…የጥገኛ ዝቅጠት መንገድ ረጅም ጊዜ ሳይቆይ ወደ ጠቅላላ መበታተንና ፍጅት የሚያመራ እንደሆነ ተተንትኖ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ በሬ ገደል ውስጥ የሚገባው ሳሩን እያየ ነው፡፡ ጅብም የቆሰለ ስጋውን እየበላ የሚሞተው የሌለ ስጋ ያገኘ መስሎት ነው፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው በኢህአዴግ የታቀፉ ድርጅቶች መጀመሪያ ራሳቸውን ካጠሩ ከጅብ መንጋጋ  ሊያመልጡ ይችላሉ፡፡ አለበለዚያ የጥገኛነት አመለካከትና ተግባር ከወረራቸው እርስ በራሳቸው እየተቦጫጨቁ ሊበተኑ ይችላሉ … አዲስ አበባ ኢህአዴግ

ከጥገኛ ዝቅጠት አደጋ ራሳችን በማፅዳት የከተማችን ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ እንዲጠናከር ተግተን እንስራ! ይስሀቅ ግርማይ

የዝቅጠት አደጋው በዋነኛነት ትግልን ስልጣንን እንደ ህብረተሰባዊ የለውጥ መሳሪያ ሳይሆን እንደ ኑሮ መደጎሚያና ራሱን እንደቻለ አላማ መጠቀም ነው፡፡ ዋነኛው የዝቅጠት ማሳያ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት እየተረባረብ እውን ከሚሆነው ልማት በምታደርገው የጉልበትና የችሎታ አስተዋፅኦ መጠን እየተጠቀምክ ለመሄድ ያለመፈለግና የእላፊ ተጠቃሚነት ፍላጎት ነው፡፡

ነገር ግን አስተማማኝ ዴሞክራሲን በማስፈን የህዝባችንን ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ካላረጋገጥን በጣም የተወሳሰበ ብሔራዊ ተዋፅኦ ባለበት/በነበረበት አደገኛ ግጭት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በመሆኑም ጠባብነትና ትምክህትን በዴሞራክሲያዊ ብሔርተኝነት ተክቶ ህዝቡ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ፈጣን ልማት ማረጋገጥ ከጠቅላላ መበታተንና ፍጅት እና ውድቀት የሚያላቅቀን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ብቻ ነው፡፡

አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ማንነታችንን ጠብቀን ከቀጠልን ኢህአዴግ አደጋው ይወገዳል፤ አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ማንነትን መጠበቅ አቅቶን ለጥገኛ ዝቅጠት አደጋ ከተጋለጥን አጠቃላይ እልቂትና ውድቀት መምጣቱ የማይቀር ነው፡፡

አብዮታዊ ዴሞክራሲ ድርጅታችን የነብር ጅራት ይዟል፡፡ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር ካፈነገጠና መስመሩን ከለቀቀ በነብሩ መበላታችን አይቀርም፡፡ የጥገኛ ዝቅጠት ጠቅላላ የጥፋት ጉዞ መሆኑን በይበልጥ ለመረዳት ቀላል ምሳሌዎች ማንሳት ይቻላል፡፡

የጥገኛ ዝቅጠት ጉዞ ስር እየሰደደ ሲሄድ ጠባብነትና ትምክህት እየተስፋፉ መሄዳቸው የግድ ነው፡፡ ሁሉም ሰው በየብሔሩ እየተከለለ የራሱን ብሔር ተወላጅ ወዳጅ፣ የሌላውን ደግሞ ተጠርጣሪና ጠላት አድርጎ ያያል፡፡ ሁሉም በየብሔሩ አጥር ውስጥ እየተከለለ ገንዘብ፣ ስልጣንና ጥቅምን ለማግኘት ይሯሯጣል፡፡ በአንድ አንድ የአገራችን አካባቢዎች ከጥልቅ ተሃድሶ በኋላም እየታየ ያለው ይኸው ነው፡፡

ይህ አመለካከትና ተግባር ከኢህአዴግ ውጭ የሚታይ ብቻ ሳይሆን በራሱ በኢህአዴግ ውስጥም ጠባብነትና ትምክህት ተስፋፍቶ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እርስ በእርስ በጠላትነት እየተያዩ በሂደት መበታተንና መጋጨታቸው የማይቀር ይሆናል፡፡

ከሁሉም በፊት የጥገኛ ዝቅጠት መንገድ ረጅም ጊዜ ሳይቆይ ወደ ጠቅላላ መበታተንና ፍጅት የሚያመራ እንደሆነ ተተንትኖ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ በሬ ገደል ውስጥ የሚገባው ሳሩን እያየ ነው፡፡ ጅብም የቆሰለ ስጋውን እየበላ የሚሞተው የሌለ ስጋ ያገኘ መስሎት ነው፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው በኢህአዴግ የታቀፉ ድርጅቶች መጀመሪያ ራሳቸውን ካጠሩ ከጅብ መንጋጋ  ሊያመልጡ ይችላሉ፡፡ አለበለዚያ የጥገኛነት አመለካከትና ተግባር ከወረራቸው እርስ በራሳቸው እየተቦጫጨቁ ሊበተኑ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የዝቅጠት ሂደት የት እንዳደረሰን በጥልቅ ተሃድሶ ጉዞአችን በተግባር እንዴት እንደሆነ አይተናል፡፡

በአንድ አንዱ የአገሪቱ አካባቢዎች እየታየ ያለው ችግር ገና ያልተፈቱ ችግሮች መኖራቸውን ያሳየናል፡፡ ነገር ግን የጥገኝነትና የዝቅጠት አደጋ በፍፁም መደገም የለበትም ብለን ሌት ከቀን መስራት አለብን፡፡ የሚያዝናና ግዜ የለንም፡፡ በየአካባቢያችን አመራሩ ያጋጠመውን አደጋ ‹ዳግም ልናየው አይገባም!› የሚል መሪ መፈክር ይዞ በተግባር መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡

በተሃድሶ ሂደት ያረጋገጥናቸውን አንፀባራቂ ድሎችን በመጠበቅ የጥገኛ ዝቅጠት ችግር እንደገና እንዳይደገም ሁሉንም ድክመቶቻችንና ለዚህ አደጋ ያጋለጡት ጉድለቶች ከስር መሰረታቸው ለማስወገድ መንቀሳቀስ ይገባናል፡፡

የጠባብነትና የትምክህት አስተሳሰብና ተግባር ጠራርገን ለማስወገድ ቆርጠን መነሳት አለብን፡፡ እነዚህም አመለካከቶችም ከስር መሰረታቸው መነቀል አለባቸው፡፡

የዝቅጠት አደጋም ከስር መሰረቱ ለማስወገድ የሚያስችለንን ግዜ ማይሰጥ ስለሆነ በቁርጠኝነት መታገል ይኖርብናል፡፡ ሰዎችን በዘራቸው የሚመዝነውን ጥገኛ አመለካከት ከባቢያዊነቱ፣ ጨምሮ በሁሉም መልኮቹ በምሬት ልንኮንነው፣ ከራሳችንና ከህዝባችን አውጥተን መጣል ጠንክሮ መታገል የህልውና ጉዳይ ይሆናል፡፡

ጠባብነት ልክ እንደ ትምክህትኝነት የተዛባ ግንኙነት መገለጫ ነው፡፡ ከአለፈው ወይም በተጨባጭ ከሚታየው የትምክህተኝነት ችግር በመነሳት በብሄር ብሄረሰቦች መካከል የነበረውንና ያለውን ትስስር የአብሮነት ገመድ ለመበጣጠስ የሚረባረብ ሃይል ነው፡፡

የጠባብነት ቡድን ዋና ዓላማ በተሸሸገበት ብሄር ብሄረሰብ ጎጥና መደብ ውስጥ በመሆን የኪራይ ሰብሳቢነት ቡድን ዋና ሃይል ወይም ምንጭ መሆን ነው፡፡ በብሄር ብሄረሰብ ውስጥ ያለው የኪራይ ሰብሳቢነት ጥገኛ ሃይል ዋና ስትራቴጅውም መነጣጠል ነው፡፡

ትምክህተኝነት የበላይነት በነበረበት ወቅት የጠባብነት ሃይል ብሄራዊ ጭቆናን መነሻ በማድረግ ጭቆናው የሚወገድበት ትክክለኛ ስትራቴጂ ከመከተል ይልቅ የጭቆናውን መልኮች ህዝቦችን ለማራራቅ፣ ቅራኔዎችን ለማጋጋልና ለመገንጠል ዓላማ ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ በሌላ መልኩ የጠባብነት ሃይል ዋና ባህሪ የብሄር ካባን በመልበስ የኪራይ ሰብሳቢነት ዓላማን ማሳካት ሲሆን ትምክህተኛ የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ስልቶችም እያጣጣመ በተመሳሳይ መንገድ ይጠቀምባቸዋል፡፡

ስለሆነም ከላይ የተገለፀው የትምክህት የጠባብነት አደጋዎች ለመመከት ዋናው መፍትሄው የውስጠ ድርጅት ትግላችንን ማጠናከር ይሆናል፡፡

ይህም ሲባል አብዮታዊ አመለካከት እሳቱን የሚለኩሰው የውስጠ ድርጅት ትግል ይሆናል፡፡ ይህ ከተለኮሰ በኋላ በራሱ ተነሳሽነት ብዙ ርቀት ሊሂድ የማይችልበትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ  ማህበራዊ መሰረቶች መነቃቃት ይጀምራሉ፣ ይጠናከራሉ፡፡ ይህ የውስጠ ድርጅት ትግሉን ይበልጥ ያጠራዋል፡፡ ይበልጥ ያጠናክረዋል፡፡ ይበልጥ የጠራውና የተጠናከረው የውስጠ ድርጅት ህይወት ተመልሶ በህብረተሰብ ውስጥ የሚካሄደውን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ትግል ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል፡፡ በዚህም መልኩ የውስጠ ድርጅት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ባህሪውን የመጠበቅ ትግል በአሸናፊነት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል የፖለቲካ ህይወታቸው የተገነባና ግንባታው የተሟሟቀ ከልሆነ የትምክህትና ጠባብነት አመለካከትና ተግባር እየፋፋ ይሄዳል፡፡ አመለካከቶቹ የበላይነት ከያዙ ደግሞ ስርዓታችን ለአደጋ ይጋለጣል፡፡

ስለሆነም የስርኣታችን አደጋ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር መሆኑ ይታወቃል፡፡ እሱን የሚመግቡት የጠባብነትና ትምክህት አስተሳሰብና ተግባራት የተጀመረው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታችንን በመሸርሸር የፀረ- ዴሞክራሲ ኔትወርክ ትስስሮችን የሚፈጥሩና ህዝብን እርስ በእርስ በማጋጨት ለአደጋ የሚዳርጉ በመሆናቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ቅድሚያ ራሳችንን በማፅዳት ሌሎች የዚሁ አመለካከት ሰለባ የሆኑትን ያለምህረት በመታገል የድርጅታችንና አገራችንን ህልውና ልንታገል ይገባል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *