ፎቶ ቢቢሲ ሶማሊኛ

በሃማሬሳ ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ካምፕ በተካሄደው ግድያ የመከላከያም ሆነ የፌደራል ልዩ ፖሊስ እጁ እንደሌለበት የሃረሪ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ እስክንድር አብዱራህማን ለኢ ኤን ኤን አስታወቁ። የምስራቅ ሃረርጌ አስተዳዳሪ በበኩላቸው አቶ ጀማል አህመድ የመከላከያ ታጣቂዎች ግድያ መፈጸማቸውን ለቪኦኤ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ዜናውን በቅድሚያ ያሰራጨ ሲሆን የኦሮሚያ ፖሊሶችም እንደተገደሉ አመልክቷል።

የችግሩ መንሴ የሆነው የእርዳታ እህል የጫኑ መኪናዎች ጉዳይ መሆኑንን ሁሉም አካላት ያስረዳሉ። ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ሃማሬሳ የተጠለሉ ተረጂዎችም ይህንኑ ያረጋግጣሉ። የሃረሪ ክልል ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ማብራሪያ ለመስጥት ምን ያህል አግባብነት እንዳለው ባይታወቅም፣ አቶ እስክንድር ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑንን አመልክተዋል።

በስፍራው ጥበቃ የሚያደርገው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል መሆኑንን ያመለከቱት አቶ እስክንድር ” በስፍራው የመከላከያም ሆነ የፌደራል ፖሊስ አልነበረም። ጉዳዩ ሆን ተብሎ መደረጉን የሚያሳየው ብጥብጡ የተከሰተው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ባለበት መሆኑ ነው” ሲሉ ተደምተዋል።

ሰባት ከባድ የጭነት መኪኖች የእርዳታ እህል ጭነው ወደዚያ እንደሚመጡ አስቀድሞ መረጃ ያላቸው ተፈናቃዮች መኪኖቹን በማስገደድ ወደ መጠለያው ግቢ አስገብተዋል። መኪኖቹን በማስገደድ ካስገቡበት ለማስወጣት ሲሞከር ችግር ተፈጠረ። አራት ሰዎች ሞቱ። አስር የሚሆኑ ቆሰሉ። እንደ አቶ እስክንድር ገለጻ። 150 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ማሽኖችና ሰባቱም ተሽከርካሪዎች ነደዱ። ሃላፊውን ያናገረው ኢ ኤን ኤን ዜናውን ለማመጣጠን የኦሮሚያንና የፌደራል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትን ማግኘት አለመቻሉን ተናግሯል። ኢ ኤን ኤን ይህንን ማለቱ ግን ትዝብት ውስጥ የሚጥለው ሆኗል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

ቪኦኤ ያናገራቸው የምስራቅ ሃረርጌ አስተዳዳሪ አኦ ጀማል አህመድ ግድያው በመከላከያ ሰራዊት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። በሃማሬሳ መጠለያ ያሉ ተፈናቃዮች እንደሚሉት ለነሱ የመጣውን እርዳታ እህል ከጉሮሯቸው ለመንጠቅ ሲሞከር ግጭቱ መነሳቱን አመልክተዋል። አቶ ጀማል አህመድ እንዳሉት ጉዳዩ የሚጣራ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን መናገር አይቻልም።

የጀርመን ሬዲዮ ይህንን ዘግቧል። በሐማሬሳ የተፈናቃዮች መጠለያ ትላንት በተቀሰቀሰው ግጭት አራት ሰዎች ሞተው 11 ሰዎች መቁሰላቸውን የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አህመዴ ለዶይቼ ቬለ ገለጹ፡፡ ወደ 3‚500 ገደማ የሚሆኑ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች በተጠለሉበት በዚሁ ጣቢያ ዛሬም ተቃውሞ የነበረ ቢሆንም ጉዳት አለመድረሱንም ተናግረዋል፡፡ 

የትናንትናው ግጭት የተነሳው እህል ጭነው እየተጓዙ የነበሩ መኪኖች “በማይታወቁ ሰዎች ተይዘው ወደ ተፈናቃዮች መጠለያ እንዲገቡ በመደረጋቸው” እና የጸጥታ ኃይሎች እነርሱን ለማስለቀቅ ባደረጉት ሙከራ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በኋላ የተፈጠረውን ደግሞ እንዲህ አስረድተዋል፡፡  

“የፌደራል የጸጥታ አካላት እና የክልል ጸጥታ አካላት (የሐረሪ እና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን) አሉ፡፡ መጨረሻ ላይ እዚያ መከላከያ ገብቶ ነበር፡፡ እንግዲህ በዚህ መካከል በተፈጠረ ችግር ነው የሰው ህይወት ሊጠፋ የቻለው፡፡ ያንን መኪና ለማስለቀቅ በሚመጡ እና እዚያ መሃል ባለው ያው የሰው ህይወት ሊጠፋ ችሏል፡፡ አራት [ሰዎች]  ህይወታቸው ሲያልፍ ወደ 11 የሚሆኑ የቆሰሉት ናቸው” ብለዋል፡፡  

ከሟቾቹ ውስጥ አንድ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባል እና አንዲት ሴት እንደሚገኙበት አቶ ጀማል አስረድተዋል፡፡ በትናትናው ግጭት የቆሰሉት በሐረር ፋና ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ ጀማል ቁስለኞቹ በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡ የሐረሪ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ በሐማሬሳው ሁከት ሰባት እህል ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከባድ መኪኖች እና ማሽኖች መቃጠላቸውን አስታውቋል፡፡ ድርጊቱ የፈጸሙት “የተደራጁ የፀረ ሰላም ኃይሎች” ነው ሲል ከስሷል።   

በሐማሬሳ መጠለያ ጣቢያ ዛሬም ተቃውሞ እንደነበር ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በጣቢያው ተቃውሞ እንደነበር ያረጋገጡት አቶ ጀማል በግቢው ያሉ የመከላከያ ኃይሎች እንዲወጡ በመጠየቅ የተደረገ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ የዛሬውን ውሎ አስመልክቶም “ያለው ሁኔታ ጠዋት በግቢው የተወሰነ ግርግር ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ገብተው ግቢውን እየጠበቁ ናቸው ያሉት፡፡ አሁን ከሀዘን ውጭ የተረጋጋ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው ማለት ይቻላል” ብለዋል፡፡

12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ከሐረር ከተማ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ገደማ ላይ የሚገኘው የሐማሬሳ መጠለያ ጣቢያ በሐረሪ ክልል ስር የሚገኝ ቢሆንም የጣቢያውን ጸጥታ ይቆጣጠር የነበረው እና ለተፈናቃዮች እርዳታ የሚያቀርበው የኦሮሚያ ክልል ነበር፡፡ የትላንትናውን ግጭት ተከትሎ በስፍራው ላይ የተገኙት የመከላከያ ሠራዊት አባላት «እንዴት ወደ ቦታው እንደመጡ መረጃው የለኝም» ሲሉ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳዳሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ «ግጭቱን በሌላ መልኩ ከመቆጣጠር ይልቅ የኃይል እርምጃ ወስደዋል» ስለመባሉ ጠይቀናቸው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

“የችግሩ ሁኔታን ለማጣራት ብዙ ሰዓት ወስደን ስናጣራ ነበር፡፡ ሙሉ ዝርዝር መስጠት ስለማልችል ነው እንጂ ያየናቸው፣ የገመገምናቸው፣ በየቦታው የተፈጠሩ ችግሮች አይተናል፡፡ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ኦሮሞዎች ያሉበት መጠለያ ነውና ለዚህ ነው የኦሮሚያ ፖሊስ እና ሌሎች የመስተዳድር አካላት እዚያ ላይ የሚሳተፉት እንጂ መስተዳድሩ የሌላ ክልል መስተዳድር እንደሆነ ብንገነዘብ ጥሩ ነው፡፡ አጠቃላይ ስለ እዚህ የምንግራችሁ ሌላ ቦታም ችግሮች ይከሰታሉ፤ እርሱ በራሱ መንገድ እየተጣራ ነው፡፡ በኦሮሚያ [ክልላዊ] መንግስትም፣ በሌሎች በኦህዴድም፣ በኢህአዴግም አጣርቶ ያው አቅጣጫ እየተቀመጠበት ነው ያለው፡፡ ከዚያ ውጭ ትላንትና በተፈጠረው ሁኔታ ጉዳዩ ተጣርቶ፣ በትክክልም የሰው ህይወት ያጠፋ አካል ተጠያቂ መሆን እንዳለበት የሁላችንም አቋም መሆን እንዳለበት መረዳት ጥሩ ነው ለማለት ነው” ይላሉ የዞኑ አስተዳዳሪ።

በሐማሬሳ ግጭት ሰዎች መሞታቸውን በመቃወም እና የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ ከመጠለያው አቅራቢያ በሚገኘው ሀሮሚያ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች ዛሬ ተቃውሞ አሰምተው ነበር፡፡ ተቃውሞ እንደነበር ያረጋገጡት አቶ ጀማል ተማሪዎችን ለመበተን ጥይት ተተኩሷል መባሉን ግን ያስተባብላሉ፡፡ የተተኮሰው ጥይት ሳይሆን የተሰበሰቡ ሰዎችን ለመበተን አገልግሎት ላይ የሚውለው «አስለቃሽ ጭስ ነው» ባይ ናቸው፡፡ ከምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የሄዱ አመራሮች በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን ለማረጋጋት መሞከራቸውንም አስረድተዋል፡፡  

ተስፋለም ወልደየስ  – ሸዋዬ ለገሠ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *