የአባዱላ አጣብቂኝ
“የለውጥ አራማጆች” ተነስተዋል በሚባልበት እና የእርሱም የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ከዚሁ የለውጥ ማዕበል ጋር የተያያዘ ነው በሚል ሲዘገብለት የነበረው “ጃርሳው” ከኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ በኋላ ጀርባውን ለኦህዴድ መስጠቱ ሁሉንም ነገር በዜሮ የሚባዛው ሆኗል።
የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር አቶ ሙሉጌታ ወርቁ፣ የጎንደር ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባባል እና ስለ ህዝባዊ አመፁ ማስረዳት ይችላሉ የተባሉ ባለስልጣናት እና የፖሊስ አዛዦች በእነ ንግስት ይርጋ ተፈራ ክስ መዝገብ ስር ለተከሰሱት 6 ግለሰቦች የመከላከያ ምስክር ሆነው (ታህሳስ 12፤ 2010) እንዲቀርቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አዟል።
የኦሮሚያና የአማራ ቴሌቭዥንን የሚገደብ አዲስ እቅድ ተዘጋጀ
የአማራና የኦሮሚያ ክልል የቴሌቭዥን ስርጭቶች በሀገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት ሙሉ ቁጥጥርና የበላይነት ያለውን ህወሐት የሚነቅፉና በማዕከላዊነት የሚተላለፈውን ፕሮፓጋንዳ መና ያስቀሩ ሆነዋል። ይህን የክልል መገናኛ ብዙሀን አንፃራዊ ነፃነት መልሶ ለመገደብ ገዥው ፓርቲ አዲስ እቅድ መንደፉ እየተሰማ ነው ……
የአቶ አባዱላ መልቀቂያ በኢሕአዴግ ተቀባይነት አገኘ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ከአፈ ጉባዔነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በኢሕአዴግ ተቀባይነት ማግኘቱ ታወቀ፡፡ በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለኢሕአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ለኦሕዴድ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የጥያቄያቸውን ምላሽ እስካለፈው ሳምንት ድረስ ሲጠባበቁ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት ግን የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተቀበለው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል,,,,,,,
የብአዴን አመራር አባላት የአማራ ሕዝብ ሆድ ብሶታል አሉ
የአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎች ባካሄዱት ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ በየወረዳዎቻቸው የሚገኙ የሕወሃት አመራሮች ቁልፍ ቦታዎችን እንደተቆጣጠሩ ይፋ አድርገዋል። የሕወሃት የበላይነት በየተቋማቱ ስለመኖሩ የተስማሙት የአዲስ አበባ ወረዳ ካድሬዎች በተለይ የመከላከያ ሰራዊት አመራር በትግራይ ተወላጆች መታጨቁን ነው የገለጹት። ይህ ብቻ አይደለም በየትኞቹም ተቋማት ያሉ ቁልፍ ቦታዎች በነሱ የተያዙ ናቸውም ብለዋል …….
ፈውስን ፍለጋ ከህንድ እስከ ታይላንድ
በአንድ ሙያዊ ሥልጠና ላይ ለመካፈል ከአንድ ጓደኛው ጋር ወደ ህንድ ያቀናው ከወራት በፊት ነበር፡፡ እንግዳ በሆኑባት ኒውዴል ከተማ እንደ ደረሱ ተቀብሎ የሚያስተናግዳቸውና ወደተያዘላቸው ሆቴል የሚያደርሳቸው ሰው መመደቡ የተነገራቸው ከአዲስ አበባ ሳይነሱ በኢሜይል መልዕክት ነበር፡፡ ሲደርሱ ግን ያጋጠማቸው ከዚህ የተለየ ነበር፡፡
እንደደረሱ ‹‹ኢትዮጵያዊ ናችሁ?›› ሞቅ ባለ እንኳን ደህና መጣችሁ ብላ ሰላምታ የተቀበለቻቸውን ወጣት ተከትለው ወደ አንደኛው የትኬት ወኪል ቢሮ አመሩ፡፡ የሁለቱንም ፓስፖርት ተቀብላም ፎቶ ኮፒ አደረገች፡፡ ሁኔታው ያላማረው ሰለሞን ስዩም የምታደርገውን ነገር በዓይነ ቁራኛ ይከታተላት እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ፓስፖርታቸውን መልሳ አንድ መኪና አስመጣችና ሂዱ ብላ ከመኪናው ሹፌር ጋር አገናኘቻቸው፡፡