በይርጋ አበበ

የህወሓት ታጋይና በኋላም የአየር ኃይል አዛዥ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ከአየር ኃይል አዛዥነታቸውና ከህወሓት/ኢህአዴግ አባልነታቸው ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ሆነው ቆይተዋል። በኋላም በጡረታ ተገልለዋል። ኢህአዴግ ሥልጣን መልቀቅ የነበረበት በ1987  ዓ.ም ነበር። ሆኖም ሁልጊዜም እኔ አውቅልሃለሁ በሚለው አመሉ እሥካሁን ሥልጣን ላይ ቆይቷል ሲሉ ይናገራሉ። በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርገዋል። ይህንንም ቃለምልልስ ለአንባቢያን በሚመች መልኩ አዘጋጅተን አቅርበነዋል።

 

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

ሰንደቅ፡- ውይይታችንን በወቅታዊ ጉዳይ እንጀምር። አገራችን የምትገኝበት ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዴት ያዩታል?

ጄኔራል አበበ፡- ጠቅለል አድርገን ስናይ ሁለት ነገሮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ወቅታዊ ጉዳይ ነው። በሌላ በኩል ደግሞመሠረታዊ የሕገ-መንግሥት ጉዳይ አለ። 

ሕገመንግሥት በእኔ አመለካከት የኢትዮጵያን የሰላም፣ የዴሞክራሲ እና የልማት ጉዞ የቀየሰሕገመንግሥት ነው። ለኢትዮጵያም የሚበጃት አሁን ያለው ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ነው።
 ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ ችግርየለበትም። ችግር ያለበት በፖለቲካው የመንግሥት ሥርዓቱ ነው። ይህ ችግር ደግሞ መሠረታዊ የዴሞክራሲ ችግር ነው። የዴሞክራሲችግር ባይኖርበት ኖሮ አሁን ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ አይታይም ነበር።

በነገራችን ላይ የፖለቲካ ቀውስ የሌለበት አገር ያለ አይመስለኝም። በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካ አለ። ልዩነቱ እነሱ ጋ ያለው የቀውሱደረጃ እና ቀውሱ የሚፈታበት መንገድ ነው። በእነሱ የችግር መፍቻ ተቋሞች አሉ። እኛ ጋ ግን እንደዚህ አይነት መሠረታዊ የሕዝብጥያቄዎች በሚነሱበት ጊዜ መልስ ሊሰጡ የሚችሉ ተቋሞች የሉንም።

ሰንደቅ፡- ቀውስ መፍቻ ተቋማት የሚሏቸው የዴሞክራሲ ተቋሞች የሚባሉትን ነው፤ የሲቪክ ማኅበራትን? ሙሉውን ቃለ ምልልስ በፒዲኤፍ እዚህ ላይ ተጭነው ያንብቡ  ሜጄ አበበ ተክለሃይማኖት

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *