በመጀመሪያ በዶ/ር መረራ መፈታት ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ! አሁን በነጻነት መናገር ይችላል! በገዛ አገሩ ማን ምን ያገባዋል! በቅጽበት እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ጉልበት እያገኘ ነው!! በታሰሩ ጊዜ ሊያምታቱን መረራን ከሌሎች ጋር ወንጅለዋቸው ነበር፡፡ የሚከተለውን ትዝብቴን ተናግሬ ነበር፡

በዚሁ ወደ ተነሳሁበት፡፡ ዘረኛው ኦነግ ከዘረኛው የህወሀቱ ትግሬ ጋር በመተባበር የመጀመሪያ ሥራ ያደረጉት ኢትዮጵያዊነትን ከሕዝብ ማጥፋት ነበር፡፡ ከሁሉም ሕዝብ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ኢላማ ነበር፡፡ ከኢትዮጵያዊነት አስወጡትና ለዘመናት መከራ ዳረጉት ብዙ ሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦችም የዚሁመ መከራ ሰለባ ሆኑ፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያዊነት ለአማራ ብቻ ተሰጥቶ ቆየ፡፡ አማራ በማንነቱ ቢታረድም፣ ቢታሰርም ቢሰቃይም ኢትዮጵያዊነቱ ግን እንዳለ ነው፡፡ ይህን ያየች ወያኔ ይህ አማራ ውስጥ የተዳፈነ ኢትዮጵያዊነት አንድ ቀን ጉድ እንደሚያደርጋት ተረዳች፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት ዋና ክምችት ያለበትን የአማራ ክልል ጎንደርን ኢላማ አደረገች፡፡ ቅማንትና አማራ የሚል የዘረኝነት መርዝ መርጨት ጀመረች፡፡ ይህ የሆነው ከጥቂት አመታት በፊት ነበር፡፡ ጉዳዩ እስከ ቅርብ ቀጥሎ በመጨረሻ ጎንደሬዎች እኛ በዘር አንለያይም የሚል ጽኑ አቋም በመያዛቸው የወያኔ ሴራ ውሃ በላው፡፡ ታዲያ ቅማንትና አማራ ብላ በተነሳችበት ወቅት ከዚህም ከዛም ለመግባት ያስቸገራት አማራነት ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ያየችው ወያኔ ቤተ አማራ የሚል ለአማራ ተቆርቋሪ በመምሰል አማራን ከኢትዮጵያዊነት የሚያመክንላት ቡድን መሠረተች፡፡

ልብ በሉ ይህ የተመሰረተው በቅማንት አማራ በሚል ዘመቻዋ ጊዜ ነው፡፡ ቡድኑን የሚመሩትም አማራን ከእነ ጭርሱ የማያውቁት ወያኔ ያሳደገቻቸው የአዲስ አበባና የሌሎች ቦታዎች አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ በኋላ ብዙ የምርም አማራ የሆኑ ይህን ቡድን ተቀላቀሉ፡፡ በአንድ ጊዜ ተመሰጉበት፡፡ ጉዳዩ ግን በሬ ሞኙ ሳሩ አይተህ ገደሉን ሳታይ ነው፡፡ ብዙ አማሮች ከመጀመሪያው ያለውን ሴራ ሳያጤኑ ደጋፊ ሆኑ ወና ተሳታፊም ሆኑ፡፡ ኦነግ ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ሲያመክን እንዲሁ ነበር፡፡ ኦሮሞ ሁሉ ለዘመናት የሞቱ ምክነያት የሆነውን ኦነግ ተከተለ ሌላውን ጠላ እኔ ብቻ አለ፡፡ በዛው ልክ ብዙ ሌሎች ኦሮሞን እንደ አውሬ ማየት ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም ኦሮሞ የተባለ ሁሉ በጠባብነት ተፈርጆ ሁሉ ነገሩ በጠላትነት እንዲታይ ተደረገ፡፡ ይህ ተረት አይደለም በአይናችን አይተን ያለፍንው እውነት እንጂ፡፡ እድሜ ለለማና ቡድኑ ኦሮሞን ወደ ጥልቅ እየወሰደች የነበረችውን የዘረኝነት መርከብ መሪዋን ይዘው ወደ ኢትዮጵያዊነት ሲመልሷት  ወያኔ መግቢያ አጣች፡፡ እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ እና ቤተ-አማራ አሁን በጣም መሽቷል፡፡

እንደ ኦነጋውያኑ ጊዜ አይመችም፡፡ አማራ በአማራነቱ ለ27ዓመት የታረደው አማራ ክልል አደለም፡፡ አማራ በአማራነቱ በሞተበትና በተሰቃየበት ቦታ ያለው አማራ እኮ ጠላቶቹ እንደሆናችሁ ከሁሉም በላይ ያውቃል፡፡ ዛሬ ላይ ይህ አማራ  ለዘመናት በመከራ የጠበቀውን ኢትዮጵያዊነት ሌሎች ወንድሞቹ እየተቀላቀሉት ድል እያገኘ ነው፡፡ አሁን አማራም ኦሮሞም በማንነት የሚገድላቸውን ጠላታቸውን አውቀውታል፡፡ በኢትዮጵያዊነት ፊት መቆም የማይችለው አውሬው ወያኔና የወያኔ አጋሮች (ኦነግና ሌሎች ዘረኞች) እንደሆኑ ተረድተዋል፡፡ ዛሬ ከረፈደ ወላጃቸው ወያኔ ራሱ መግቢያ በአጣበት ወቅት ቤተ-አማራ ተብዬው በኢትዮጵያዊነት ላይ ሊቆምር ይሞክራል፡፡ አማራነት የአማራ ክልልንም አይወክልም፡፡ ቅማንትና አማራ የተባለው እክ አማራነት አይወክልም ለማለት ነው፡፡ አገው አለ፡፡ ኦሮሞም ሌላም ሕዝብ አለ፡፡ የቤተ-አማራ አማራዊ ጽንፈኝነት አላማው ሁሉም በክልሉ ያሉ ሕዝቦች እኔም እኔም በሚል ዘረኝነት ጉሮኖ እንዲሰበሰቡና በክልሉም ሰላም እንዳይኖር፡፡ አማራንና ሌሎች የክልሉን ሕዝቦች ከኢትዮጵያዊነት ማምከንና ለወያኔ አቅም የሌለው እንደልብ የሚዘውር ማሕበረሰብ መፍጠር ነው፡፡ ሚስጢሩ ይሄና ይሄ ብቻ ነው፡፡

ልብ በሉ ጎንደር ላይ የተነሳው ኢትዮጵያዊነት በምን ያህል ወያኔን ወገቧን እንደሰበራት፡፡ ልብ በሉ እነ ለማና ቡድኑ ከሕዝቡ (ጎንደሬዎች) የተቀበሉት ኢትዮጵያዊነት በምን ያህል ፍጥነት ወያኔን ወደመቃብር እያፋጠናት እንደሆነ፡፡ አውን ለማና ቡድኑ ኦሮሞ ብቻ ብለው ኢትዮጵያዊነትን ባያነሱ አሁን ያመጡተን ስኬት ይቻላቸው ነበር? ዛሬ ሁሉም ደረቱን ነፍቶ ሊናገረው የሚችል ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት! በየትኛውም መስፈርት የዘር ጉሮኖ ውስጥ ገብቶ ዲሞክራሲ ፍትህ የሚባልን ማሰብ አይቻልም፡፡ ገና ብዙ የሚቀር ጉዳይ አለ፡፡ ማንም በማንነቱ የሚያገኘውም የሚያጣውም ጥቅም ሊኖር አይገባም፡፡ ማንም በማንነቱ መብቱ ሊገፈፍ አይገባም፡፡ አሳፋሪ በሚሆኑ ፖሊሲዎች እኮ ነው ዛሬ እየተነዳን ያለነው፡፡ ለማና ቡድኑ አሁን በፍጥነት የኦሮሚያ ክልል ሕገ-መንግስትን መናድ አለባቸው፡፡  ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ያለን ሌላ ነግር የለንም፡፡ ይህን የተናገሩት ራሳቸው ለማ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ከመራን በኢትዮጵያ ምድር ሁሉ መብት አለን፡፡ ይሄ ነው ወያኔን እያርበተበታት ያለው ኃይል፡፡ እንጂማ ማን ጠመንጃ ታጥቆ ተዋጋት፡፡ እንደ እንቧ ካብ ይንዳታል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ወያኔን እንጦሮጦስ ይጨምራታል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተውል ከዚህ በኋላ  አትታለል፡፡ እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው አንዴ ሳያየው ሁለተኛ በሌላ ቀን መንገድ ላይ ተጠቅሉ አግኝቶት ለጓደኛው ባለፈው የነደፈኝ እኮ ይሄ ነው ብሎ በጣቱ ነክቶ ሲያሳየው ነደፈው፡፡ እኛ ብዙ ጊዜ ተነድፈናል፡፡ በዘር ማንነት የምታስቡ ሁሉ ንስሀ ግቡ፡፡ ከዚህ በላይ እርግማን የለም፡፡ ቤተ አማራ የተባለው በቀጥታ በአማራ የኦነግ ግልባጭ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ብዙ ሕዝብ የሰመጠበት ግን ወደ መውደቂያው እየሄደ እንደሆነ አላስተውል ያለበት፡፡ እኛ በኢትዮጵያዊነታችን ወያኔን እያርበደብድነው ነው፡፡ ይሄው ነው ሚስጢሩ፡፡ ጥቂት ወደ መከላከያውና ሌሎች የታጠቁ ሀይላት ይሄንኑ ኢትዮጵያዊነት ማስረጽ ስንችል፡፡ ዘረኛ ሁሉ ወይ ይፈወሳል ወደ ቦታው ይላካል፡፡ ከመሸ የወያኔ ዘረኛ ቡድን ቤተ-አማራ መርከብ ላይ የወጣችሁ ውረዱ፡፡ አላማቸው ያደረጉት ምን እንደሚሰሩ ስለሚያውቁ ባሕር መሐል ትተዋችሁ እንደሚመለሱ አትጠራጠሩ፡፡ ይሄን ማስተዋል ካልቻላችሁ እናዝናለን፡፡

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! አሜን!

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *