ለናሳ(NASA) ሁለት የኤሮ-ስፔስ መወርወሪያ ሜካኒዝም ለቦይንግ ኩባንያ ሲሙሌተር (Flight Dynamic Simulator) እና አድቫንስድ ወይንም ኔክስት ጀነሬሽን (Advance or Next Generation) በመባል የሚታወቁትን ግሎባል ፖዚሽን ሳተላይት ሲስተም(Global Positioning Satellite System) ከፈለሰፉት ውስጥ አንደኛው ሰው እሳቸው ነበሩ ዶክተር ቅጣው Trans Tech International በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት በመመስረት የተለያዩ ሀገሮች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ በአማካሪነት አገልገለዋል። …. (source ጉዳያችን )

ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ የካቲት 25 ቀን 1948 (እ.ኤ.አ) ከአባታቸው ከአቶ እጅጉ ሃይሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ በላይነህ በከፋ ጠቅላይ ግዛት በቦንጋ ከተማ ተወለዱ።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦንጋ፣ በዋከና በጅማ ከተማ ካጠናቀቁ በኋላ በባህር ዳር በሚገኘው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

ዶክተር ቅጣው ወደ ጃፓን አገር በመሄድ በኦሳካ ዪኒቨርስቲ በቋንቋና የጃፓን ኢኮኖሚ፣በሄሮሺማ ዩንቨርስቲ የኢንደስትሪ እና የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ አጥንተው ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

በኋላም አሜሪካን ሀገር ስኮላር ሺፕ አግኝተው በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ማስትሬታቸውን በመጨረሻም ለትምህርት ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በኤሮ-ስፔስ ምህንድስና ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።

(በልጅነታቸውም የድቁና ትምህርትን ቀስመዋል፡፡)

ዶክተር ቅጣው በናሳ (NASA) በሲስተም መሃንዲስነትና በጠፈር ሳይንቲስትነት የሰሩ ሲሆን ከሌሎች መሃንዲሶችና ሳይንትስቶች ጋር በመተባበር ለእኛ አለም (Planet Earth) እና ለተቀሩት ፕላኔቶች የምርምር ሳይንስ (Planetary Science Research and Exploration) የሚረዱ የጠፈር መንኮራኩሮችና ሮኬቶች ፈጥረዋል።

ዶክተር ቅጣው በዚህ ከፈጣሪ በተቸሩት ታላቅ ችሎታና እውቅት ለዚህች ለምንኖርባት ዓለምና ሕዝብ ታላቅ አስተዋፅዎ አበርክትዋል።

ከነዚህም ጥቂቱን ለመጥቀስ ለናሳ(NASA) ሁለት የኤሮ-ስፔስ መወርወሪያ ሜካኒዝም ለቦይንግ ኩባንያ ሲሙሌተር (Flight Dynamic Simulator) እና አድቫንስድ ወይንም ኔክስት ጀነሬሽን (Advance or Next Generation) በመባል የሚታወቁትን ግሎባል ፖዚሽን ሳተላይት ሲስተም(Global Positioning Satellite System) ከፈለሰፉት ውስጥ አንደኛው ሰው እሳቸው ነበሩ ዶክተር ቅጣው Trans Tech International በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት በመመስረት የተለያዩ ሀገሮች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ በአማካሪነት አገልገለዋል።

ዶክተር ቅጣው ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ስቴላ እጅጉ ጋር በመልካምና በደስታ ጋብቻ ተጣምረው የኖሩ ሲሆን ቢንያም ፣ ያሬድ እና አቢጋኤል የተባሉ የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት አባት ነበሩ።

ዶክተር ቅጣው እጅጉ ወደ ኦስትን ቴክሳስ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ መጥተው ድንገት በደርሰባቸው ሕመም ምክንያት በጥር 13 ቀን 2006 (እ.ኤ.አ) በ58 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ዶክተር ቅጣው እጅጉ በመልካም ባህሪያቸው የተወደዱ፣ በትህትናቸው የተመሰገኑ፣ በስራቸው የተደነቁ፣ በራዕያቸው ብዙ ተከታዮችን ያፈሩ፣ የብዙዎች ተስፋና አርዓያ እንዲሁም የሀገር ኩራት የሆኑ ታላቅ ሰው ነበሩ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *