠፋፉ እንጅ የሚስማሙ አይደሉም፡፡

የብአዴን አባላት የብአዴንን ዴሞክራሲያዊ ብሄረተኝነት የሚል መስመር ትተው ሀቀኛውን የአማራነት መስመር መቀላቀል ይችላሉ፡፡ ይሄንን ግን በየራሳቸው የግል ውሳኔ የሚያደርጉት ነው፡፡ እንጅ ብአዴን እንደ ድርጅት ወደትክክለኛው የአማራነት መስመር ሊገባ ተፈጥሮው አይፈቅድለትም፡፡ ብአዴን ወደሀቀኛው የአማራነት መስመር የሚገባ ከሆነ በቀጥታ ከህወሀት ጋር ጦርነት ውስጥ ነው የሚገባው፡፡ ብአዴን ደግሞ እንደ ድርጅት ይሄንን ሊያደርግ አይችልም፡፡

ብአዴን ውስጥ ያለው አብዛኛው ስብስብ በህወሀት ኢንዶክትሬኔሽን የታወረ እና በራሱ ህዝብ ላይ በጠላትነት የተሰለፈ ሀይል ነው፡፡ ይሄንን በህወሀት ስብከት የተሞላ አእምሮውን አጥቦ ወደሀቀኛው የአማራነት መስመር ለማሰለፍ በርካታ አመታት ይወስዳል፡፡ አመታቱም ብቻቸውን አይቀይሩትም፡፡ ነገር ግን የብአዴን ተቃራኒ የሆነ ጠንካራ የአማራነት መስመር ያስፈልጋል፡፡

የብአዴን አብዛኛው አባላት ለሀቀኛው የህዝብ ጥያቄ ጆሮ ሊሰጡ ካስፈለገ በተከታታይ ጥፋታቸውና ክህደታቸው መነገር፤ ከህዝባቸው በጠላትነት እንደቆሙ እንዲያውቁ መደረግ አለበት፡፡ ከዛ ውጭ ብአዴንን አትንኩብን ማለት ሀቀኛውን የአማራ መስመር ለድንዝዙ ብአዴን አስረክቦ የአማራን ትግል እንደመቀልበስ ይቆጠራል፡፡ በትክክልም መቀልበስ ነው፡፡ ብአዴንን አትንኩብን የሚለው አባባልም ብአዴንን የመሰለ ተላላኪ ድርጅት ሲሰደብ ይከፋዋል ብሎ የሚያምን እና ለማሳመን የሚሞክር አሳፋሪ አካሄድ ነው፡፡

እንደተጠቀሰው ብአዴንና ሀቀኛው መስመር ተደጋጋፊ ሳይሆኑ ተጠፋፊ ናቸው፡፡ መጠፋፋታቸው እንዲቆም ካስፈለግ የብአዴን አብዛኛው አባላት ወደሀቀኛው መስመር በውድም በግድም እንዲመጡ መደረግ አለበት፡፡ የአማራ ትግል ብአዴንን የሀቀኛው የህዝብ ጥያቄ ምርኮ ማድረግ እንጅ ሀቀኛውን መስመር ብአዴን ማድረግ አይደለም፡፡ እንደዛ ከተደረገ ራስን እንደማጥፋት ይቆጠራል፡፡

ብአዴንን ማቆላመጥ ተጨማሪ ህዝብ እንዲገድል፣ ለህወሀት ሎልነቱ እንዲበረታ እና አማራን ማለቂያ ለሌለው መከራ መዳረግ ማለት ነው፡፡ ይልቅ ብአዴንን ማዋከብ፣ ማጋለጥ፣ ማጨናነቅ፣ እና ጥፋቱን እንዲያምን እና አሰላለፉን እንዲያስተካክል ማድረግ አለብን፡፡ ተመስግኖ ይቅርና እየተዘለፈ እንኳ ጆሮ ሊገዛ ያልቻለ ድንዝዝ ስብስብ ነው፡፡ ድንዝዝን እንዲነቃ ደግሞ ጋቢ መደረብ ሳይሆን መቀቀል ነው ሚሻለው፡፡

ስለሆነም ብአዴንን ለመማረክ እንጅ በብአዴን ለመማረክ አደባባይ ወጥተን ከሆነ ከባድ ስህተት ነው፡፡

Mesganaw Andualem

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *