ያሳሰራቸው ከጀርባቸው እየተውጠነጠነ የነበረ ፖለቲካዊ ሴራ (Political Framing) ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ይቻላል፡፡ ፖለቲካዊ ሴራ (Political Framing) ማለት “አንድን ንፁህ ግለሰብ፣ ድርጅት ወይም ማህበረሰብ… ባልዋለበትና ባልሰራው ኃጢያት አቅዶና ሆን ብሎ፣ ሴራ በመጎንጎንና ሰነዶችን በማቀነባበር በህዝብና በፍትህ አካላት ተጠያቂ ለማድረግ የሚሸረብ ፖለቲካዊ ሴራ” ማለት ነው ይላሉ በመስኩ ጥናት ያደረጉ ተንታኞች፡፡ እንዲህ ያለው የሴራ ፖለቲካ አሜሪካንን ጨምሮ በአውሮፓና በሌሎችም በርካታ ሀገሮች ይፈጸማል፡፡

በእኛም በገር (የሩቁን ዘመን ትተን) ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የስልጣን ተቀናቃኝን፣ አልታዘዝም ባይን፣ አፈንጋጭን፣… ለማንበርከክ መንግስታት የሚጠቀሙበት የሸርና የተንኮል መንገድ ነው፡፡ (ወንድማችንን ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲንን ከእንዲህ ያለው ሸፍጥ አላህ ይጠብቃቸው!!!)
ሳር ቤት አካባቢ ወደሚገኘው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ (መቻሬ ሜዳ) በሄድኩ ቁጥር ከሼህ ሙሐመድ ትልቅ ፎቶግራፍ ስር የተጻፈ ሁሌም ቀልቤን የሚስብ አንድ ጥቅስ አለ፡፡ እንዲህ ይላል፤ “ፈረሱም ሜዳውም እነሆ፡፡ አንድና አንድን በማቀናጀት አስር ለማድረግ በርትታችሁ ስሩ” ይላል፡፡ ይህ ጥቅስ ከሼህ ሙሐመድ ንግግር ላይ የተወሰደ ነው፡፡ መቼና የት እንደተናገሩት ባላውቅም ሼህ ሙሐመድ ይህንን “ሚሽን” (ተልእኮ) የሰጡት በኩባንያዎቻቸው ለሚሰሩ ሰራተኞቻቸው መሆኑ ነው፡፡ መጀመሪያ ላይ አንድ እና አንድ ተቀናጅቶ እንዴት አስር ሊሆን እንደሚችል አልገባኝም ነበር፡፡ በኩባንያዎቹ ያለውን ስራና የአሰራር ስርዓት እንዲሁም በየዓመቱ የሚመዘገበውን ውጤት ሳይ ይህ ሼህ ሙሐመድ ለሰራተኞቻቸው የሰጡት ሚሽን ግልጽ ሆኖልኛል፡፡
“ድንጋይና ቅዝምዝም የሚወረወረው ጣፋጭ ፍሬ ያፈራ ዛፍ ላይ ነው” እንዲሉ ሼህ ሙሐመድ የታሰሩት ታላቅ የስራ ሰው በመሆናቸው ነው እንጂ በነውረኛ ነገር ውስጥ ተገኝተው እንዳልሆነ በኢትዮጵያ ውስጥያለው ስራቸው ህያው ምስክር ነው፡፡ እንዲህ ያለው ውንጀላም ሆነ የሊቀ መንበራችን መታሰርና መንገላታት አያስበረግገንም! እርሳቸው ታሰሩም ተፈቱ፣ በሀገር ውስጥ ኖሩም አልኖሩ… እርሳቸው የሰጡንን አንድ እና አንድን በማቀናጀት አስር የማድረግ ተልእኮ ለማሳካት መላው ሰራተኛ በበለጠ ትጋትና ጥንካሬ የምንሰራ መሆኑን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል፡፡
በመጨረሻም፤ የሳዑዲ ዓረቢያን የሙስና ዘመቻ በተመለከተ አንዲት ነገር ለማንሳት ወደድሁ፡፡ በቅርቡ የሳዑዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ወደ ፈረንሣይ ፓሪስ ለመዝናናት ሄደው ነበር፡፡ መሄዳቸው የሚገርም ነገር አይደለም፡፡ የሚገርመው ነገር ከንጉሳዊ ቤተሰቡ ጋር ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ፈረንሳይ ተጭኖ የሄደው “ጓዝ” ብዛት ነው፡፡ ክብደቱ 25 ቶን (2,500 ኩንታል) ነበር፡፡ ይህንን “ጓዝ” ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ አረፉበት ሆቴል ለማጓጓዝ፣ ለመጫንና ለማውረድ የነበረውን ውጣ ውረድ አስቡት፡፡ ሆቴሉ ውስጥ ወደ ፎቅ ለማውጣት የሆቴሉ አሳንሳር አልችል ብሎ እንደነበርም ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡
ለመሆኑ ይህ ሁሉ “ጓዝ” ምንድነው? ልብስ ከሆነ አንድ ሁለት ሻንጣ ይበቃል፡፡ ቤትና አገር የለቀቁ ይመስል ዐረቢ መጅሊስ፣ መኪናና ምግብ ጭምር ጭኖ ሽርሽር ከመሄድ በላይ ብክነትና ሙስና አለ? የሳዑዲ መንግስት ሙስናን እዋጋለሁ ማለቱ ከልቡ ከሆነ መጀመሪያ በንጉሳዊ ቤተሰብ የሚፈጸመውን ልቅ ኑሮና መረን የለሽ ብክነት እንዲቀር ማድረግ ቢጀምር መልካም ነው፡፡ በርግጥ ሙስናን ከልብ እንዋጋ ካሉና ዘመቻውንም ከቤት ከጀመሩ የንጉሳዊ ቤተሰቡ መኖሪያ ከርቸሌ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህንን ሳያደርጉበሌሎች ላይ ጣት መቀሰሩ ግን የአንድ ሰሞን ሆይ ሆይታን ከመፍጠር የዘለለ ትርጉም አይኖረውም፡፡ ሼህ ሙሐመድ መታሰራቸው እንደተሰማ “የድርጅቱ ባለቤት የሉም፣ ታስረዋል፣ አይመጡም…” በሚል አስተሳሰብ አንዳንድ ወገኖች በአንዳንድ ኩባንያዎች ላይ ያሳዩትን አሉታዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ እና ከሼህ ሙሐመድ መታገት ጋር የተያያዙ ተጨማሪ ሃሳቦችን ይዤ እመለስበታለሁ፡፡ እስከዚያው ድረስ ሊቀ
መንበራችን እንደሚፈቱም ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ – ኢንሻ-አላህ!!!

PDF  “አንድና አንድን አስር” የማድረግ ተልእኳችንን እንወጣለን!

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *