ኸርማን ኮሆን ተጸጽቻለሁ ይላሉ። ኢህአዴግን ገዢ እንዲሆን ስልጣን ሲያከናንቡት በዚህ ደረጃ አምባ ገነን ይሆናል የሚል ግምት እንዳልነበራቸው በመግለጽ ነው መጸጸታቸውን ዛሬ ላይ ሆነው ከ26 ዓመት በሁዋላ የተናገሩት። ስልታኑንን፣ ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውን በሙሉ መቆጣጠራቸው ይፋ የተናገሩት ኮሆን አሜሪካ የበኩሏን ልትወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቪኦኤ ይህንን ዘግቧል።

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትርና አምባሣደርም ሆነው ያገለገሉት ኸርማን ኮኸን ባለፈው ሣምንት ውስጥ በትዊተር ባወጡት ሃሣብ ለሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ – ሕወሐት መሪዎች ምክር አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።

አምባሣደር ኮኸን በዚሁ ትዊታቸው ያሠፈሯቸው ቃላት ሲተረጎሙ

“ሕግና ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ከመፈራረሣቸው በፊት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሁሉንም ወገኖች የሚያሣትፍ ጉባዔ አዘጋጅቶ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲዘረጋ ይሸመግል ዘንድ ለመጠየቅ የሕወሐት አመራር በጥብቅ ሊያስብበት ይገባል” ይላሉ።

ሚስተር ኮኸን የደርግ መንግሥት በመሃል ሃገርና በኤርትራም ውስጥ ገብቶባቸው የነበሩ ግዙፍ ጦርነቶች እንዲያበቁ በአንድ በኩል በኢሕአዴግና በደርግ፣ በሌላ ግንባር ደግሞ በደርግና በሕዝባዊ ግንባር ሐርነት ኤርትራ መካከል የነበሩ ሽምግልናዎችና ድርድሮችን የመሩ ሰው ናቸው።

አምባሳደር ኮኸን በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር ከ1989 ዓ.ም. እስከ 1993 ዓ.ም. በነበሩት የዩናይትድ ስቴትስ 41ኛው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አስተዳደር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ከዚያ ቀደም ባሉ ዓመታትም በጋምቢያና በሴኔጎል የአሜሪካ አምባሣደር ነበሩ። ዛሬም በተለያዩ ዓለምአቀፍ ሥራዎች ላይ ተሠማርተው ይገኛሉ።

ከሃያ ስድስት ዓመታት በኋላ ሚስተር ኮኸን ‘ይድረስ ለሕወሓት መሪዎች’ ብለው ትዊት ሲያደርጉ ምን ታይቷቸው ይሆን? ደግሞስ “ሕግና ሥርዓት ጨርሶ ከመፈራረሣቸው በፊት…” ሲሉ ጣልቃ ገብነትን መማፀናቸው ምን ማለታቸው ይሆን?

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *