“ሃዋሪያ” ሃብታሙ፣ ይዲዲያ “መምህር” ግርማ ወንድሙን በአካል ተገናኝተው እንዲጸልዩ፣ አስፈልጊም ከሆነ እሳቸውን መሰል በሙሉ ተሰባስበው እሱ ብቻውን መጥቶ ትክክለኛው መንፈስ እንዲገለጥና ትውልድ እንዲድን ጥያቄ አቀረበ። ብዙም ጭፈራና ዝላይ የማይወዱ አገልጋይ ከሆኑት መካከል አንዱ ” ጉዳዩ የመንፈስ ጉዳይ ነው፤ በጸሎት ማሸነፍ እንጂ የአደባባይ ፉከራ ዋጋ የለውም፤ መንፈስ የሚሸነፈው በመንፈሳዊ ጦርነት እኒ በአደባባይ ግብግብና በቲፎዞ ፊት በሚደረገ ግጥሚያ አይደልም” ብለዋል።

በ “አስማት ጥንቆላ፣ መስተፋቅር፣ ሙዋርት ፣በመናፍስት አሰራርና በድግምት ሕዝብን ለምታተራምሱና ለእርስዎ ጭምር” ሲል ጥሪውን ያቀረበው ሃብታሙ፣ መምህር ግርማ ወይም እሳቸውን መሰሎች በሙሉ ቅድሚያ እንዲጸልዩለት ይጠይቃል። “ሕዝብ በሚይይበት እኔ ብቻዬን እመጣለሁ” በማለት እጅግ በርካታ ተከታይ ያላቸውን መምህር ግርማ ጋብዟቸዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በቪዲዮ ብቻ በመለፍለፍ እንደማያቆም ያስታወቀው አገልጋይ ” በጨሌ መደብደብ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አይደልም። አጋንንት የሚወጣው በአንድ ኢየሱስ ስም ብቻ ነው” ይልና፣ እሳቸውና መሰሎቻቸው በቅድሚያ ሕዝብ እያየ ከጸለዩለት በሁዋላ ” እኔ እጸልይሎታለሁ” ሲል ከዛ በሁዋላ ሁሉም እንደሚገለጥ አመላክቷል።

habtamu (2)

ሕዝብ በተሰበሰበበት፣ ስታዲዮም፣ ገላጣ ሜዳ ሊሆን ይችላል በማለት “እንገናኝ” ያለው የወንጌል አገልጋይ ” መምህር” ግርማ ፓስተሮችና ፕሮቴስታኖች በሙሉ በአጋንንት ሃይል የተሞሉ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ይናገራሉ። የሳቸው መስመር ትክክል እንደሆነ አድርገውም ይመልከታሉ። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየዞሩ ከመናፍስት ጋር ቃለ ምልልስ በሚመስል ደረጃ ፈውስ ሲሰጡ የሚያሳዩ በርካታ ቪዲዮ አላቸው። ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተከታዮችም አሉዋቸው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አገልጋዩ የግል ስልኩን 0911384779 የላከላቸው ሲሆን መምህር ግርማ ወንድሙ ነኝ ብለው መልዕክት ከላኩለት እንደሚደውልላቸውም አስታውቋል። ቪዲዮውን ከታች ይመልከቱ

ይህንን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው አንድ ረጋ ያሉ ወንጌላዊ ” የሁለት ታዋቂ ቦክሰኞች የፍልሚያ ቀጠሮ ይመስላል። ስሜትና አገልግሎት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አምላካቸውን ለሚወዱ ሁሉም ጉዳይ የሚመረመረው በመጽሃፍ ቅዱስ ብቻ ነው። እናም የመንፈስና የመናፍስት አሰራር እንዴት እንደሚለይ ስለተጻፈ፣ በተጻፈው መሰረት መጓዝ ነው። መንፈስ በመንፈስ እንጂ በስሜትና በግብገብ አይሆንም። አምላካችን እንዳለው እሱ መንፈስ ስለሆነ የሚመለከውና የሚሰገድለትም በመንፈስ ብቻ ነው። ሌላው ሁሉ ስሜትና የተግበሰበሰ ነገር አምላካዊ አይደለም። በጸሎት ሃይል ይወድቃል። ብዙዎች አገር አንጫጭተው ነበር። ወድቀዋል። አሁንም መድሃኒቱ ግብግብ ሳይሆን ጸሎት ብቻ ነው….”

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

 

ይድረስ ለመምህር ግርማ

Публикувахте от Christian ዜማ Tube в Понеделник, 23 октомври 2017 г.

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *