በተለያዩ ማህበራዊ ገጾችና የመረጃ መረቦች የሚሰማው ፣ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ” በዚህ አጋጣሚ ህይወቱን ያጣው ወንድማችን ነብሱን በገነት ያኑረው” ሲሉ አንድ ሰው ህይወቱ ማለፉን አረጋግጠዋል። እንደ መረጃዎቹ ከሆነ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል።

የመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ከወልደያ ጋር ለመጨወት ወደ ወልድያ ሲያመራ በርካታ ደጋፊዎች ተከትለውታል። ደጋፊዎቹ ወልዲያ ከተማ በጭፈራ መልክ ነገር ጀመሩ የሚሉ አሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ” ወደ ከተማ እንዳይገቡ ተከለከሉ” የሚሉም አሉ። ምንም ተባለ ምን ግን በምስል የተደገፉ መረጃዎች እንደሚያስረዱት ግጭቱ ከፍተኛ የሚባል፣ ንብረት የወደመበት፣ የንግድ ሱቆች የተቃጠሉበት፣ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች የታዩበት፣ ጥይት የተተኮሰበትና አስለቃሽ ጭስ የተረጨበት ነው።

የትግራይ ክለቦች ወደ አማራ ክልል ሲሄዱና የአማራ ክልል ቡድኖች ወደ ትግራይ ሲሄዱ ግጭት፣ ፍትጊያ፣ ዱላና ድብደባ ሜዳ ውስጥና ከሜዳ ውጪ መታየት የተጀመረው የፖለቲካ ግለቱ ከተፋፋመ ጀምሮ ነው። ሁሉም ወገኖች እንደሚሉት የትግራይ ክለቦችና ከአማራ ክለቦች ጋር መጫወጥ የማይጭሉበጥ ደረጃ ደረጸዋል። ይህ ፖለቲካው የሰለበው ስፖርት ከዚህ በላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት ወደማደረስ እንዳያመራ ፍርሃት አለ።

5D7EB083-9C08-4674-9A22-B891C711EDFF

ሰዎች ስፖርትን የታመቀ ስሜታቸውን የሚገልጹበት መድረክ ማድረጋቸው ምን ጊዜም የማይቀር በመሆኑ ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት ግድ ነው። ዛሬ በወልደያ እንደታየው የትግራይ ደጋፊዎች በሰራዊት ኮምቦይ እየታጀቡ የሚንቀሳቅሱት እስከመቼ ነው? የትስ ጋር ይቆማል? አቶ ሲሳይ ንጉሱ እንደ አንድ ባለሙያ ሳይሆን የክልል አፈ ቀላጤነት ሳይሆን እንደ አንድ መርዶ አርጂ  በፌስ ቡክ ገጻቸው ይህንን ብለዋል

መረጃ ስለ ወልዲያ
በተፈጠረው ረብሻ ምክንያት አንድ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል ሲረዳ የነበረ ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን የተለያዩ ሱቆች እና ተቋማት ዘረፋ ተካሂዶባቸዋል። እንዲያው ለመሆኑ ከኳስ ጨዋታ ጋር የተያያዘ ግጭት እና ክቡር የሆነው የሰው ህይወት መጥፋት እና ሰው ለፍቶ ያፈራውን ሀብት መዝረፍ ምን ያገናኛቸዋል? ኳስ ሌላ ዘረፋ ሌላ !!! ይህ ተግባር ሰላም አያመጣ፣ኳስ አያሳድግ ፣ሀገር አይገነባ!! ሰላም ወዳዱ እና እንግዳ ተቀባዩ የወሎ ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን ሰላሙን የሚያደፈርስ ተግባር በአስቸኳይ ሊያስቆም ይገባል። በአይነቱ ልዩ የሆነ ስቴዲየም ይዞ እንዲህ ዓይነት ነገር ሲገጥመው ቆም ብሎ ማሰብ ይገባዋል። በዚህ አጋጣሚ ህይወቱን ያጣው ወንድማችን ነብሱን በገነት ያኑረው እንላለን። ይላሉ አቶ ንጉሱ  አክለውም በደሴ ከተማ የተካሄደው ጨዋታ በሰላም ተጠናቋል። ብለዋል

woldeya

 

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ይህ የተሰናከለና የተንጠራወዘ የመንደር ወሬ የሚመስል መረጃ አንድን ክልል ከሚወክል የመርጃ አቀባይ መሳማት በሚዲያ ቋንቋ ግልብነት ነው። ሃላፊነት የሚሰማው አካል መረጃዎቹን ስብስቦ በአግባቡ ሪፖርት ያደረጋል እንጂ አይዘላብድም። ወይም ጎጎሎ መረጃ አያቀብልም። ቢያንስ የጉዳቱን መንስኤ፣ የጉዳቱን መጠን፣ማን ጉዳት አደረሰ? ማን ሰለባ ሆነ፣ አጋዚ ለማን ወገነ? ሲጀመር ማን ፊሽካ ነፋ የሚሉትን መሰረታዊ ጉዳዮች ከቦታ፣ ጊዜና መቼት ጋር ቀምረው ማቅርብ ይግባቸው ነበር። ስራቸውም ነው። 

የወልደያ ነዋሪዎች የህወሃትን ስም በመጥራት ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደበር የቪዲዮ መርጃዎች አሉ። በሌላም በኩል ከተለያዩ ከተሞችም ወገናዊነትን መነሻ ያደረጉ አቋሞች ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ነው። ዘረኝንተ የበላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይድን መታመሙ ከዚህ በላይ መገለጫ የለውም!! 

 

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Nigu

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *