መረራ ግልጽ፣ ሽብርን የሚጠላ፣ ዜጎች ሁሉ እኩል እንዲዳኙ የሚከራከር፣ ጠባብ አመለካከትን ቀድሞ የተዋጋና ያመከነ፣ የፊደል አባት፣ ሩህሩህ፣ ገሃድ ስሜቱን የሚገልጽ፣ ብሩህ አዕምሮ ያለው፣ አሳሪዎቹን ያነቃና ፊደል ያስቆጠረ፣ የሚያውቀውን ለማንም የሚናገር፣ ጀርባው የጸዳ፣ አገር ልታከብራቸው ከሚገባቸው መካከል የሆነ፣ ታማኝና ሰፊ ድጋፍ ያለው፣ አሁን ኦህዴድ ውስጥ ያሉትን ያሳደገ፣ ተስፋ የማይቆርጥ፣ የሕዝብ ልጅነቱን ለአፍታም የማይዘነጋና ለገበያ የማያቀርብ፣ የማይፈራ፣….  ዛጎል

ከመረራ ብዙ የሚጠብቁ ዜጎች የሚራሩለት ውድ የኢትዮጶያ ልጅ እንኳን በህይወት አጥሩ ተሰበረልህ። ውድ የመረራ ባልደረቦች በተለይም ብዙ የማይባልልህ ለጁ የሆንከው ኦልባና ለሊሳ የአንተም አጥር መሰበሩን በመጠባበቅ ላይ ሆነን ለሁላችሁም ” ይሕዝብ ልጆች” ትግላችሁን አድሳችሁ ያሰባችሁትን የዴሞክራሲ ጎዳና ኢትዮጵያ ላይ እንድትተክሉ ይሁን!! 

መረራ ዛሬ “መንግስት ሰፊ ድጋፍ ካላቸው የፖለቲካ ሀይሎች ጋር ሀቀኛ ድርድር በማድረግ ሁላችንንም በእኩል የምታስተናግድ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ቢያደርግ መልካም ነው” ሲል ወደሁዋላ እንደማይል አሳየ። 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *