የሀገሪቱ ባለስልጣናት በዓለ ሲመቱን ከሀገር ክህደት ለይተው እንደማያዩት እና ኦዲንጋንም ለእስር ሊቢያበቃቸው እንደሚችል ቢያስጠነቅቁም የተቃዋሚ መሪው ወደ ኋላ አላሉም፡፡ 10 ሺህ በሚልቁ ደጋፊዎቻቸው ፊት ዛሬ በናይሮቢ ባለ መናፈሻ መጽሀፍ ቅዱስ ይዘው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

“እኔ ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ ከበላይ የተሰጠኝ ጥሪ በመከተል ኬንያ ሪፐብሊክን ፕሬዝዳትነት ተረክቤያለሁ” ብለዋል በቃለ መሃላቸው። ኦዲንጋ “ለኬንያውያን የገባነውን ቃል አክብረናል” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ዛሬ ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙም አስታውቀዋል፡፡ በግርግር የተሞላው ስነ ስርዓት በአጭሩ ቢቋጭም የኦዲንጋ ደጋፊዎች ግን ለሰዓታት በጠራራ ጸሐይ የተቃዋሚ መሪውን በትእግስት ሲጠብቁ ቆይተዋል፡፡

ናሳ ተብሎ የሚታወቀውን እና ኦዲንጋ የሚመሩትን የተቃዋሚዎች ጥምረት የሚደግፈው ላሪ ኦዩጊ ተከታዩን ብሏል፡፡ “ለገዢው ፓርቲ የምንነግረው ሀገሪቱ መከፋፈሏን እና የኬንያ ህዝቦች ህገመንግስቱን የሚለውን ለመቀበል መወሰናቸውን ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ራሱ የሁሉም ሉኡላዊ ስልጣኖች የኬንያ ህዝቦች መሆናቸውን እና ተግባራዊ የሚደረጉትም በህገመንግስቱ መሰረት መሆኑን ይገልጻል፡፡ ለዚህም ነው በአግባቡ የተመረጡትን ፕሬዝዳንታችንን ራይላ ኦዲንጋን ቃለ መሃላ ለማስፈጸም እዚህ የተገኘነው” ሲል በስነስርዓቱ የተገኘበትን ምክንያት አስረድቷል።

በኦዲንጋ እርምጃ ደስተኛ ያልሆነው የኬንያ መንግስት በዓለ ሲመታቸውን በቀጥታ ሲያስተላልፉ የነበሩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡ የኬንያ መንግስት በመገናኛ ብዙሃኑ ላይ የወሰደው እርምጃ ትችትቶች አስከትሎበታል፡፡ DW radio

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *