ሰማኽኝ ጋሹ አበበ (PhD)The Amhara people and Ethiopian regime (TPLF)

ከየትኛዉም የአለም ክፍል በተለየ መልኩ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሜዳ የሁሉም ግራ የፖለቲካ ድርጅቶች አፍ መፍቻ የሆነዉ የብሄር ጭቆና ትርክት በዝነኛዉ የስታሊን “Marxism and the National Question” ፅሁፍ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በቀድሞው ሶቭየት ህብረትም ሆነ በኢትዮጵያ አንድ ብሄር ሌሎችን ጨቁኑዋል በሚል አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ነዉ። በሶቭየት ህብረት የጨቋኝነት ካባ የተሰጠዉ ለሩስያ ብሄር ነበር። ስታሊን በ1923 በተካሄደዉ 12ኛዉ የሶቭየት ኮሚኒስት ፓርቲ ኮንግረስ ‘ የብሄረሰቦች መብት መከበር ትልቁ እንቅፋት የሩስያ ትምክህተኝነት ነዉ’ ብሎ ነበር።

በእኛም አገር የበቀሉትና የስታሊንን እንቶ ፈንቶ ያነበንቡ የነበሩት (ሁንም ያሉት) የግራ ፖለቲከኞች አማራዉ ጨቋኝ ሌላዉ ብሄረሰብ ተጨቋኝ እንደሆነ በግልፅ አቋም የወሰዱበት ጉዳይ ነዉ። ይህን ለማረጋገጥ የዋለልኝን ፅሁፍ ፥ የህወሃትን ፕሮግራምና የአንዳንድ ፅንፈኞችን ቃለ ምልልስ ማየት በቂ ነዉ። አሁንም ድረስ አንድ ሰዉ ስለኢትዮጵያ አንድነት ወይም የጎሳ ፖለቲካን በመቃወም ሲናገር ‘ ነፍጠኛ ፥ ትምክህተኛ፥ የቀደመዉ ስርአት ናፋቂ’ የሚባለዉ ‘ አማራ ጨቋኝ ነዉ’ ከሚለዉ ትርክት የሚነሳ ነዉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአማራዉ ማህበረሰብ እያመረረ ሲመጣ ስለታየ ‘ አማራ ጨቋኝ’ ነዉ አላልንም ገዥዎችን ነዉ የሚል አባባል እየሰማን ነዉ። ነገር ግን ይሄ ሸፍጥ ነዉ። ጨቋኝ የአማራ ስርአት የሚባለዉ ከወደቀ ከ40 አመት በሁዋላ የአማራዉ ማህበረሰብ የሚገደለዉ፥ የሚሳደደውና የቀደመዉ ስርአት ናፋቂ እይተባለ የሚሰደበዉ አማራዉ ጨቋኝ ነዉ የሚለዉ አስተሳሰብ በማሀበረሰቡ ዉስጥ እንዲሰርፅ ስለተደረገ ነዉ።

እዉነተኛ እርቅና ምናልባትም አንድነት ሊፈጠር የሚችለዉ አማራን በጅምላ ጨቋኝ ብለን መፈረጃችን ስህተት ነበር በማለት የኦሮሞ፤ ትግራይና የሌሎች ብሄር ኢሊቶች አምነዉ ይቅርታ መጠየቅ ሲችሉና አማራዉን ትምክህተኛ እያሉ ማሳደድና ማሸማቀቅ ሲያቆሙ ነዉ። አሁን እንደምንሰማዉ ግን አይ እኛ አማራዉን ጨቋኝ አላልንም የሚለዉ በገሃድ የሚታየዉን ነገር መካድ ስለሚሆን የትም አያደርሰም።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *