በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ መቋረጡን፣ ስብሰባው የተቋረጠውም ኦህዴድና ብአዴን ስብሰባውን ረግጠው በመውጣትቸው ነው። ጉዳዩ ከነጻና ገለልተኛ እንዲሁም ከኢህአዴግ ወገን ማረጋገጫ ባይሰጥበትም፣ ሁለቱ ድርጅቶች ስብሰባውን ረግጠው የወጡት በአሁኑ ሰዓት በክልላቸው ባለው ሁኔታ ነው።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሐመድ ያሰራጨው መረጃ እንደሚያስረዳው ሁለቱ ድርጅቶች ኦህዴድና ብአዴን ለተጨማሪ እርምጃዎች የየራሳቸውን ስራ አስፈጻሚ አስቸኳይ ስብሰባ ለነገ መጥራታቸውም ተጠቁሟል። አቶ ሃይለማሪያም ፓርላማውን ማምሻውን እንዲሰበሰብ ጥሪ ቢያስተላልፉም ስብሰባው ቦይኮት መደረጉ ተጠቅሷል።

በዚህ የማያበቃው የኦህዴድና የብአዴን አቋም በክልላዊ ጉዳዮች ህግን በተላለፈ መልኩ የሚፈጸመውን ግድያና ከህግ አግባብ ውጭ፣ ህገመንግስቱን በሚጻረር መልኩ የሚከናወነውን ጣልቃገብነት እና በሲቪል ዜጎች ላይ በእብሪተኝነትን ወታደሮች የሚወስዱትን እርምጃ ለመከላከል አቋም የመያዝ እቅድ እንዳላቸው አቶ ጁሃር ያሰራጩት መረጃ አመልክቷል። 

የአቶ ጁሃር መረጃ በማስተባበልም ሆነ በመደገፍ ገለልተኛ ወገኖች ይህ እስከታተመ ድረስ ያሉት ነገር የለም። የስብሰባውን መጀመር ይፋ ያደረጉት የኢህአዴግ ልሳኖችም የስብሰባውን ውሎም ሆነ አቅጣጫ አስመለክቶ ምንም አልዘገቡም። በደፈናው ግን መጠኑ ባይጠቀስም ከፈተኛ የሚባል ውሳኔ እንደሚወሰን ነው ቀደም ብለው የገለጹት።

ኦህዴድና ብአዴን ከህወሃት ጋር ያላቸው የቀደመው ግንኙነት የተበላሸ ደረጃ ላይ መድረሱ፣ የበታች ካድሬዎች ማፈንገጣቸው፣ ከፍተኛ የሚባሉት አመራሮችም ቢሆኑ ለበታች ካድሬዎች ታማኝ መሆናቸው በኦፊሳል ሲነገር መሰንበቱ ይታወሳል። በዚሁ መነሻ ” ጥልቅ ተሃድሶ” በሚል ስር ነቀል ለውጥ እንደሚደረግ ቃል የተገባ ቢሆንም የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታና ሰላም እያሽቆለቆለ ይገኛል። አቶ ጁሃር ይህንን ነው ያሰራጩት።

The EPRDF executive committee meeting the began yesterday has been discontinued as OPDO and ANDM walked of meeting citing the ongoing situation in the two regions. Both ANDM and OPDO said to have called for an emergency meeting for their perspective central committees for tomorrow to discuss further steps. The puppet minister also invited members of parliament for discussion this evening but it was boycotted.
NOT nearly enough. They need to clearly and publicly speak against the unconstitutional intervention in regional affairs and extrajudicial killings of the military and, take decisive action to protect civilians against the madness of the generals or step aside!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *