አብዛኞች እንደሚሉት ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ችግር የሌለባቸው ወገኖች በቴዎድሮስ ካሳሁን ስራዎች ላይ ጥርስ ሊነክሱ አይችሉም። አለያም የአርቲስቱ ከህዝብ ጋር ያለው ግንኙነትና ፍቅር የሚያበሳጫቸው አካላት ካልሆኑ በስተቀር በአገር ደረጃ ማዕቀብ ሊጣልበት አይገባም። ለባለሃብቶች አለማለቅለቁና የህዝብን ስሜት በማንጸባረቁ የተነሳ በችግር ውስጥ ሊያልፍ እንደማይገባ በተደጋጋሚ ብዙ ተብሏል።

አሁን የጎሳ ፖለቲካ አገሪቱን አላምጦ ሊሰለቅጣት ጫፍ በደረሰበት ወቅት ” ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” የሚሉ ፖለቲከኞች ራሱ ህወሃትን ጨምሮ ይህንን ሱስ የሚሉትን ኢትዮጵያዊነት ቴዎድሮስን ከፊት በማስቀደም ቢያራምዱት ትርፋማ ስለመሆናቸው የሚያጠራጥር አይደለም፤ ዛሬ የአማራ ክልል ሸንጎ ላይ አቶ መርሃ ጽድቅ የቴዎድሮስን ” ማሬ” የሚለውን ፍቅር እስከመቃብር ባጭሩ ዘፈን በክልላቸው ሚዲያዎች አለመስማታቸው እንደሚያስገርማቸው ተናገረዋል።

አማራ ክልል ለዘፈኑ ቀዳሚ መሆን ሲገባው ራስን በማቀብ ይሁን በፍርሃትና በትዕዛዝ በውል ባለተገለጸ መልኩ የክቡር ዶከተር ሃዲስ አለማየሁን ውብ መጽሃፍ አቀናብሮ ያቀረበውን የቴዎድሮስን ዘፈን አለማቅረብ የምክሰር ያህል መሆኑንን አቶ መርሃ ጽዮን ያስታወቁት። ወጋየሁ ለመጽሃፉ ውበት እንዳፈሰሰበት የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ ፣ የቲዎድሮስን ይህንን ዜማ በአማራ ክልል አለመስማት አስገራሚ እንደሆነባቸው አመላክተዋል።

የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ዘፈኑን ሳያነሱ በደፈናው ” የከለከለ የለም” ለማለት ዳድቷቸዋል። ሁሉምነገር ነጻና ክፍት እንዲሁን ድጋፍ ይሰጣል በማለት ዴሚክራሲያዊ አሰራር እንዳለ አመላከተዋል። ለወደፊቱም ቢሆን  ያለ አንዳች ገደብ በነሳነትና በሃላፊንት ባለሙያዎች ያመኑንበትን እንዲያከናውኑ የክልሉ ፍላጎት መሆኑንንም አመልክተዋል።

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *