ስደተኞቹ በዋነኝነት ወደመጡበት ሃገር እንዲመለሱ ይደረጋል። ይህ እርምጃ ከሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካውያን ስደተኞች በባርነት ሲሸጡ የሚያሳየው ቪዲዮ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተወሰደ ነው። via –  BBC AMHARIC

በሊቢያ እስር ቤቶች ስቃይ የሚደርስባቸው ስደተኞች በአሰቸኳይ የሚወጡበት እቅድ ሊተገበር ነው። ይህ አፋጣኝ ውሳኔ የተላለፈው በአይቮሪኮስት ዋና ከተማ አቢጃን በተካሄደው የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ጉባኤ ላይ ነው። በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈው የሊቢያ አስተዳደርም ስምምነቱን ተቀላቅሏል።

ሆኖም አካባቢዎቹን የመቆጣጠር አቅሙ አነሰተኛ በመሆኑ እቅዱን እንዴት ሊተገብር እንደሚችል ጥያቄ እየተነሳ ነው። ስደተኞቹ በዋነኝነት ወደመጡበት ሃገር እንዲመለሱ ይደረጋል። ይህ እርምጃ ከሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካውያን ስደተኞች በባርነት ሲሸጡ የሚያሳየው ቪዲዮ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተወሰደ ነው።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አውሮፓ ለመግባት የሰሃራ በረሃንና የሜዲትራኒያን ባህርን ያቋርጣሉ። በሺዎች የሚቆጠሩት መንገድ ላይ ሲሞቱ የተረፉትም ቢሆኑ ምንም ገንዘብ ስለማይኖራቸው በሊቢያ ለዘመኑ የባርያ ንግድ ይጋለጣሉ።

ሊቢያም ቪዲዮው ከተለቀቀ በኋላ በግብርና ሥራ ባሪያ ሆነው ለሚያገለግሎ እስከ 400 ዶላር በወረደ ዋጋ ሰዎች እንዴት እንደሚሸጡ ለማወቅ ምርመራ ጀምራለች። ናይጄሪያ በበኩሏ ባለፈው ማክሰኞ 240 ፈቃደኛ ስደተኞችን ወደቤታቸው በመመለስ የራሷን እርምጃ ወስዳለች።

በጉባኤው ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ”አስቸኳዩ ተልዕኮ” ሊቢያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ቻድና ኒጀርን ጨምሮ በ 9 ሃገራት ስምምነት መደረሱን ተናግረዋል። ተልዕኮውን ለማስፈጸም ሊቢያ እነዚያ አስደንጋጭ ትዕይንቶች የሚፈጸሙባቸውን ካምፖች የመለየት ኃላፊነት ተጥሎባታል።

በተባበሩት መንግስታት የሚደገፉት የሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ ሳራጅ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ወደ ካምፖቹ እንዲገባና ስደተኞቹ በቀጣይ ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ እንዲወጡ የመጠየቅ ፈቃድ ለመስጠት ተስማምተዋል። ስደተኞቹ ከመጡባቸው ሃገራት ጋር በመቀናጀት “ሥራው በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል” ያሉት ሚስተር ማክሮን፤ በተለይ ለከፋ ችግር ሊጋለጡ የሚችሉት ስደተኞች አውሮፓ ውስጥ ጥገኝነት ሊያገኙ እንደሚችሉ ጨምረው ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረት ምንጮች ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅትን ጨምሮ የእርዳታ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ሃገራት የመጡ 13ሺህ ስደተኞችን መልሰው አቋቁመዋል።

የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት በስብሰባቸው ጨምረው እንደተስማሙት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩትን ኢላማ በመድረግ ስደተኞችን የሚያዘወውሩ ቡድኖችን በማፈራረስ ንብረቶቻቸው እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ ግብረ-ኃይል ይቋቋማል።

ነገር ግን የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት፤ የአውሮፓ ህብረትን ስደተኞች ለችግር እንዲጋለጡ አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል ብለው ይከሳሉ። ምክንያቱም ከሊቢያ ወደ አውሮፓ የሚያቀኑ ስደተኞችን ይዘው ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ ሲያደርጉ የበለጠ ለችግር እንዲጋለጡ ያደርጋል በማለት ነው።

በሊቢያ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ተልዕኮ እንደሚሉት ዋና ተጠሪ ኦትማን ቤልቤሲ በሊቢያ ያሉት ስደተኞችን የሚያዘዋውሩ ህገወጥ ቡድኖች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ እየተጠናከሩ ነው።

Image copyrightREUTERS

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *