የእሥር ቤቱ ጠባቂ ከእንቅልፉ ሲነቃ በሮቹ ሁሉ ተከፍተው አየ፥እስረኞቹ ያመለጡ ስለመሰለውም ራሱን ለማጥፋት ሰይፉን መዘዘ።በዚህን ጊዜ ቅዱስ ጳው ሎስ ድምፁን ከፍ አድርጐ “በሰውነትህ ልዩ ክፉ አትሥራ፥በገዛ እጅህ ታርደህ አትሙት፥ማንም ያመለጠ እስረኛ የለም፥ሁላችንም ከዚህ ነን፤”አለው።የገረፈውን ያሰቃየውን እና ያሠረውን ወታደር ከሞት አዳነው።“ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉ አትመልሱ፥በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ፤”ብሎ በቃል ያስተማ ረውን በተግባር አሳየ

ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ፡-የልድያን ቤተሰቦች ካጠመቀ በኋላ ወደ ጸሎት ስፍራ ሲጓዙ፥ጋኔን የሚያዘፍናት (የሚያንዘፈዝፋት) አንዲት ብላቴና ተከ ተለቻቸው።ይህች ብላቴና እየጠነቆለች ለጌቶቿ ብዙ ገንዘብ ታስገባ ነበር።ከጀር ባቸው ሆና፡-“እሊህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር ሰዎች ናቸው፥ድኅነት የምታገኙ በትን ነገር ያስተምሯችኋል፤”እያለች ትጮኽ ነበር።አያሌ ቀናትም በመጮዃ ቅዱስ ጳውሎስን አሳዘነችው፥አተጋችው።ወደ ኋላም ዘወር ብሎ መንፈሱን፡- “ከርሷ ትወጣ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ ፤”አለው፥ያን ጊዜም ተለይቷት ወጥቶ ሄደ።በተሰጠው ጸጋና ሥልጣን ሴቲቱን ከአጋንንት ቍራኝነት አላቀ ቃት።

26195874_1923959344299722_3154026326431295396_n.jpg

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡-በሠራው በጎ ምግባር አልተመሰገነበትም።ጌቶቿ የተመለከቱት የገረዲቱን መፈወስ ሳይሆን የትርፋቸውን መቋረጥ ነው።የተደረገው ተአምራትም አበሳጫቸው እንጂ አላስደሰታቸውም።በመሆኑም ቅዱስ ጳውሎስን እና ሲላስን፡-በአደባባይ እየጐተቱ ወደ ሹማምንቱ ወሰዱአ ቸው።የሐሰት ክስ ፈብርከው፡-“እሊህ ሰዎች አገራችንን እያሸበሩብን ነው፥የሮም ሰዎች ስንሆን ልንሠራው የማይገባንን ሥርዓት እያስተማሩን ነው፤”እያሉ ከሰሱ አቸው።ሕዝቡና መኳንንቱም የክሱን ይዘት ሳይመረምሩ የቅዱሳኑን ልብስ ገፍ ፈው አብዝተው በበትር ደበደቡአቸው።መላልሰው በጭካኔ ከደበደቡአቸው በኋላ አሥረው ለእሥር ቤት ጠባቂው አሳልፈው ሰጡአቸው።የእሥር ቤት ጠባ ቂውም አጽንቶ እንዲጠብቃቸው ስላስጠነቀቁት ሰው በላ ወንበዴዎች ከታሠሩ በት ከምድር ቤቱ፥እግሮቻቸውን በእግር ብረት አሥሮ፥እንዳይንቀሳቀሱም ከግ ንድ ጋር ጠርቆ አሠራቸው።

መንፈቀ ሌሊት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ እንደታሠሩ፥በደም እንደተ ነከሩ የተለመደውን ጸሎታቸውን አደረሱ፥እስከ ቍስላቸው በዝማሬ እግዚአብሔ ርን አመሰገኑ።ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡-“ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያ ደርግ፥ትዕግሥትም ፈተናን፥ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራ ችን ደግሞ እንመካለን፤”ያለው እንዲህ በተግባር አሳይቶ ነው።ሮሜ፡፭፥፫።እርሱ እንደ እኛ የቃል ሳይሆን የተግባር መምህር ነው።ይህ ሁሉ ሲሆን እሥረኞቹ ሁሉ በመገረም ያደምጧቸው ነበር።ያን ጊዜ በጸሎታቸውና በመዝሙራቸው ኃይል የወኅኒ ቤቱ መሠረት እስኪናውጥ ድረስ ምድር ተንቀጠቀጠች።ወዲያውም የወ ኅኒ ቤቱ በር ወለል ብሎ ተከፈተ፤ሰንሰለቶቹ ከእጆቻቸው፥የእግር ብረቶቹ ከእግ ሮቻቸው እየወለቁ ወደቁ።

የእሥር ቤቱ ጠባቂ ከእንቅልፉ ሲነቃ በሮቹ ሁሉ ተከፍተው አየ፥እስረኞቹ ያመለጡ ስለመሰለውም ራሱን ለማጥፋት ሰይፉን መዘዘ።በዚህን ጊዜ ቅዱስ ጳው ሎስ ድምፁን ከፍ አድርጐ “በሰውነትህ ልዩ ክፉ አትሥራ፥በገዛ እጅህ ታርደህ አትሙት፥ማንም ያመለጠ እስረኛ የለም፥ሁላችንም ከዚህ ነን፤”አለው።የገረፈውን ያሰቃየውን እና ያሠረውን ወታደር ከሞት አዳነው።“ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉ አትመልሱ፥በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ፤”ብሎ በቃል ያስተማ ረውን በተግባር አሳየ።ሮሜ፡፲፪፥፲፯።የወኅኒ ቤት ጠባቂው፡-መብራት አብርቶ እየ ተንቀጠቀጠ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ ከእግራቸው በታች ወድቆ ሰገደላቸው።ወደ ውጭ አውጥቶም “ጌቶቼ እድን ዘንድ ምን ላድርግ፤” አላቸው።እነርሱ የጸጋ ጌቶች፥ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የባህርይ ጌታ ነውና።እርሱ የጌቶች ጌታ የተባለው ለዚህ ነው።ራእ፡፲፱፥፲፮።

ቅዱስ ጳውሎስ እና ሲላስ ጠባቂውን፡-“በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አን ተም ቤተሰቦችህም ትድናላችሁ፤”አሉት።ወንጌልን፡-ለእርሱም ለቤተሰቦቹም አስ ተማሩአቸው።ያን ጊዜ በሌሊት ወስዶ ቍስላቸውን ጠረገላቸው፥ደማችውንም አጠበላቸው።እርሱና ቤተሰቡም አምነው ተጠመቁ።ሰፊ ማዕድም አቀረበላ ቸው፥በሆነው ነገር እርሱም ቤተሰቦቹም እጅግ ተደሰቱ።በማግስቱም ጳውሎ ስን እና ሲላስን ፍቱአቸው የሚል መልእክት መጣ።(የሐዋ፡፲፮፥፲፮-፵)። =በዘመናችንም ንጹሐኑ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ የታሠሩበት ሰንሰለቶችና የእግር ብረቶች አሉ።እነ ቅዱስ ጳውሎስ “አሸባሪዎች” ተብለው እንደተገረፉና እን ደታሠሩ፥ዛሬም ብዙ ንጹሐን “አሸባሪዎች” የሚል ታፔላ እየተለጠፈባቸው ተገር ፈዋል፥ታሥረዋል።ወንድና ሴት ሳይለይ የእጅ የእግር ጥፍሮቻቸው በጉጠት እየ ተነቀለ ተሰቃይተዋል።ሲሰሙት እንኳን እንዴት ይዘገንናል።ለመሆኑ ከእስር የተ ረፈ ማነው? እንደምንሰማውና እንደምናየው እየታሠሩ እየተሰቃዩ ያሉት ፖለቲ ከኞቹ ብቻ አይደሉም።

ከገበሬ እስከ ምሁር፥ከዲያቆን እስከ መነኵሴ ወዘተ . . . መብቱን ነጻነቱን የጠየቀ ሁሉ በየእስር ቤቱ እየታጐረ ነው።እነዚህም እየደረሰባ ቸው ያለውን ስቃይ በችሎት ፊት ሱራያቸውን አውልቀው እስከ ማሳየት ደርሰ ዋል።ወንድ ልጅ ካልባሰበት በስተቀር ቀበቶውን ፈትቶ፥ሱሪውን አውልቆ ኀፍረተ ሥጋውን በአደባባይ አያሳይም።

በእኛ ዘመን በእኛ ኃጢአት፥በአሣሪዎችም ክፋት ዓለምን ንቀው፥ኃጢአትን ተጸይፈው በረሀ የወደቁ የዋልድባ መናንያንም ከሥቅየቱ አላመለጡም።እንደነ ቅዱስ ጳውሎስ “አሸባሪዎች”ተብለው ከጨለማ ቤት ተወርውረዋል፥በበትር ተደ ብድበዋል።ለመሆኑ ወንጀላቸው ምንድነው? “ገዳማችን የስኳር ፋብሪካ መሆን አይገባውም፤” ማለታቸው ወንጀል ነው? “የመናንያኑን ስፍራ ከተማ አታድርጉ ብን፥እኛ ወደዚህ የመጣነው እኮ የከተማውን ኃጢአት ሸሽተን ነው፤”ማለታ ቸው ወንጀል ነው? እንደ ያዕቆብ፡-“ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፤ይህ ስፍራ የእግ ዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፥ይህም የሰማይ ደጅ ነው።”ማለታ ቸው ወንጀል ነው?ዘፍ፡፳፰፥፲፯።እነዚህ አባቶች ሕጉን ተከትለው እስከ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፥እስለ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ሄደው ነበር።ነገር ግን ሰሚ አላገኙም።ቤተ ክህነቱም ቤተ መንግሥቱም አልሰማቸ ውም።

መንግሥት የተመለከተው እንደ ጠንቋይዋ ጌቶች የሚያግበሰብሰውን ትርፍ ብቻ ነው።ለዚህም ነው እነዚያ እነ ቅዱስ ጳውሎስን አስረው እንዳሰቃዩአቸው፥እነዚህ ደግሞ የዋልድባን መነኮሳት አስረው የሚያሰቃዩአቸው።ሰው አልታፈ ረም፥እግዚአብሔርም አልተፈራም፥ቤተ ክህነቱም በዝምታ ተውጦአል።ለመሆኑ መጮኽ የነበረበት ማነው? የቤተ ክህነት ሹም የተሆነው ቤተ ክርስቲያንን ለመ ጠበቅ፥ለቤተ ክርስቲያን ለመጮኽ እንደሆነ እንዴት ይረሳል? ካልሆነልን ሹመ ቱን ትተን፥መስቀሉን አስረክበን ወታደር መሆን ነው።የታሠሩትስ መከራውን ችለው፥ሥቃዩን ታግሠው ለሀገራቸውም ለቤተ ክርስቲያናቸውም መሥዋእትነት እየከፈሉ ነው።አንድ ቀን እግዚአብሔር የታሠሩበትን ሰንሰለት ይፈታላቸዋል፥ከእግር ብረት ያላቅቃቸዋል፥መዝጊያውን ይከፍትላቸዋል፥ያሠሩአቸውን እና ያሠቃዩ አቸውን ያንበረክክላቸዋል።የእኛ የለዘብተኞቹ ሰውንም እግዚአብሔርንም ማስ ደሰት ያቃተን መጨረሻችን ምን ይሆን? ለመሆኑ እውነቱን እውነት፥ሐሰቱን ሐሰት ማለት ፖለቲካ ይሆን?

kesis dejene shiferaw

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *