(ጌታቸው ሽፈራው)

ህወሓት አሁንም የውርደት ካባውን ይዞ እየተጓዘ ነው። ጠዋት የተናገረውም ማታ የሚክደው ሕወሓት እስረኛ እፈታለሁ ብሎ ለፍልፎ ከአንድ ሺህ በላይ የአማራና የኦሮሞ ልጆች በታሰሩበት 115 እስረኞች ፈትቻለሁ ብሏል። ሆኖም እፈታቸዋለሁ ካላቸው መካከለ

1) ሉሉ መሰለ
2) በጋሻው ዱንጋ
3) ጌታሁን ቃጳ
4) ቶሎሳ በዳዳ
5) ዲንሳ ፉፋ
6) ያረጋል ሙሉ ዓለም ፈትቻለሁ ብሎ ወደ ቃሊቲ አዛውሯቸዋል። አሁንም አልፈታቸውም። ቃሊቲ ዞን 4 ይገኛሉ።

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ ከላይ እስከታች በሕወሓት አባላት የተያዘው የቂሊንጦ እስር ቤት፣ ገንዘብ እየተመዘበረበት ይገኛል። ከየ አካባቢው ታፍነው የመጡትን የድሃ ልጆች በሙሉ ተፈቱ የተባሉት ምንም ሳንቲም ሳይሰጣቸው፣ ከማጎሪያ ቤት አውጥተው ጥለዋቸዋል። የቂሊንጦ ኃላፊዎች ለእስረኛው ምንም ገንዘብ ሳይሰጡ በአንድ ታራሚ 695 ብር ተካፍለዋል። በ115 እስረኞች ስም 77925 ብር ተካፍለዋል። ይህን ስንል ያለ ማስረጃ አይደለም። ከስር ያለው ማስረጃ እኛ እስረኞች ከእስር ቤት ያገኘነውና ያስወጣነው ነው!

(ሰነዱ የማረሚያ ቤቱ ማህተም የሚጎድለው ቢሆንም ከእስረኞች የተገኘ ነው። በቂሊንጦ እስር ቤት እስረኞች በኮምፒውተር ማፃፍ አይችሉም። እስረኞች በፖሊስ አማካኝነት ማህተም ሳትመታበት አግኝተውት ነው ተብሎ ይገመታል)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *