አዲሱ የህወሃት ሊቀመንበርና የክልሉ እጩ ፕሬዚዳንት በትግራይ ሕዝብ ስም የሚቆምሩትን ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ተናገሩ። በትግራይ ሕዝብ የሚቆምሩ ሲሉ የተጠቀሙበትን ሃሳብ ግን አላብራሩም። ድርጊቱ ፖለቲካዊ ቁማር ይሁን ሌብነት አፍታተው ያልተናገሩት ዶክተር ደብረጽዮን፣ በአሁኑ ሰዓት ህወሃት ተለቶ ይጥቃት ኢላማ መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም አካሄድ ህወሃትን ማዳከም ስርዓቱን ማፍረስ ተደርጎ የተወሰደ ስልት መሆኑንን ገልጸዋል። 

ፋና የሚከተለውን ዘግቧል

በትግራይ ህዝብና በድርጅቱ ስም የሚነግዱ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡ ይደርጋል- የህውሃት ሊቀመንበር

ለክልላዊና ሀገራዊ ችግሮች አመራሩ ተጠያቂ መሆኑን አዲሱ የህውሃት ሊቀመንበር ገለፁ። ሊቀ መንበሩ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በቀደመው የህውሃት አመራር ወስጥ መናቆር እና በዝምድና እስከ መስራት የዘለቀ ችግር እንደነበር ተናግረዋል።

ዶክተር ደብረፅዮን ከፋና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ በህዝብዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ አመራር ስለተደረገ ሹም ሽር ድርጅቱን ኢላማ ስላደረገው ጥቃት፣ ስለሀገራዊ እና ክልላዊ ሁኔታ አንስተዋል። ሊቀመንበሩ እንደተናገሩት 35 ቀናት በወሰደው የህወሓት ግምገማ የድርጅት የውስጥ ችግር በጥልቀት ታይቷል።

በዚህ ግምገማ የአመራሩ ደክመት ድርጅቱን እንደጎዳው እና የበላይ አመራሩም ስለዚህ ስራው ሲገመገም ብዙ ጉድለት እንደተገኘበት ነው ያመለከቱት። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ቅድሚያ ድርጅታዊ፣ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮችን ገምግሞ ወደ አመራሩ በማለፉም ለእርምጃ ያበቃ ጠንካራ ግምገማ እንዲያካሂድ እንደረዳው ገልፀዋል።

ሶሰት ስራ አስፈፃሚዎችን ከስፍራቸው ያነሳው፣ ለድርጅቱም አዲስ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ያስገኘው ይህ እርምጃ በጠንካራ ግምገማ የመጣ መሆኑን ዶክተር ደብረጽዮን አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅት በስፋት እየታየ ስላለው ህወሓትን ኢላማ ያደረገ የጥቃት ዘመቻም ሊቀመንበሩ ድርጊቱን የቆየ ምንጩም የጠላት ምልከታ ነው ብለዋል። የትግራይ ክልል ከስርዓቱ የተለየ ጥቅም እንዳገኘ አስመስሎ ማቅረብም የዘመቻው ዋና አካል መሆኑን አንስተዋል።

ይህ “ህወሓትን ማዳከም ስርዓቱን ለማፍረስ መሰረት ነው” ከሚል ስሌት የመጣ መሆኑን ያነሱት ሊቀመንበሩ፥ ይህም ዘመቻ የትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ነው ያስታወቁት። በጠላት ሀይል ተቀነባብሮ እየተነዛ ያለው የሃሰት ሀሳብ ብዙዎችን እያሳሳተ መሆኑ እንዳለ ሆኖ እውነታውን መግለፅ አለመቻል ግን የድርጅታቸው ድክመት ተደርጎ መነሳቱን ገልፀዋል።

በህወሓት እና በትግራይ ህዝብ ስም የሚቆምሩ እና በጥፋታቸው ልክም በህግ ያልተቀጡ ግለሰቦች መኖራቸው የችግሩ ሌላ ምንጭ ነው ሲሉ አንስተዋል። ሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶች ጣትን ወደሌላ መጠቆመም አንዱ የችግሩ ምንጭ እንደሆነ ይናገራሉ።

እነዚህ ሁሉ ድክመቶች ተደማምረው ውስጣዊ ተገላጭነትን አስፍተዋል ነው የሚሉት። ለእነዚህ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሄ ፖለቲካዊ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ደብረፅዮን፥ በትግራይ ህዝብ እና በድርጅቱ ስም የሚነግዱ ግለሰቦችም ለህግ እንዲቀርቡ ያደርጋል ብለዋል።

በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ላይ የተጠናቀረውን ዘገባ ዛሬ ምሽት በፋና ቴሌቪዥን ፋና 90 ላይ ይከታተሉ።

በዳዊት መስፍን  (ኤፍ ቢ ሲ) 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *