የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ኮሚኒኬሽን ሃለፊ አቶ ታዬ ደንደዓ ክልሉ ”የክስ መዝገቦችን እያጣራን ነው። እሰከ ጥር 12 ድረስ አጣርተን እንጨርሳለን” ብለዋል። ”የፖለቲካ ተሳትፎ የሚባል ወንጀል የለም። ከፖለቲካ ተሳትፎ ጋር ተያይዞ የታሰሩ በሙሉ ይፈታሉ።” ሲሉ ከፌደራል አቃቤ ህጉ የተለየ መግለጫ ሰጡ።

“እስረኞች የሚፈቱበት ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የለም” ሲሉ ያስታወቁት ሃላፊው፣ ”በሽብር፣ ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን ለመናድ ሙከራ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሰረተባቸውም ይፈታሉ” ሲሉ አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ በግል ጸብ የሰው ህይወት ያጠፉ ወይም አካል ጉዳት ያደረሱ እስረኞች ምህረት እንደማያገኙ አመልክተዋል። የፌደራሉ አቃቤ ህግ ግን መስፈርት በማውጣት በሽብር፣ ህገመንግሥታዊ ሥርዓትን ለመናድ ሙከራ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሰረተባቸው እንደማይፈቱ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

አቶ ማሩ ቸኮል የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው ክልሉ ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ ነው ብለዋል። ክልሉ ልክ የፌደራል አቃቤ ሕጉ እንዳስቀመጣቸው ያሉ መስፈርቶች የሚኖሩት ሲሆን “እኛም የምንከተለው አካሄድ ተመሳሳይ ይሆናል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“ክሶችን የፌደራል ወይም የክልሉ ስልጣን የሆነውን የመለየት ስራም ይሰራል። ከዛ በኋላ የሚለቀቁትን እስረኞች ለሕዝቡም ለመገናኛ ብዙሃንም ይፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

በክልሉ የተዋቀረው ኮሚቴ ከርእሰ መስተዳድሩ፣ ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ እና ከሌሎች አባላት ጋር በመሆን ተወያይቷል ያሉት አቶ ማሩ በዚህ መግለጫ ወቅት የሚፈቱ ታራሚዎች ስም ዝርዝር ለምን አልደረሰም ለሚለው ጥያቄ የደቡብ ክልል ቀድሞ ተዘጋጅቶ ካልሆነ በስተቀር ታራሚው በርካታ ስለሆነ እና የማያዳግም ስራ ለመስራት እንዲያስችል እየሰራን ነው።

“ከዚህ በላይ ባይዘገይ እኔም ደስ ይለኛል ታራሚዎቹ ተለይተው እንዳለቁም ይፋ እናደርጋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር - ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *