አገር ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአንድ ዓመት ያህል ከኢሕአዴግ ጋር እያደረጉት ካለው ድርድር የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ራሱን እንዳገለለ አስታወቀ፡፡ ኢራፓ ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ፓርቲዎቹ በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ለመወያየት በተሰበሰቡበት ወቅት ነው፡፡
‹‹እስካሁን ባደረግነው አጠቃላይ የድርድር ሒደት የምናቀርበው ሐሳብ ተቀባይነት እያገኘ ባለመምጣቱ ኢራፓ እየተካሄደ ካለው የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር ራሱን አግልሏል፤›› ያሉት የፓርቲው ተወካይ፣ ከዛሬ በኋላ በድርድሩ ላይ አንገኝም በማለት ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ወጥተዋል፡፡
ኢራፓ ዛሬ ለአምስተኛ ጊዜ ውይይት እየተደረገበት ያለውን የፀረ ሽብር ሕግ ሙሉ በሙሉ እንዲቀር አቋሙ እንደሆነ ገልጾ ነው ከድርድሩ ራሱን ያገለለው፡፡
Reporter Amharic ነአምን አሸናፊ phto Reporter
Related stories ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው
Powered by Inline Related Posts
Send news by email
just click on follow button and you will get every article when posted automatically. if you need to send article see our email on contact us. thanks