ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኑን ሕግና ቀኖና ለማሰከበር ባለበት ኃላፊነት በተለይም የምእመናን መለያየት ክፉኛ ስላሳስበው የወሰደው መንፈሳዊ እርምጃ መሆኑ ታውቆ አባ ኃ/ጊዮርጊስ ተሾመ፣ ቄስ አብርሃም ቦጋለ እና ቁስ አለምእሸት አብርሃ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አገልግሎታቸው እውቅና የሌለው በመሆኑ ተቀባይነት ስለሌለው ምዕመናን ይህንኑ በመረዳት ማንኛውንም ክህነታዊ አገልግሎት ከነዚህ ግለሰቦች ባለመቀበል ለቀኖና ቤተክርስቲያን ዘብ እንዲቆም ቤተክርስቲያን ጥሪዋን እንደምታቀርብ ውሳኔው ዘግቧል።

በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ በኮሎምበስ ኦሃዮ ከጥቅምት 22-24/2010 (November 1-3/2017 E.C) ባካሄደው 46ኛው መደበኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በአትላንታ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ ጥረት በማድረግ ፋንታ ችግሩ ተባብሶ በምዕመናን መካከል መከፋፈል ተፈጥሮ በተለይም ቀኖና ቤተክርስቲያንን እና የቤተክርስቲያኑን ህገ ደንብ ከጣሱት ህገ ወጥ የቦርድ አባላት ጋር ህብረት በመፍጠር በፈጸሙት ኢቀኖናዊ ምግባር ምክንያት ሶስት ካህናት ማለትም

1ኛ. አባ ኃ/ጊዮርጊስ ተሾመ
2ኛ. ቄስ አብርሃም ቦጋለ
3ኛ. ቄስ የዓለምእሸት አብርሃ ክህነታቸው እንዲያዝ መደረጉ ታውቋል።

በዚህም መሠረት እነዚህም ካህናት ከዲሲምበር 3 2017 ጀምሮ በማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን ማገልግል እንደማይችሉ ቷውቋል። ይህንንም ውሳኔ የሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ተግባራዊ እንዲያደረጉ የቅዱስ ሲኖዶሱ ጽሕፈት ቤት አዟል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ይህን ውሳኔ ለመወሰድ ያሰገደደው እነኚህ ካህናት

፩ኛ፦ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በማቃለል በዓለማዊ አሠራር፤ የአድማ አጋሮቻቸው ከሆኑት የተወሰኑ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ጋር በመሆን ሊቀ ጳጳሱን በሌላቸው ሥልጣን መክሰሳቸው ፤

፪ኛ፦ መንፈሳዊውን ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስን እንጂ የአስተዳደር ቦርድን አይመለከትም በማለት ስለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያናቸው በተቆረቆሩ ከፊል የቦርድ አባላት አማካኝነት ጉዳዩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን አጥንቶ የሰጠውን መመሪያ ባለመቀበላቸው፤

፫ኛ፦ ሊቀ ጳጳሱን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንን ቤተ ክርስቲያን አንዳይገቡ በፖሊስ ታግደው በውጭ ቆመው ሳለ ቅዳሴ በመቀደሳቸው፤

፬ኛ፦ ከዚህም በተጨማሪ በተለይም በቅርቡ የመጣውና በጊዜያዊነት ተቀጥሮ የሚያገለግለው ቄስ ዓለምእሸት አብርሃ የተባለው ግለሰብ ባልኖረበትና በሌለበት በወሬ ብቻ ተደረገ በተባለ ጉዳይ ላይ ለአድማ ሲል ፈርሞ ከመገኘቱም በላይ ያለ ችሎታውና የሞራልም ይሁን የእውቀት ብቃት ሳይኖረው ከዲቁና እስከ ማዕረገ ጵጵስና ከሰማንያ ዓመት በላይ ቤተክርስቲያንን በትጋት ያገለገሉትን ይህችንም ካቴድራል ለዚህ ታላቅ ደረጃ ያደረሷትን የቤተክርስቲያናችንን ባለውለታ የሆኑትን ታላቁን አባት ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን፣ ሌሎች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን እና የቤተ ክርስቲያን ታላላቅ አባቶችን ስም እየጠራ በአውደ ምህረቱ ላይ በድፍረት በመዝለፉና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር በመጋፋቱ፤

፭ኛ፦ በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት በመሄድ ጥፋት እያደረሱ ያሉትን፣ ቀኖና ሐዋርያትን ተከትለው የማይሰሩትን፤ ሥልጣነ ሐዋርያትን ያቃለሉ፣ለማስተማር ፈቃድ የሌላቸውን ሰዎች በመጋበዝና በማስጋበዝ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን ያስነቀፉ፣ የክህነታቸውን አደራ ያልተወጡ፤ ቅዱስ ሲኖዶስንና አባቶችን የሚዘልፉና የሚያዘልፉ፤ ሁከት ፈጣሪዎች፣ ተመክረው የማይሰሙ፣ ስነ ምግባር የጎደላቸው እና ምዕመናንን ግራ የሚያጋቡ በመሆናቸው፤ እስከ አሁን ተመክረውም በመመለስ ፈንታ በጥፋታቸው ሰለቀጠሉብት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በማበላሸታቸውና ህገ ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ለምዕመናኑ መከፋፈል ትልቅ ምክንያት ሆነው በመገኘታቸው ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኑን ሕግና ቀኖና ለማሰከበር ባለበት ኃላፊነት በተለይም የምእመናን መለያየት ክፉኛ ስላሳስበው የወሰደው መንፈሳዊ እርምጃ መሆኑ ታውቆ አባ ኃ/ጊዮርጊስ ተሾመ፣ ቄስ አብርሃም ቦጋለ እና ቁስ አለምእሸት አብርሃ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አገልግሎታቸው እውቅና የሌለው በመሆኑ ተቀባይነት ስለሌለው ምዕመናን ይህንኑ በመረዳት ማንኛውንም ክህነታዊ አገልግሎት ከነዚህ ግለሰቦች ባለመቀበል ለቀኖና ቤተክርስቲያን ዘብ እንዲቆም ቤተክርስቲያን ጥሪዋን እንደምታቀርብ ውሳኔው ዘግቧል።

በነዚህ ካህናት አግልግሎት ያገኙ የነበሩ ምዕመናን ቅዱስ ሲኖዶስ ምዕመናኑ አገልግሎት እንዳያገኙ የሚል አቋም ስለሌለው ምዕምናን ከሀገረ ስበክቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር በመመካከር አገልግሎት እንዲያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ ማድረግ እንደሚችል ገልጿል። በአንድ ሀገረ ስብከት ያሉ ካህናት የሀገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ሳያውቅና ሳይፈቅድ አገልግሎት መስጠት ቀኖናውን እንደሚፃረር ለማወቅ ተችሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ውዝግቡ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ወደ ሦስት ጊዜ ከሊቀ ጳጳስ እስከ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሆኑትን የአባቶች ልዑካን በመላክ ጥረት ቢደርግም የወያኔን የመለያየት አጀንዳ ለማስፋፋት ምክንያት የሆኑት አስሩ የቦርድ አባላት ውዝግቡ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ባለመፈለጋቸው ምክንያት ቤተክርስቲያኗ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የፈረቃ አገልግሎት ለመስጠት ተገዳለች።

እነዚህ የቦርድ አባላት የወያኔ ቅልብ ሰባክያንን ከአዲስ አበባ ድረስ ቲኬት እየቆረጡና ውሎ አበል እየከፈሉ በማስመጣት በስደት አገር በሽምግልና እድሜ ሻንጣ እየጎተቱ አህጉር አቆራርጠው በመላው ዓለም የተበተነውን ምእመን የሰበሰቡትን አባቶች ያሰድባሉ። ይህ ሁሉ ፍትጊያ ይህችን ለሰደተኛው ሕዝብ መመኪያ የሆነችውን ታላቅ ካቴድራል ከሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ አውጥቶ በአባይ ጸሃይ በሚዘወረው ለአዲስ አበባው ሲኖዶስ ለማስረከብ እንደሆነ ባለፈው አንድ አመት ብቻ የተፈጸመው እኩይ ምግባር ምስክር መሆኑ ታውቆ ሕጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ በመቀበል ይህን ኢቀኖናዊና ሕገ ወጥ ተግባር በተለያይ አቅጣጫ ከሚታገሉት ምዕመናን ጋር መቆም እንዳለብን በማሳሰብ መልዕክቴን በዚሁ አጋጣሚ አስተላልፋለሁ።

ተክለ ጊዮርጊስ ከአትላንታ

አባ ኃ/ጊዮርጊስ ተሾመ
ቄስ አብርሃም ቦጋለ
ቄስ የዓለምእሸት አብርሃ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *