ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ለማ መገርሳ የኦሮሚያ የጸጥታ መዋቅርና ፖሊስ ከህዝብ ጋር እንዲቆም አሳሰቡ- ጨለንቆ ማን ግደሉ እንዳለ ክልሉ አያውቅም

” ማን እንደላካቸው አናውቀም። ማን እንዳዘዛቸውም አናውቅም” በማለት ነው ገዳዮቹን የገለጿቸው። በጨለንቆ የተፈጸመውን ግድያ ክልሉ ካላወቀው ማን ሃላፊነት ይወስዳል? የሚለው ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ የሆነውም አቶ ለማ በክልሉ መገናኛ ይህንን ለሕዝብ ይፋ ካደረጉ በሁዋላ ነው።

” በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ ድርጊቱን ያወገዙት የኦሮሚያ አዲሱ መሪ፣ “የሰላም ሃይል” ሲሉ የጠሩት የክልሉ የጸጥታ መዋቅርና የፖሊስ ሃይል ከህዝብ ጋር እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ባልተለመደ መልኩ አደባባይ በመውጣት በፌደራል ደረጃ የሚሰራውን ስራ መጋፈጥ የጀመረው ኦህዴድ፣ በመሪው አማካይነት ” ህዝብ ሲጎዳ ዝም ብለን አናይም” የሚል መልዕክት አሰተላልፏል።

አጥፊዎች ካሉ በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩን ያመለከቱት አቶ ለማ ” ማን እንደላከው የማይታወቅ” ያሉት የታጠቀ ሃይል ለፈጸመው ግድያ አስቸኳይ ፣ማጣራት ተደርጎ ህግ ፊት የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ አበክረው ተናግረዋል። የህግ የበላይነት እንዲያስጠብቅ የሚጠበቅበት ሃይል እንዲህ ያላ ተግባር መፈጸሙ የክልሉን መንግስት እጅግ እዳሳዘነ አመልክተዋል።

chelenqo1

የጨለንቆ ከተማ ነዋሪ የሆኑና በወቅቱ በስፋርው ሆነው መታዘባቸውን የገለጸ የአይን እማኝ ለጀርመን ሬዲዮ እንደተናገሩት ሰርቆማ በምትባል የሶማሊና የኦሮሚያ ድንበር ላይ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አንድ ሰላማዊ አርሶ አደር ይገላሉ። የሰውየውን መገደል የሰሙ የጨለንቆ ወጣቶች የወረዳውን አስተዳደር መኪና በመጠየቅ፣ ሌሎችም በቀጥታ ወደ ስፍራው ሊያቀኑ ሲሉ የመከላከያ ሰራዊት ተኩስ ከፈተ። እሳቸው እንዳሉት 18 የሚሆኑ ንጹሃን ተገደሉ። አቶ ለማ 15 መገደላቸውን ይፋ ቢያደርጉም እማኝ ነኝ ያሉት የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀሩ መግደላቸውን መሰከሩ።

አስራ አንድ የሚሆኑት በአን ስፍራ ቀብራቸው ሲፈጸም፣ የተቀሩት አስከሬናቸው ወደሚኖሩበት ቀበሌ ገበሬ ማህበር መላኩን በአይኔ አይቻለሁ ሲሉ ነው የአይን እማኙ ያስታወቁት። በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል ምን የተጀመረው ደም አፋሳሽ ውዝግብ መቆሚያው ግራ የሚያጋባ ሆኗል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩትን ያፈናቀለው የሁለቱ ክልሎች ችግር ሚስጥር ተራ የኮንትሮባንድ አዙሪት መሆኑንን ኢህአዴግ በተደጋጋሚ ቢያስታውቅም እርምጃ መወሰድና ማስቆም ያልቻለበት ምክንያት እንቆቅልሽ ሆኗል።

chelenqo3

የኮንትሮባንድ ንግዱ ላይ ተሰማርተዋል የሚባሉት ክፍሎች የማይነኩ መሆናቸው እርምጃ አወሳሰዱ ላይ ጫኛ ማሳደሩን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናጋራሉ።

በሌላ ዜና በሻምቡ ካምፓስ የትፈጸመውን ብሔርን የለየ ጥቃት አቶ ለማ አውግዘዋል። በስሜታዊነት መነዳት አግባብ እንዳልሆነ ያመለክቱት አቶ ለማ ድርጊቱ በየትኛውም መስፋርት ተቀባይነት የሌለው መሆኑንን አበክረው ተናገረዋል። ማሰብ እንደሚያስፈልግ ደጋግመው የጠቆሙት አቶ ለማ አስበን ካልሰራን የምንሰራው ይበላሻል” ሲሉ ማስጠኝቀቂያና ምክር ለግሰዋል። በሻምቡ ካምፓስ ሁለት የትግራይ ተወላጆች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። መንስኤውም ቀደም ሲል በአዲግራት ዩኒቨርስቲ የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉና ቁጥራቸው አሁን ድረስ በው፤ ያልታወቀ ተማሪዎች በብሄር ተኮር ጥቃት መቁሰላቸው መሆኑ ተአውቋል። 

በኦሮሚያና በአማራ ክልል በርካታ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት የቆመ ሲሆን ተቃውሞውም እየከረረ መሆኑ ተሰምቷል። ገጭቶቹ ከዚህም በላይ ሄደው መስመር እንዳይለቁ ፍርሃቻ አንዳለም በተደጋጋሚ እየተጠቆመ ነው።

foto OMN

0Shares
0
Read previous post:
የመረጃ ጠላፊዎች ከኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ከ10 ሚሊየን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ ዘርፈዋል

የሩሲያ ቋንቋ የሚናገሩ የመረጃ ጠላፊዎች የኤ ቲ ኤም ማሽኖችን በመጥለፍ በአሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና ሩሲያ ከሚገኙ...

Close