ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የህወሓት ማ/ ኮ/ አማራር ግምገማ ወዴት ኣቅጣጫ እያቀና ነው? ምንስ ውጤትስ ይኖረዋል ?

ከኣስገደ ገብረስላሴ 
በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስራ ኣስፈጻሚ የተጀመረው የተሀድሶ ግምገማ እንደመሪ ግምገማ ሆኖ ወደ ኢህኣደግ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ እና የኣጋር ፓርቲዎች በታዛቢነት ተሸኝቶ በጠቅላላ ለ10 ሳምንታት (ለ70ቀናት)ያካያዱተና እየተካየደው ያለው ግምገማ እነሱ እንደሚሉት ስር ነቀል ግምገማ እያካየድን ነው በማለት ለራሳቸው በኣስመሳይነት ሲተቹ ተሰምተዋለ ። በተጨማሪ በዝህች ኣገር በተሳሳተ የኣማራር እስትራተጃችን ምክንያት ኣገርና ህዝብ ጎድተናል ብለው በህዝብ ፊት ሲናገሩም ሰምተናል ። ይህ ኣነጋገራቸው ግን ኣምነውበትና ኣስበውበት ናቸው ወይ ያስብላል ።

በቡዙ ወገኖች ግን የሚነግሩን ያሉ ከልባቸው የመነጨ ፍላጎት ንሮዋቸው ያደረገት ግምገማ ሳይሆን ፣ የኢትዮጱያ ህዝቦች ለ26 ኣመታት ያህል በደረሰበት ብሶት የወለደው መራራ ትግል ኣካይዶው ፣እልፍ ኣእላፍ ዜጎች በጅምላ መስዋእት ከፍለው ታስረው በስቃይ ምርመራ ተጎድተው ፣ ለስደት ለመከራ ተዳርገው ፣ ዜጎች በሀገራቸው የዜግነት መብታቸው ተነጥቀው በሞኖራቸው በሰላማዊ መንገድ ፍትህ ለማግኜት ባለመቻላቸው መርዋቸው ባደረጉት ህዝባዊ ኣመጽ ምክንያት ተገደውና በህዝብ ተጽእኖ በጭንቀት እያደረጉት ያለው ግምገማ ነው ይሉታል ። በእኔ እምነትም ህዝብ እያለው ያለው እደግፋለሁ ።

ይህ በጥልቀት ተሀድሶ በማድረግ ሙሱና እኪራይሰብሳቢነት ፣የከፋ የመልካም ኣስተዳደር እጦት እናጠፋለን የሚል ግምገማ የሚካየደው ያለው ጠ/ ምኒስቴር መለስ ሳለም ይካየድ ከነበረው የተሀድሶ ግምገማ በመሰረተ ሀሳብ ልዩነት እንኳን ባይነረው በዛን ጊዜ ግን በተግባር የማይታይ የመናገርና የመሸወድ ችሎታ ስለነበረው የህዝብ ተቃውሞ ኣንድ ጊዜ ይቀጣጠላል ኣንድ ጊዜ ይጠፋ ስለነበር ስልጣናቸው ለመራዘም ችለው ነበር ።

የኣሁኑ የህዝብ ጥያቄና ተቃውሞ ግን እንደድሮው በቀላሉ በመደናገር የሚበርድና የሚመለስ ኣልሆነም ።ምክንያቱም እኒህ ፍጡራን በኢትየጱያ ህዝብ ላይ ያደረሰሱት ችግር ጥልቀት ያለውና ስር የሰደደ በመሆኑ በጠግን ጠግን የሚፈታ ኣይደለም ። ጭራሹም በዚህ ኣገር መሰረታዊ የስርኣት ፣ ማለት የኣይዶሎጂ የፓሊሲ ፣በኣጠቃላይ የኣስተሳሰብና የስስቴም ለውጥ በነዚህ ሰዎች የሚመጣ ኣይደለም ።

ለዚሁ ሀቂ ኣንዱ ማሳያ በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ፣በኢህኣደግ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቲ በኣጋር ፓርቲዎች በታዛቢነት ታጅቦ የተካዬደ ግምገማ ምንም እንኳ የ100 ሚሊዮን የኢትየጱያ ህዝቦችና የኣለም ኣቀፍ ተጽኖ በፈጠረው ተገደው 26 ኣመት ሙሉ በሀገራችን እስር ቤቶች ፓለቲካ እስሮኞች የሉንም እያሉ ኖረው ኣሁን ሳያፍሩ ፓለቲካ እስሮኞች ስላሉን እንፈታለን በማለት ኣበረታች የሚመስል እድሜ ማስቀጠያ እርምጃ መውሰዳቸው ለሚቀጥለው የህዝቦች ሰላማዊ ትግል መልካም ጎደና የሚጠርግ በመምስል ።

በተጨማሪ ለሁሉም ክልሎች እንደመሪ ገምጋም ይሆናል ተብሎ ታሳቢ በማድረግ በመላው ሀገራችን በተለያዩ የመንግስት እና የፓርቲ ከፍተኞ ኣማራር የነበሩ ፣በትግራይ ክልልም እንደዚሁ በከፍተኛ ኣማራር የነበሩ ከ2000 በላይ የሚሆኑ የህወሓት ኣባላት ፓርቲ የተሳተፉበት ዝግ ግምገማ ለ9 ቀን ሲካየድ ሰንብቶ ነበር ።በዚሁ ግምገማ እጅግ ቡዙ ኣባላት ከፍተኛ ኣማራር የህዝብና የመንግስት ሀብት ዘርፈው ቡዙ ህንጻዎችና ቢላዎች ፣የንግድ ድርጅቶች በባለቤትነት እንደያዙ ራስ በራሳቸው እንደተጋላለጡ ምንም እንኳ ሚስጢር ከውስጣቸው እንዳወጡ ሞባይላቸው ተቀምተው ወደ ስብሰባ ኣዳራሽ እየገቡ ቢሰነብቱም በኣዳራሹ ይባል የነበረው ሚስጢር በምሳ እና ማታ ጊዜ በጎደና ይበትኑት ስለነበር ለህዝብ የሚደበቅ ኣልነበረም ። በተጨማሪም በሚስታቸው ፣በልጆቻቸው ፣በጓደኞቻቸው በዘመድ ኣዝማዳቸው ቡዙ ሀብት የሰበሰቡ ፣የያዙ እንደተገኙ ሲነገር ሰንብታል ።

በሌላ በኩል ሁሉም ከፍተኛ ኣማራሮች የመልካም ኣስተዳደር ጠንቆች መሆናቸው ፣ዜጎች በመልካም ኣስተዳደር ችግር ምክንያት ለስራ ኣጥነት ለስደት ለኣመጽ ፣የጠባብነትና የትምክህት ኣደጋ እንዲያቡቡ እንዳደረጉ እና የፍትህ የዲሞክራሲ መብቶች መከልከል ጠንቆች እነሱ መሆናቸው ፣ በየደረጃው ተጠያቄዎች እንደሚሆኑ ቀንጨብ እያደረጉ ሲነግሩን ሰንብቷል ነገር ግን በሙሶኞችና በኪራይ ሰብሳቢዎች ከመጤፍም የምታክል እንኳን እርምጃ ሲወስዱ ኣላየንም ።

ውጤቱ ግን የህወሓት ከፍተኛ ኣማራር ግምገማ ይቅርና ለመላው ሀገራችን ፣ለራሱ ኣባል ፓርቲዎች መሪ ግምገማና ተሞኩሮ ሊሆን በቀጥታ በነዚ የህወሓት ከፍተኛ ኣማራሮች ያገኜው ጥቅም የለም ። የነበረው የሁሉም ዜጎች የለውጥ ሙኞትም ባዶ ሆኖ ቀረ ።

ባዶ መሆኑ ተጨባጭ መረጋገጫ በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ፣በኢህኣደግ ስራኣስፈጻሚ ፣በህወሓት ከፍተኛ ኣማራር ከባድ ሂስና ግለሂስ ተደርጎ በባለስልጣናት ከባድ የቅጣት እርምጃ እንደሚወስዱ በኣቶ ሀይለማርያም ደሳለኝና በኣዲሱ ተሻሚ የትግራይ ክልል ምክትል ፕረዝዳንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሚዲያ በተግባር የማይ የማይዳሰስ የማይታይ ዲስኩር ሲያሰሙ ባጅቷል በተለይ በህወሓት ማእከላይኮሚቴ ስራ ኣስፈጻሚ በነኣባይ ወልዱና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ከባድ እርምጃ እንደወሰዱ በሚዲያ ኣውጀዋል የትግራይ ህዝብና መላው የኢትየጱያ ህዝበችም እነዚ ሰዎች በህወሓት መሪዎች ከባድ እርምጃ ከተወሰደ በሌላ ክልሎች ያሉ ወንጀሎኞችም እርምጃ ሊወስዱባቸው ነው የሚል ኣስተሳሰብ ኣሳድሮ ነበር ። ሆኖም የተመኙት ኣልሆነም እንዳው ውሀ ዘግነው ቀሩ ።

በኣንጻሩ ግን በፈጸሙት ገበና ከባድ እርምጃ የተወሰደባቸው ኣባይ ወልዱ የኣንባሳደርነት ሽመት ተሸልመዋል ። በመሆኑም ህወሓት ኢህኣደግ ባደረገው ግምገማና ለወደፊትም እስከ ቀበሌ የሚያካይደው ግምገማ በወንጀሎኞች እርምጃ እንደ መውሰድ ፈንታ በእከከኝ ልከክህ ብለው ህዝብን በኣጉል ተሰፋ ኣንሳፍፈው ታረቀው እንደሚሸኛኙ ያሳያል ።

እኒህ ሰዎች ኣሁንም ኣገሪቱ በጎዱት ባለስልጣናት ህዝብን ሊያስተምር በሚችል እርምጃ እንደመውሰድ ፈንታ በተለመደው ስልታቸው ካሁን በፊትም መለስ በነበረበት ጊዜ እየተከተሉት እንደመጡ ሁሉ ኣሁንም የመለስ የኣሰራር ስልት እና እስትራተጂ በመውረስ የክልል ባለስልጣን የነበሩ ወደ ኣንባሳደርነት ፣ወደ ጠቅላይ ምኒስቴር ቢሮ በኣማካሪነት ፣ወይ ወደ ፈደራል መንግስት ቢሮ ሀላፊነት ፣እንነደሚደበቁ የታወቀ ነው ።በሁሉም ክልሎች ዞኖች ወረዳዎች የነበሩ ከፍተኛና መካከለኛ ኣማራርም ከክልል እስከ ፈደራል መስራቤቶች ወይ በፓርቲዎች ኩባኒያዎች ይደበቁዋቸዋል እንጅ ኣንድም ኣመርቂ እርምጃ ኣይወስዱም ። ይህ ስልታቸው ደግሞ ህዝብ ኣስቀድሞ ወይ ኣልፏቸው ኣውቆት የቆዬ ነው ። ይህ ተንኮልም በሀገራችን ተፈጥሮ ላለው ሁሉ ኣቀፍ ቀውስ ያባብሰዋል እንጅ መፍትሄ ኣሆንም ።

በመጠቃል የኢህኣደግ ስራ ኣስፈጻሚ በጠ/ ምኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ ኣፈ ቀላጤነት ኣድርጎ የፓለቲካ እስሮኞች የመፍታት በአጠቃላይ በሀገሪቱ ያሉ መዝባሬዎች የሰብኣዊና ዲምክራሲያዊ ጠንቆች ለሆኑ ባለስልጣኖችና ኣጃቢ ሸሪኮቻቸው እርምጃ እነወስዳለን የሚለው ኣነጋገር ለጊዘው ማስታገሻ ነው እጅ ታማኝነት የለውም ።

ታማኝነት ሊነረው ከሆነ 1ኛ በ26 ኣመት ወስጥ የታሰሩ ፖለቲካ እሰሮኞች ፣ጋዜጦኞች ይፈቱ 2ኛ የህዝብ ፍላገት የልብ ትርታ ይደመጥ ።3ኛ የሀገራችን ሀብት በመዘበሩ ህዝቦች መካከል ግጭት ፈጥረው ለዘርኣዊ እልቂት የዳረጉ ፣የሀገር ሀብት ያወደሙ ባለስልጣናትና ተላላኪዎቻቸው ላይ ህዝብ የሚያምነው ተጨባጭ እርምጃ ይወሰድ ። 4ኛ በኣሁኑ ጊዜ መላው የኢትዮጱያ ህዝቦች ፣ባገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የሰላም ፓለቲካ ፓርቲዎች ፣ ስቢክ ማህበራት ፣ታዋቂ ግለሰዎች ፓለቲከኞች ፣ሙሁራኖች በሀገራች ያለው በኢህኣደግ የተባላሸ ኣማራር በምን መንገድና ኣቅጣጫ እንደሚፈታ ኣቅጣጫ ላይ ኣንድ ኣይነት መግባባትና ድምዳሜ ደርሰዋል ።በመሆኑም ኢህኣደግ ልብገዝቶ የነዚህ ህዝቦችና ሊሂቃኖች ድምዳሜ ያድምጥ ። ካለበለዝያ ወጤቱ እጅጉን ኣደጋ ነው !!!
ከኣስገደ ገብረስላሴ
መቀለ
12 / 05 / 2010