ዛጎል ዜና – ከመቀሌ አዲስ ዜና እየተሰማ ነው። ቀድሞውንም በውስጥ ለውስጥና በተባራሪ እንዲሁም ” ውስጥ አዋቂ ነን ” የሚሉ ሲሉት እንደከረሙት እየሆነ ነው። የሆነው ደግሞ አቶ መለስ እንዳደረጉት ዓይነት ነው። ” ከእንጥላችን በስብሰናል፣ ገምተናል” በማለት ነበር አቶ መለስ ዙሪያቸውን አጽድተው ” አምልኮ” የፈጠሩት።

በወራት እድሜ ውስጥ በተለየ መልኩ ራስን የማስተዋወቅ ወይም የለውጥ ናፋቂ ስሜትን ያዘሉ ቃለ ምልልሶች ሲካሄዱ ነበር። በተመሳሳይ ይህንኑ ሚዲያ ውስጥ የመሸሸግ ጉዳይ በተቋም ደረጃ የመሞሽለቅ ስራም በባለስልጣናት ተሰርቷል። የብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ በተለይ የራሱን ሚዲያ /ENN /ጠቅሶ እርምጃ እንደሚወስድ ሲያስጠነቅቅ ጉድዩ የኦሮሚያና የሶማሊ ክልል እንደሆነ ተደርጎ ቢታይም ምላሽ እስከ መስጠትና አካሄዱ ” ዴሞክራሲያዊ አይደለም” በሚል ፈቃድ የሰጣቸውን አካል የተገዳደሩም አልጠፉም።

ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ከሚዲያዎች ሁሉ በስተጀርባ ሰዎችና ልዩ ሃሳቦች ስለመኖራቸው በስፋት ሲተቹ ነበር። ትችቱ እንዳለ ሆኖ ግን ከሁሉም ወገን እንቶ ፈንቶ ይልቅ አቶ ስብሃት ነጋና ወ/ሮ አዜብ መስፍን የተናገሯቸው ዛሬ ቀን ቆጥረው ገሃድ ሆነዋል። ስብሃት ” ሕዝባዊነት ሞቷል፣ ድርጅታችን ከሕዝብ ተለይቷል፣ አሁን ያለው ሁኔታ አደገኛ ነው” በማለት ደጋግመው ሲናገሩ ” ሙስናና ኪራይ ስብሳቢነት የቃለምልልሳቸው ማሟሻ ነበር።

Related stories   ትህነግ ከትግራይ አስተዳደር ጋር መሳሪያ አስረክቦና ጦሩን በትኖ እንዲደራደር ታስቧል፤ መንግስ የተረፈውን ሃይል ሊያጸዳ ነው

አቶ ስብሃት ስርዓቱ አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በተለያዩ መልኩ ሲያስረዱ ቆይተው ሲያጠቃልሉ  ” እርግጠኛ ነኝ ኢህአዴግ ይህንን ፈተና ያልፈዋል” በማለት ነበር። ኢህአዴግ ፈርሶ ልማታዊ ባለሃብቶችን ያካተተ የሰራተኛው ፓርቲ ሊገባው በተገባ እንደነበር በማውሳት ትልቅ ፖለቲካዊ ትርጉም ያለው ጉዳይ ፈንጥቀው ነበር በሚል ጉዳዩን ያጦዙ ክፍሎች ነበሩ። አቶ ስብሃት ይህንን ሲሉ እጃቸው የት ድረስ ቢዘረጋ ነው? የሚል ጥያቄ የሰነዘሩም አልታጡም። አቶ በረከትም ” በቃኝ” ከማለታቸው በፊት ፋና ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ” የኢህአዴግ ትልቁ ድል መክሰም ነው” ማለታቸውን በማስታወስ ጉዳዩ አዲስ እንዳልሆነ በጠቆም  ” የመዘላበድ” ያህል አድርገው ያዩትም ነበሩ።

የስብሃት ነጋን ንግግር ወይዘሮ አዜብ መስፍን በዛሚ ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ ምልልስ ጋር እያዋሃዱ ላጣጣሙት ግን ጉዳዩ ተራ ” መዘላበድ” ሳይሆን ኢላማ የነብረው እንደሆነ፣ አቶ ስብሃት አሁን ካለው ባለጡንቻ ቡድን ጋር የተቆራኙ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ የሚሰጥ እንደሆነ በልበ ሙሉነት የሚያምኑ ክፍሎች፣ አሁን አገሪቱ የገባችበትን የፖለቲካ ግለት ለማስተንፈስ በሚድረገው ደፋ ቀና ውስጥ ስብሃት ሚናቸው የጎላ መሆኑንን ይናገራሉ።

Related stories   የባይደን አስተዳደር ፖሊሲ አምስተኛው ምሰሶ የኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉን ቡድን መወሰንና የ 2021 ምርጫን ማዋደቅ (1ኛ ክፍል 2)

ወ/ሮ አዜብ የተለዩዋቸውን ባለቤታቸውን እያጣቀሱ ሙስናን ሲረግሙና ሲቀብሩ ውለው ” ሃብት ካለኝ ለድሆች ይሰጥ” በሚል በደመደሙት ቃለ ምልልስ ሕዝባዊነት መሞቱን አስረግጠው ሲናገሩና ስር ነቀል ለውጥ እንደሚያሻ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። የዩቲዩብና የፌስ ቡክ አይርን ያጥለቀለቁት ወ/ሮ አዜብ ጀርባቸው የጸዳ መሆኑንን በልበ ሙሉነት ሲያስረዱ እሳቸው የሚመሩት ኤፈርትን በመጠቆም ይህ ነው የሚባል ስራ መራታቸውን ሲያጎሉ ተስተውለዋል።

በዚህ የተገመደና የተጋመደ የኤፈርት ጉዳይ ማንን ራሳቸውን ያሳዩት ወ/ሮ አዜብ፣ አካባቢያቸው እንደ ድሮው የሞቃቸው እንዳልሆነ ከመልዕክታቸው ለመረዳት ቀላል ነበር። ” ተኳሽ፣ ትንታግ ” እየተባሉ ሲሞካሹ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ በምልልሳቸው ውስጥ ደጋገመው ያነሱት ጉዳይ ቢኖር ከላይ እንደተገለጸው በግልጽ መገማገምን ነበር። ለምን ቢባል ሕዝባዊት ተሸርሽሮ ስላለቀ!!

Related stories   ጄኔራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል – በትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪ ሆነው ተሾሙ

ከዚህ በሁዋላ አንዴ ትግራይ ሌላ ጊዜ አራት ኪሎ የተካሄደውና ያልተቋጨው የህወሃት መሪዎች ስብሰባ ዛሬ ” እርስ በርስ ተሞሻለቁ” በሚል መሪ ዜና ይፋ ሆኗል። ቪኦኤ ” ሰበር” ሲል ያቀረበው ይህ ከፍተኛ አመአሮቹ የተሞሻለቁበትን ስብሰባ ረግጠው የወጡም አሉ። ዜናው ስብሰባውን ረግጠው የወጡትን በስም ባይጠቅስም የስብሰባውን አጀንዳዎች አመላክቷል።

መበስበስና የድርጅቱ የዲሞክራሲ ትግል ጉድለት የአሰራረ ግልጽነት መጥፋት፣ በሚል እየተካሄደ ያለው ስብሰባ የአመራሩ አፈጻጸም ብቃት ማነስ እንዲሁም የትራንስፎርሜሽ እቅድ አፈጻጸም አጥጋቢ አለመሆኑ በዘገባው ተጠቁሟል። ስብሰባው የቃላት መሞሻለቅ የታየበትና ሃሳቡ በአብላጫ ድምጽ ሲጸድቅ ባለመቀበል አንዳንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸው ተመልክቷል።

ጉዳዩ ከዚያም በላይ እንደሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች ስብሰባውን ረግጠው ከውጡት መካከል የክልሉ ፕሬዚዳንትና ወ/ሮ አዜብን በግንባር ቀደምትነት ያነሳሉ። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት የክልሉ መሪና ወ/ሮ አዜብ ካላቸው ሃላፊነት ከሚነሱት መካከል እንደሆኑ ጠቁመዋል። ዜናውን አስመልክቶ በድርጅቱ ድርገጽም ሆነ ኢህአዴግ በሚያስተዳድራቸው ሚዲያዎች ይህ እስከታተመ ድረስ የተባለ ነገር የለም።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *