በሐይለገብርኤል አያሌው – የቀድሞው መዐሕድ አመራር አባል

የመቀሌው ስብሰባ ማራቶን ሹምና ሽረቱ የመግለጫ ጋጋታው የጥልቅ ተሃድሶው ውጤት ከግር ጥፍሩ እስከ ዶቃ ማሰሪያው በንጹሀን ደም ለጨቀየው የሌባና የሰው በላ የወያኔ ቡድን ለዳግም ግፍ ለበለጠ አፈና በሚያመቸው መልኩ የጭካኔ ጠበብቶቹን መሪ አድርጎ ሊዘምትብን መዘጋጀቱን አውጇል። የሕዝብ ለህዝብ መተላለቅን የሚሰብኩ ጀሌዎቹን አሰልፎ በሕዝባችን ላይ ከነመርገሙ ሊጫንብን አፈር ልሶ ተነስቷል:: የህወሃት ትዕቢት ጨለምተኝነቱና ለህዝብ ያለው ንቀት ድንበር የለሽ በመሆኑ አማራና ኦሮሞን በእሳትና ጭድ መስሎ በአደባባይ የተናገረውን ስቅላት ይገባው የነበረን ጸረ ሕዝብ ግለሰብ ከፍ ላለ ወንበር መሾም ነደው እንዲጠፋ በተመኘላቸው ሕዝቦች ላይ ሌላ ዙር የከፋ ዘመቻ አቅዶ ለመነሳቱ አመላካች መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም::

የትግሬ ነጻ አውጪውን ወያኔን በተንኮሉ አይነት በጭካኔው ደረጃ በክፋቱ ልቀት ሰይጣንን በእድሜ ካልሆነ በተገባር እንደማይስተካከለው በማህበራዊ ድህረገጽ ያየሁት አባባል የወያኔዎችን ባህሪ በሚገባ ያሳያል። ኢትዮጵያን በመሰለ የደጎችና የመንፈሳዊያን ምድር እንዲህ በድርጊቱ ከዲያቢሎስ የከፋ አረመኔ አገዛዝ በታሪኳ ገጥሟት አያውቅም። ከአንድ መሐጸን የፈለቁትን አቤልና ቃዔልን ደም ያፋሰሰ ጋኔል ፤ በትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ተበልጦ በዘመናት አብሮነት እንደ ሰርገኛ ጤፍ ተቀላቅለው የኖሩትን የአማራና የኦሮሞ ወንድማማች ነገዶች በሃሰት ወሬ ፤ በጥላቻ ቅስቀሳና ፤ በፈጠራ ታሪክ የተሳሰሩበት ገመድ እንዲላላ አብሮነታቸው ጥርጣሬ እንዲያጠላበት የማድረጉ ሴራ ተሳክቶለት ላለፉት 26 አመታት ፍላጎቱን ለማሳካት አስችሎት ቆይቷል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ   amhara-and-oromo-unity

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *