ከ70 ዓመት በላይ የሚሆኑ አዛውነት ዜጎች፣ እናቶች፣ እድሜያቸው ከአስር አመት በታች የሚሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆች የአሰቃቂው ድርጊት ሰለባ ናቸው

ባልተለመደ መልኩ የዋናውን አስፓልት መንገድ በመተው የጫኑት አቃና ንብረትነታቸው የማን እንደሆነ የማይታወቅ ስምንት ከባድ የጭነት መኪናዎች ወደ ገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ይዘልቃሉ። ሕብረተሰቡ ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለ ጉዳይ አይቶ ስለማያውቅ ይጠይቃል። መኪኖቹ ህገወጥ ኮንትሮባንድ ጭነዋል በሚል እንዲፈተሹ ይጠይቃል።
የጭነት መኪናዎችቹን ማስፈተሽ ያልፈለጉት ” የመከላከያ አባላት” ለህዝቡ አግባብ ያለው ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ” አብረን እንፈትሽ” በሚል ህዝቡን አታለው ጥቃት መፈጸማቸውን ድብዳቤው ያመለክታል። ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት፣ ለመከላከያ ሚኒስትር፣ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ በአካባቢው ለሚነቀሳቀሱ የተለያዩ የጦር ክፍሎች… ወዘተ የተበተነው ደባዳቤ እንዳለው ” ሕዝቡ ተታሎ ኢሰብአዊ ጥቃት ተሰንዝሮበታል። ሶስት ሲገደሉ፣ 19 ቆስለዋል።
ዲሽቃ፣ ዙ-23፣ መትረየስና ስናይፐር የታጠቁት ክፍሎች በወገን ቀርቶ በአንድ ወራሪ የጠላት ሃይል ላይ ሊደረግ በማይገባ መልኩ ኢሰብአዊ ድርጊት መፈጸሙን ያስታወቁት የቦረና ዞን አስተዳዳሪ ሊበን አሬሮ ” ይህ ደብዳቤ የደረሳችሁ ማንኛውም የመንግስት አካላት፣ በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ የተወሰደውን ኢሰብአዊ ድርጊት በመገንዘብ …. ” ሲሉ ሃዘን የተሞላበት ማሳሰቢያ በማቅረብ ፍትህ ተማጽነዋል። አያይዘውም የዚሁ ግፍ የፈጠረውን ስሜት ክፉ መሆኑንንም ጠቁመዋል። ዱላ ባልያዘ ህዝብ ላይ እንዲህ ያለ ድርጊት መፈጸም ከቶውንም አግባብነት የሌለው መሆኑንን አመልክተዋል።

ደብዳቤውን ተከትሎ መንግስት በጥቅሉ ኮንትሮባንድ ውስጥ የገቡ በሚል በየዕለቱ ከሚናገረው ውጪ ይህንን ጉዳይ አስመልከቶ በተለያዩ ጊዚያት በሚቀርቡ መግለጫኦውች ያለው ነገር የለም።

ፎቶ- የቦረና እናት

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

ደብዳቤውን ያንብቡ

borena letter 1ኅኅኅህ

borena letter 2

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *