ለሕዝብ ድምጽ እጅግ ቅርብ የሆነውና በሚያቀርባቸው የጥበብ ፈጠራዎች ብስለት ክብር የተጎናጸፈው ቴዎድሮስ ካሳሁን -ቴዲ አፍሮ የሚያቀርበው የሙዚቃ ድግስ ከጸጥታ ችግር ነጻ እንደሆነ ክልሉ አስታወቀ። ክልሉ እንዳለው ‹‹የሙዚቃ ዝግጅቱን ሁሉም የሚፈልገው ስለሆነ የፀጥታ ችግር አይኖርም፤››

በባህር ዳር ዳሽን ቢራ ስም ሲቀየር ያዘጋጀውን ዳንኪራ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት ፍንዳታ ደርሷል። ለፍንዳታዎቹ በገሃድ ሃላፊነት የወሰደ ድርጅት ወይም አካል ባይኖርም በደፈናው የተቃውሞው አካል እንደነበር በተለያዩ ሚዲያዎች በወቅቱ ተመልክቷል። ክልሉ የቴዲን  ” ኢትዮጵያ የፍቅር ጉዞ” የሙዚቃ ድግስ በተመልከተ በባህር ዳር ስታዲዮም ሲካሄድ ከ30 እስከ 40 ሺህ ታዳሚ ይገኛል ተብሎ እንደሚገመት ሪፖርተር የቴዲ አፍሮ ማኔጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይን ጠቅሶ ተናግሯል።

ቴዲ አዲሱስን አልበሙንም ሆነ ቀደም ሲል ስራዎቹን ለአፍቃሪዎቹ ለማቅረብ ጥያቄ ቢያቀርብም የሚሌኒየም “ኮንቴነር አዳራሽ ” ባለቤቶችን ጨምሮ ስማቸውና ሃላፊነታቸው በውል የማይገለጽ ክፍሎች በተደጋጋሚ እንደከለከሉት ይታወሳል። አርቲስቱም ቢሆን ” እንዲህ ያላው ሰብአዊ መብትን የሚጋፋ ድርጊት አግባብ አይሆንም” በማለት ቅሬታውን መግለጹ ይታወሳል።

Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

በተለይም የአዲሱ አልበሙ አካል የሆነውን ማር አስከጧፍ ለማስመረቅ በሂልተን ሆቴል ከአድናቂዎቹን ጥሪ ካደረገላቸው ወገኖቹ ጋር ሊያደርገው ያሰበው ዝግጅት በመጨረሻው ሰዓት መታገዱ የቅርብ ጊዜ ዜና ነበር። ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ዝግጅቱን ለማቅረብ ጫፍ ላይ ሲደርስ ማንነታቸውን ያልገለጹ ” ሃያላኖች” የፈጸሙት ህግን ያልጠበቀ አካሄድ እስከዛሬ ድረስ ጠያቂ ብቅ አላለበትም። ከዚህ አንሳር አማራ ክልል ስራው ቢሆንም ለሕዝብ ፍላጎት፣ እንዲሁም ለጥበብ ባለሙያው መብት ክብር መስጠቱ ያስመሰገነው። ዝግጅቱ በክልሎች መልካም ፈቃድ በተለያዩ ከተሞች ይካሄዳል የሚል ሰፊ እቅድና ራዕይ ያለው መሆኑንን መገለጹ ይታወሳል። አሁን እነ ለማ መገርሳ ከሚያሰሙት የኢትዮጵያዊነት “ተሃድሶ” በመነሳት ኦሮሚያ ክልል ለቴዲ ጥያቄ በማቅረብ ፊንፊርኔ ላይ ዝግጅቱ እንዲደረግ ባማስቻል ቃላቸውን በተግባር ማሳየት ይገባቸዋል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *