“Our true nationality is mankind.”H.G.

እነለማ መገርሳ በፍፁም የማይሸነፉበት ምክንያት

መኮንን ሀብተጊዮርጊስ ብሩ (ዶ/ር)

ከጥቂት ዓመታት በፊት ቅንጅት መንፈስ ነዉ ሲባል ይሰማ ነበር። እዉነት ነበር ፣ እዉነትም ነዉ። አብሮነት ከፈጣሪዉ ለሰዉ ልጅ የተ ሰዉ የመሆን መንፈስ ነዉ። ሴይጣ ጥለቀቱ ዉስጥ እስኪገባ ድረስ ያን የፍቅር መንፈስ አሳንሶና አኮስሶ ደቀ መዛሙርቱንም ሲቻለዉ በየ እስር ቤቱ አጉሮ ሳይቻለዉ ከተፈጠሩባት ምድር አሳዶና አስወጥቶ ቤተ መቅደሱንም ቤተመርገም ሊያደርገዉ ቢፍጨረጨርም፣ መቼም ሊሸነፍ የማይችለዉ የአብሮነት መንፈስ በቁጣ መቅደሱን ሊረከብ ተዘጋጅቷል። እነ ለማ፡፣ አዲሱና፣ገዱ ወደ ደማስቆስም ይሁን ባሕር ዳርሲጓዙ ያ ሊሸነፍ የማይችል የአብሮነት መንፈስ የተገናኛቸዉ ይመስላል። ፈጣሪ ያኔ አሳደህኛልና ሲል ጳዉሎስን ከማዉገዝ ይልቅ ደቀ መዝሙሩ አድርጎ መሾሙን እዚህ ጋ አንድ ይሉሃል።

ለብዙ ሺህ ዓመታት ብዙዎች በየዋሁ የኢትዮጲያ ሕዝብ ላይ እየነገሱ ገራገርነቱንና ፍቅሩን ከዉስጡ መጠዉ ሊጨርሱ ቢመኙና ቢጥሩ ሊሆንላቸዉ አልቻለም። አይችልምም!! ‘በዉኑ ኢትዮጲያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጉርጉርነቱን ይለዉጥ ዘንድ ይችላልን’ ሲል ኤርምያስ በትንቢቱ መጠየቁን እዚህ ጋ ሁለት ይሉሃል (ትንቢ ኤርምያስ 13:23) ።

ማሰር፣ መግደል፣ ማሳደድ፣ ሴት እህቶቻችንን ለአርብ ሀገራት መሸጥ መለኮታዊ አይደለም። ከአዉዜንና ከበደኖ፣ እስከ ባሕር ዳርና ጨለንቆ ድረስ የፈሰሰዉ የብዙሃን ወንድምና እህቶቻችን ደም አብርሃም ልጁን ይሳቅ ለመስዋህት ያቀርብ ዘንድ በቅዱስ መንፈስ ታዞ የተደረገን ያህል ህወኣት መልሶ መላልሶ እስኪያቅለሸ ልሸን ብቻ ሳይሆን እስኪያ ቅረን ድረስ ለሃያሰባት ዓመታ ት ሊግተን ቢሞክርም በቃን ብለናል። በየዕለቱ በግፍ ለሚገድላቸዉና በየ ጨለማ ቤቱ ለሚወረዉራቸዉ ወገኖቻችን ዉሃ የማይቋጥርና የማሞ ቂሎን መሰል ተረት ተረት ምክንያት አየሰጠን ቢሰነባብትም አሁን ሁሉም ነገር ለአብዛኞቻችን ገብቶናል። በጀርባ በር እየገባና ጭንብል እያጠለቀ ኦሮሞን መስሎ ኦሮሞን ሲገድል፣ አማራን መስሎ አማራን ሲገድል የማይገባዉን ያህል ዘመን ቢሰነባብትም፣ አሁን ሁሉም ነገር ገዐድ ሆኖ መደምደሚያዉ ተቃርቧል። ዮሐንስ በወንጌሉ ‘እዉነት እዉነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው’ ማለቱን እዚህ ጋ ሶስት ይሉሃል (የዮሐንስ ወንጌል 10:1) ።

አዎን!  ቅንጅትና አብሮነት መለኮታዊ መልህክት ያለዉ መንፈስ ነዉ። የሰዉ ልጅ ሲፋቀር፣ የሰዉ ልጅ ሰላም ሲሆን፣ የሰዉ ልጅ ሲግባባ፣ የሰዉ ልጅ ሲተባበር የሚወድ መንፈስ መለኮታዊ መንፈስ ነዉ። ይህ መንፈስ ደግሞ እንግዳ ሲመጣበት እግር አጥቦ ቤት ያፈራዉን  አብልቶና መኝታዉን ለቆ ለሚያሳድረዉ ንፁሕ እና ቀና ሕዝብ የተሰጠ መለኮታዊ መንፈስ ነዉ። ይህን የአብሮነት መንፈስ ከኦሮሞም ከአማራም ከሌሎችም ኢትዮጲያዉያን መነጠል የሚችል አይኖርም። ‘እግዚአብሔር ያጣመረዉን እንግዲህ ሰዉ አይለየውም’ ሲል ማርቆስ በወንጌሉ መናገሩን ኢዚህ ጋ አራት ይሉሃል (የማርቆስ ወንጌል 10 : 9)።

ዛሬ እነለማ መገርሳ እያስተጋቡ ያሉት በወለጋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በመቱ፣ በአፋር አና በሌሎቹም የሀገራችን ግዛቶች እያስተጋባ ያለዉን የእያሪኮን ጬህት በመሆኑ የህወኣትን ሳጥናኤላዊ ደንቃራ መገርሰሱ ሳይታለም የተፈታ እዉነት ነዉ። አዎን! ህወኣት ለማ መገርሳንም ይሁን ገዱ አስራትን ማሰር ወይም መግደል ይቻላት ይሆናል። ለማና ገዱም ቢሆን በዉስጣቸዉ እየቃተተ ያለዉን መለኮታዊ የአብሮነት መንፈስ እንደ ይሁዳ በምድራዊ ከንቱ መክሊት ሊለዉጡ ይከጅሉ ይሆናል፤ ምንም ይሁን ምን ግን አሁን በብዙ ሚሊዮን ኦሮሞዎች፣ በበርካታ ሚሊዮን አማሮች እና ሌሎች ኢትዮጲያዊያን ዉስጥ እየተንቦለቦለ ያለውን ቅዱስ የአብሮነት እና የፍቅር መንፈስ ግን ማንም ሊያጠፋዉ  አይቻለውም። ቅድስቲቱ ሀገር እጇን ወደ አብሮነት አና የፍቅር አምላክ ዘርግታ መቆየቷ ተበታትኖ ለመጥፋት ወይም በምድሯ የተፈጠሩትን ፍጡራን ለስደትና እርዛት ይሰጡ ዘንድ ለመጠየቅ አይደለም።  ማቴዎስ በወንጌሉ ‘ለምኑ ይሰጣችሁማል፣ ፈልጉ ታገኙማላችሁ’ ሲል የፃፈዉን ቃል ኪዳን እዚህ ጋ አምስት ይሉሃል ።ማቴዎስ 7:7) ።

የስቃይና የበደል ፅዋ በህወኣት ዘመን በትዉልድ ሀገራችን ሞልቶ ፈሷል።  እነ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ፣ ኦልባና ሌልሳ፣ በቀለ ነገሪ፣ አንዱዓለም አራጌ እና ሌሎችም ብዙ ሺዎች በቅሊንጦ፣ በዝዋይ፣ በማዕከላዊና በሌሎች በሚታወቁና በማይታወቁ የስቃይ ጨለማ ቤቶች አካላቸዉ ብቻ ሳይሆን መንፈሳቸዉንም ለማርከስ ብዙ ብዙ ኢሰብአዊ በደል ተፈፅሞባቸዋል። ብዙዎቹ በተፈጠሩባት ምድር መፈጠራቸዉን እስኪጠሉ ድረስ ተገፍተዋል። ብዙ ሺዎችም በአጋዚ ጥይት ተቆልተዋል። ኩበት ጠፍጥፋ ያሳደገች የኦሮሞ እናት፣ እንደ ወንድ ልጅ አርሳ ያሳደገች  የአማራ እናት፣ ልጆቿ ስትል የከብት ጭራ ስትከተል የኖረች የጋምቤላዉ እናት የዘመናት ጩኽት ፅዋዉን ሞልቶታል። ከእንግዲህ በኋላ የሚደረግ ምንም ዓይነት ስብሰባና መሯሯጥ  ይህን የትዉልድ ሰቆቃና እንባ ሊያጠራዉ አይችልም። ይልቁንም አዲስ አስተሳሰብ እና ብሔል ያስፈልገናል። ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለዉ በህወኣት መንገድ አይደለም። የህወኣት መንገድ የእርኩሰት መንገድ ነዉ። የህወኣት መንገድ ወንድምና እህትን የመጥላት  መንገድ ነዉ። የህወኣት መንገድ በሞት ዉስጥ መሆን ነዉ። ሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመሪያ መልህክቱ ላይ ‘ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል’  ያለዉን እዚህ ጋ ስድስት ይሉሃል ( 1 ዮሐንስ 3: 15).

ደጃች ዉቤ ጨካኝ እንደነበሩና በማሰር ብቻ ሳይወሰኑ እንደ አረቦቹም እጅ መቁረጥ ይወዱ እንደነበር ክቡር ተክለ ፃደቅ መኩርያ ፅፈዋል። ታዲያ ጊዜ ተለዉጦ እሳቸውም ለእስር በቅተዉ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብት መልሱ ሲባሉ እምቢ በማለታቸዉ እጃቸዉ ደም እስኪቋጥ ር ድረስ ከተገረፉ በኋላ ሲያንጎራጉሩ እንዲህ ብለዉ አንጎራጎሩ ይባላል፣

መከራን በሰዉ ላይ እንደዚያ ሳቀለዉ
እንደዚህ ይከብዳል ለተሸከመው ሰው።

(ዓፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጲያ አንድነት። ገፅ 141)

ታዲያ ዛሬ የእነ በቀለ ገርባና እስክንድር ነጋን ስቃይ እነ ለማና ገዱ የተረዱ ቢመስል ተዓምር አያሰኝም፤ ይልቁንም ግንቡን ሊያፈርሰዉ ጥቂት ከቀረው የእያሪኮ የድል ጩህት ጋር አብሮ ለፍትህ መጮሁ ብቻ ሳይሆን ካስፈለገ ለመስዋህትነትም ጭምር መዘጋጀቱ ይበጃል። በኢትዮጲያዊን ልብ ዉስጥ ህወኣት ሞቷል። አሁን እነ ለማ መገርሳ ማውቅ ያለባቸው የህወኣትን የዘረኝነት እርኩስ መንፈስ ከእሬሳዉ ጋር ለመቅበር መጣር ነዉ።  በዚህ መንፈ ስ እስከተመሩ ድረስ በፍፁም አይሸነፉም።

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር። አሜን

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ
0Shares
0