የቀድሞው የታማዦር ሹም ጄነራል ጻድቃን ባልተጠበቀ ሁኔታ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ተመልካች መሆን እንደማይጋባት አጠቃላይ ምስራቅ አፍሪቃን የቃኘ ትንታኔ ሰጡ። ኤርትራ ላይ ያለውን መንግስት ማንኛውንም ዓይነት ዘዴ፣ ሃይልን ጨምሮ በመጠቀም ማስወግድ ግድ እንደሆነም አመልክተው ነበር።

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝም በኤርትራ ላይ አዲስ ፖለሲ መከተል እንደሚጀመር ከትግራይ ህዝብ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልሥ ሲሰጡ አስታውቀው ነበር። No war, No peace በሚል መጠቅለያ ሃሳብ አክቲቪስቶች፣ አፍቃሪ ኢህአደግ የሆኑ ምሁራንና ሚዲያዎችም ድርጅታቸው ወደ አንድ መፍትሄ እንዲያመራ ሲገፉም ነበር።

ሁሉም ክፍሎች ጀነራሉን ጨምሮ ሟቹ መለስ “ቀይባህርን  አንፈልግም” በሚል የአገሪቱን ድርሻ ሰርግና ምላሽ አድርገው ሲያስረክቡ አልተነፈፈሱም ነበር። ይልቁኑም ” አሰብ የግመል መፈንጫ” ይሆናል የሚል የነተበና በተንኮል የተለወሰ ምላሽ ሲሰጡ እኒህ ክፍሎች አድናቂና የገደል ማሚቶ ነበሩ።

ዛሬ በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልል፣ እንዲሁም በተለያዩ ክፍሎች ተቃውሞ ሲያይል ይህ ድሮ በትኩሱ መላ ሊባል የሚገባውን የቀይ ባህር ጉዳይ ከጣሉበት ጉሮኖ አነሱት። የኤርትራ ህዝብ ካፈራው ንብረትና ከኖረበት ቀዬ እየተጎተተ ሲባረር፣ በተመሳሳይ ኤርትራ ኢትዮጵያዊያኖችን አሽቀንጥራ ስትወረውርና ሃብታቸውን ስትዘርፍ ደንታ ያልሰጣቸው ክፍሎች ዛሬ ስለ ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መዘመርና ማልቀስ መጀመራቸው ሰፊውን ህዝብ እያስገረመ ነው።

ተጨማሪ ይህንን ያንብቡ ኢህአዴግ – አስመራ ላይ ምን አሰበ? ” ጥልቅ ጥናት እየተደረገ ነው፤ ተግባራዊ የሚያደርገው ሕዝብ ስለሆነ ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል” ሃይለማሪያም ደሳለኝ

የመሃሉን ፖለቲካ ጎሳና ዘር እንደ አረም ወረውት አብሮ መማር፣ አብሮ ኳስ መቻወት፣ በነጻነት ማለፍና ማግደም… አስቸጋሪ ሲሆን የኢትዮጵያና ኤርትራ ማቆሚያ የሌለው ችግር አሳሰበን የሚሉ የሃይማኖት ተቋማት ሰራተኞች፣ የኈቱን ሕዝቦች እንወክላለን የሚሉ አካሎች የመታየታቸው ጉዳይ በበጎ ቢታይም፣ እነዚ የሃይማኖት ተቋማት መጀመሪያ አገር ቤት ያለው ቀውስ ለዓይናቸው አልሞላ ብሎ ነው የኤርትራን ጉዳይ ቅድሚያ የሰጡት? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

የዓለምአብያተ ክርስቲያናት ምክርቤት ሁለቱን አገሮች ለማስታረቅ ደፋ ቀና ማለቱን የነገሩን የአገራችን ” የሃይማኖት ባቶች” አገር ቤት በየቀኑ ሰው እያለቀና ፖለቲካው ውሉ እየጠፋ፣ በራሱ በኢህአዴግ ቋንቋ ” መጠራጠር ሊያጠፋን ነው” የሚለውን ጩኽት እየሰሙ ዝም ማለታቸው አሳፋሪ ይሆናል። እንደ እምነት መሪም ብቃትም ሆነ ቅድስና የራቃቸው ካድሬዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል። እንዲህ ዓይነት የእምነት መሪዎች የአገሪቱን ባህል፣ ወግ፣ ፈርሃ አምላክ፣ አዛኝነት፣… አጥፍተውታል። ምግባራቸው ከሃላፊነታቸው የሚቃረን በመሆኑ ሰው ክዷቸዋል።

አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ የሃይማኖት መሪዎች የርቅ ሩጫ ፖለቲካዊ ነው። ከፖለቲካነቱም በላይ የሚቀኘው በህወሃት ሰዎች ነው። ይህ መሆኑ ደግሞ እርቁን የሁለት አገሮች አያደርገውም። ጎልጉል የተባለው የድረ ገጽ ጋዜጣ

” በአገር ውስጥ ያለው ሁኔታ እየተወሳሰበና መፍትሔው እየጠፋ ባለበት ባሁኑ ወቅት ህወሓት በማኒፌስቶው ላይ እንዳሰፈረው ትግራይን ሪፑብሊክ የማድረግ ዕቅዱ ከታሰበው ጊዜ የቀደመበት ይመስላል። ለኢትዮጵያ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሰጥተናል እያለ ሲፎክር የነበረው የህወሓት ፈጣሪና ጌታ ሻዕቢያም “ተስፋው” ግቡን አልመታለትም። ከዚያ አልፎ በኢትዮጵያ አንጡራ ሃብትና በህወሓት ተላላኪነት ኤርትራን ሲንጋፖር የማድረግ ሕልሙ ከህወሓት ጋር በከፈተው ጦርነት ቅዠት ሆኖ ቀርቷል። ከነዚህ ሁሉ ጉዳዮች በመነሳት ሁለቱ የወንበዴ ቡድኖች ስምምነት የማድረግ ፍላጎታቸው ባሁኑ ሰዓት ቢነሳሳ የሚገርም እንዳልሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ”  ሲል ከሁለት ሳምንት በፊት ዘግቧል።

በመርሃ ደረጃ እርቅ የሚደገፍ ቢሆንም፣ ህወሃት በአገሪቱ እምነት ስለነጠፈበት አካሄዱን የሚጠራጠሩ ቁጥር አይገልጻቸውም። በግልጽ እንደሚሰማው በዚህ አዲስ የእርቅ ሃሳብ ዙሪያ የሚራወጡት ክፍሎች ማንነትና የወጡበት አስኳል ብሄራቸው ጥርጣሬውን ያሰፋዋል። ከሁሉም በላይ የተመረጠው ጊዜ የሚነሱትን ጥያቄዎች አሳንሶ ማየት እንደማይቻል ያመላክታል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ይህ በንዲህ እያለ “የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች የሰላም ተነሳሽነት” በሚል ከሁለቱም አገር የተወጣጡ ወገኖች አሉበት የተባለ እንቀስቃሴ መጀመሩን ቪኦኤ ትላንት ዘግቧል። በዘገባው ከኢትዮጵያ ወገን የተወከሉት ይፋ ባይሆኑም ከኤርትራ ወገን አቶ ይስሃቅ ዮሴፍ የተባሉ ” ከጀርባ የሚገፋን ከፊት የሚጎትተን የለም” ሲሉ እጅግ ገለልተኛ እንቅስቃሴ መሆኑንን ገልጸዋል።

ፐሮፌሰር መድህኔ ታደሰ ጽሁፍ ሲያቀርቡ የአፍሪቃ ቀንደን፣ የቀይ ባህርን አጠቃላይ ሁኔታ አመላክተዋል። እናም ከየትኛውም ተቋም የሁለቱን አገሮች ችግር እንደማይፈታ ሲናገሩ ተሰምቷል። በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ቀውስ እንዳሳሰባቸው የሚናገሩት ክፍሎች የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማስቀመጥ ወደ ተግባር እንደሚገቡ የቪኦኤ ዘገባ ያስረዳል።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ግለትና ዘር ላይ የተመሰረተው ጥላቻ የወለደው የሰላም ሩጫ ምን ያህል የተሳክ የሆናል? የሚለው ወደፊት የሚታይ ቢሆንም ሁለቱ አገሮች አስጠግተው የሚያደራጁዋቸው ተቃዋሚዎች ጉዳይ አብሮ እየተነሳ ነው። የኤርትራ መንግስት በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም የሰላም ሂደቱ በዓለም አቀፉ ቤትክርስቲያን በኩል ተጀምሯል።

በኤርትራ ያሉ ተቃዋሚዎችን ” ካሮት” የሚሉዋቸው ቢበዙም ለውጥ ያመጣሉ የሚል እምነት ያላቸውም አሉ። ከሁለቱም በተለየ መንገድ አስተያየት የሚሰጡ ክፍሎች ” አንረባም” ሲሉ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ። አማራ አሁን ድርስ በድርጅት ጋጋታ ወኪል እንደሌለው የሚጠቁሙት ክፍሎች ” የኦሮሞ ድርጅቶች ወደ አንድ የመሰባስብ እድላቸውን አስፍተዋል። አየር ላይ ያላው አማራው ነው” ይላሉ።

የሰላም ድርድሩ “የህወሃትና የሻዕቢያ ነው” ሲሉ አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩት ክፍሎች ሌሎች ተቃዋሚ የሚባሉት ድርጅቶች ወደ አንድ ሃሳብ ካልመጡ መጪው ጊዜ ከቁጥጥር ሊወጣና አደገኛ ሊሆንባቸው እንደሚችል ያመለክታሉ። አርቆ ማስተዋል እንደሚገባ የሚጠቁሙ ክፍሎች ነገ ላለማልቀስና በቁጭት ላለመኖር የስካሁኑን ስህተታቸውን ተመልክተው በሁሉም መንገድ መዘጋጀት አስፈላጊ እንደሚሆን ይጠቁማሉ። በተለይ በአማራ ህዝብ ዙሪያ ያሉ ወገኖች ሊያስቡበት እንደሚገባ ይመክራሉ።

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *