ድሬደዋ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተወጠረች ከተማ ናት። ከፍተኛ የወሃ ችግር ያምሳታል። የጤና ኬላዎችና የአምቡላንስ ችግር ዜጎችን ዋጋ እያስከፈላቸው ነው። አሁን ይፋ እንደሆነው ደግም ከተማዋ እሳት ቢነሳ ራስዋን የምትታደግበት አንድም የሳት አደጋ መከላከያ መኪና የላትም። የሳት አደጋ ሃይሉ ባዶ እጁን ነው። የድሬደዋ ተንሳ እንጂ ስንት ከተሞች ናቸው የእሳት አደጋ መከላከያ መከላከያ ተሽከርካሪ ያላቸው?

የethiopian fire birgade ምስል ውጤት

የድሬ ደዋ ምክር ቤት ስብሰባ የሞቀ ነበር። “አንዱ አባል ድሬደዋን የምታክል ከተማ” አሉ። ሃዘንና ቁጭት፣ እንዲሁም መገረም በተሞላበት ” ድሬደዋን የሚያክል አንድ ከተማ አንድ እሳት አደጋ መከላከያ መኪና የለውም” የመስተዳደሩ መሪ የውጭ ምንዛሬ ችግር ያመጣው ጣጣ መሆንኑ አስታውቀዋል።
እንደ ተናጋሪው ገለጻ ድሬደዋ አንድ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና ብቻ ነበራት። እሱም ተበላሽቶ ለጥገና ተልኮ በዛው ቀርቷል። ወይም አልተመለሰም። ምክንያቱም አይታወቅም። አዲስ እንዲገዛ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ተግባራዊ አልሆነም።
ስብሰባውን እያሳየ ዘናውን ያስተላለፈው ENN መስተዳደሩ ጥያቄውን ለፌደራል ቢያቀርቡም ችግሩ የውጭ ማንዛሬ እጥረት ስለሆነ ሊገዛ አልቻለም። እጅግ ሞቃታማ በሆነችው ድሬደዋ እሳት ቢነሳ በቂ ወሃም ሆነ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና የለም።
በተመሳሳይ የአምቡላንስ ችግር ስላለ አምቡላንሶች እንዲገዙለት የድሬደዋ መስተዳድር ገንዘብ ለፌደራል የጤና ጥበቃ ቢልክም ምንም ምላሽ እንዳላገኘ፣ ይህም ለዓመት በላይ ማስቆጠሩ በስብሰባው ተመልክቷል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *