“በወያኔ ላይ ጸሐይ ጠልቃለች” ሲሉ ስርዓቱ እንዳከተመለት አቶ ጁሃር ገልጸዋል። ” ደም በፈሰሰ ቁጥር ደም ይፈላል” ሲሉ ግድያ ትግሉን ሊያጨናግፈው እንደማይችል ሰው በሞተ ቁጥር ቁጣው መበራከቱን አመልክተዋል። በዚህም የተነሳ ሁሉንም ወደሚያስተናግድ የፖለቲካ ወሳኔ መግባት ግድ መሆኑንንም አስምረውበታል።

የopdo leaders ምስል ውጤት

አቶ ጃዋር መሀመድ በኦሮሚያ ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሲያሳስቡ ” የወያኔ ስርዓት ጸሃይ ጥልቆበታል። ለሁላችንም የሚሆን ስርዓት ለመገንባት ወደ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲያመሩ እምከራቸዋለሁ። አለበለዚያ አወዳደቃቸው የተወሳሰበና የተፈረካከሰ ይሆናል” በማለት ነው። ዶክተር አቢይ አህመድ በበኩላቸው አሁን እየተካሄደ ያለው አግባብ ፍጹም ተቀባይነት የሌለውና ሊቆም እንደሚገባ፣ ካልቆመ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል።
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር ይህንን ያሉት በሚመሩት ሚዲያ ላይ ቀርበው በሰጡት መግለጫ ነው። በክልሉ ተጠርቶ የነበረውን የስራ ማቆም ተቃውሞ አድማ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ጃዋር ” ከሚገባው በላይ ውጤታማ የሆነ” ሲሉ የጠሩትን አድማ የሶሰተኛው ቀን መርሃ ግብር መቀየሩን ተናግረዋል።
በዚሁ መሰረት ዛሬ አድማው ቆሞ ህዝብ የተፈቱ እስረኞችን ወደ መቀበልና የተዘጉ መንገዶችን መክፈትና ከተሞችን ማጽዳት ላይ ትኩረት ይደረጋል። በእነ በቀለ ገርባ መፈታት ትግሉ እንደማይቆም ያወሱት አቶ ጃዋር ሁሉም የአገሪቱ እስረኞች እስኪፈቱ ትግሉ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ትግሉ መለሳለስ አሳይቶ የነበረው ተፈናቃዮችን ለመርዳት በሚል እንደነበርም አመልክተዋል። አያይዘውም ትግሉ ወገኖችን ለማቋቋም በሚል መለሳለሱ ኦህዴድንም ሆነ ወያኔን ወደ ቀድሞው መንገዳቸው ለመመለስ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል ሲሉ ተደምጠዋል።
“በወያኔ ላይ ጸሐይ ጠልቃለች” ሲሉ ስርዓቱ እንዳከተመለት አቶ ጁሃር ገልጸዋል። ” ደም በፈሰሰ ቁጥር ደም ይፈላል” ሲሉ ግድያ ትግሉን ሊያጨናግፈው እንደማይችል ሰው በሞተ ቁጥር ቁጣው መበራከቱን አመልክተዋል። በዚህም የተነሳ ሁሉንም ወደሚያስተናግድ የፖለቲካ ወሳኔ መግባት ግድ መሆኑንንም አስምረውበታል።
” ኦህዴድ ጫና ማድረግ ጀምሮ ነበር” ካሉ በሁዋላ እየዋለ ሲያድር ኦህዴድ ወደ ቀድሞው አፈጣጠሩ የማፈግፈግ ሁኔታ ማሳየቱን ጠቁመዋል። አቶ ጃዋር እንደሚሉት ይህ አካሄድ ኦህዴድን ይጎዳዋል። የኦሮሞን ሕዝብ ገሎ መጨረስ እንደማይቻል ያመላከቱት አቶ ጃዋር “… ግድያው ይልቁኑም በስርዓቱና በሕዝብ መካከል መቆራረጥን ፈጥሯል” ሲሉ ወያኔና የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ማይታረቅ ልዩነት ማምራታቸውን አስረግጠው ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ሃላፊ ድንበር የወረረ አካል አለመኖሩን፣ የታጠቀ አማጺ በሌለበት፣ ጦርነት በሌለበት ሁኔታ የመከላከያ ሰራዊት መሐል ከተማ ምን ይሰራል ? ሲሉ ጥያቄ ያቀርባሉ። አያይዘውም መከላከያ የሚባለው ሃይል ባለበት ሁሉ ነብስ ይጠፋል። አገር ጠብቁ ብሎ ደሞዝ የሚከፍላቸውን ህዝብ የሚገል ሰአራዊት ምን አልባትም ያለው ኢትዮጵያ ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል። ” እናም” አሉ ” እናም ይህ ሰራዊት ነብስ ማጥፋቱን እንዲያቆም እማጸናለሁ። ነብስ በማጥፋቱ ትግሉን አያቆመውና”
በሃማሬሳ ኮንትሮባንድ የጫነ መኪና ያስቆሙ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ፣ በሃሮሚያ፣ በጨለንቆ፣ በኢሬቻ ወቅት እና በተለያዩ ስፍራዎች የተፈጸሙትን ግድያዎች በማስታወስ የመከላከያ ሰራዊቱን ያወገዙት አቶ ጃዋር ” ለጫት ንግድ ሲባል በሶማሌ ክልል አሳቦ ጭፍጨፋ ያወጀ የጦር መሪ ማዕረግ ሲሰጠው ማየትና መስማት ያስፍራል። ጉዳዩ ማንም የሚያውቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ ይህንን ሰው ለፍርድ ከማቅረብ ይልቅ ኮከብ ጨምሮ መሾም እጅግ አሳዛኝ ነው” ሲሉ አቶ ጃዋር ሃዘናቸውን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ያሉ እስረኞች፣ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ያሉ እስረኞች፣ በኦሮሚያ ያሉ እስረኞች ሙሉ በሙሉ ሳይፈቱ ትግሉ አንደማይቆም ያወሱት አቶ ጃዋር ” ቄሮ” ስርዓቱን የማንበርከክ አቅም እንዳለው በሙሉ ልብ ተናግረዋል። አያይዘውም አዲስ የትግል ስትራቴጂ መነደፉን ጠቁመዋል። ኢህአዴግን በኢኮኖሚ መግደል ቀላሉ፣ ነገር ግን ዋና ስልት መሆኑንንም ደጋግመው አውስተዋል።
ይህንኑ ለሁለት ቀን ተካሂዶ በሶስተኛው ቀን እንዲቆም የተወሰነውን አድማ አስመልክቶ “መንገድና የንግድ ተቋማትን መዝጋት ከዛሬ ጀምሮ መቆም አለበት “- ሲሉ ዶ/ር አብይ መናገራቸውን ፋና የኦሮሞ ሚዲያን ጠቅሶ አመልክቷል። የፋና ዘገባ ከላይ ያለውን ዜና ስለሚያመጣትነው እንዳለ አቅርበነዋል።
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንገድና የንግድ ተቋማትን መዝጋት ከዛሬ ጀምሮ እንዲቆም የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።

የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አብይ አህመድ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል። ዶክተር አብይ በመግለጫቸው፥ ህዝብ አንድ ላይ በመደራጀት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የራሱን መንግስት ማስገደድ እና ጫና በመፍጠር የተለያዩ ጥያቄዎችን ማንሳት በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ወሳኙ ነገር ነው ብለዋል። ሆኖም ግን ማንኛውንም ጥያቄ በምን መልኩ መቅረብ እንዳለበት እንዲሁም ግራ እና ቀኙን አስተውሎ መመልከት እና ማሰብ ያስፈልጋል ነው ያሉት ይህም ህዝብ እና የሀገርን ሀብት በማይጎዳ መልኩ መሆን ይገባዋል ብለዋል ዶክተር አብይ።

በአሁኑ ወቅት ከስራ ማቆም ጋር ተያይዞ እየተነሱ ካሉ ጥያቄዎች ውስጥ “የታሰሩ ሰዎች ይፈቱልን” የሚል ጥያቄ እየተነሳ መሆኑንም ዶክተር አብይ አስታውሰዋል።

ይህን ጉዳይ አመራሩ ከጥልቅ ተሃድሶው በኋላ ዋና ስራው አድርጎ በመውሰድ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ተለቀው በተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲሰማሩ ለማድረግ መወሰኑንም ነው የተናገሩት።

“እስር ከበዛ ህዝብ ይቸገራል፤ ማደግም ሆነ መለወጥ አይችልም” ያሉት ዶክተር አብይ፥ “ስለዚህ የእስረኞች መለቀቅ ጉዳይን ዋነኛ አጀንዳችን በማድረግ እየሰራን ቆይተናል” ነው ያሉት።

አጀንዳ ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ ስራዎች መስራት እንደተቻለ አስታውሰው፥ ከጥልቅ ተሃድሶው ወዲህ በኦሮሚያ ክልል ስልጣን ስር የነበሩን ከ30 ሺህ በላይ ሰዎችን ከእስር መፍታት መቻሉንም አስረድተዋል።

የፌደራል መንግስት መስራት ባለበት ጉዳይ ላይም ድርጅታቸው ጠንካራ ትግል ማካሄዱን ጠቅሰው፥ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ጉዳያቸው በፌደራል ደረጃ እየታየ ካሉ ሰዎች ውስጥም ከግማሽ በላዩ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ መደረጉን አንስተዋል።

አሁን ላይ ድርጅቱ ህዝቡን የሚጠቅሙ ታላላቅ እርምጃዎችን መውሰድ በጀመረበት ወቅት የስራ ማቆም አድማን በማሳበብ በኦሮሞ ስም የግለሰቦች እና የመንግስትን ሀብት የመዝረፍና ማውደም ተግባራት እየተፈጸመ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም በክልሉ የሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦችን ላይ ጥቃት መፈጸም፣ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት የማድረስ እና መሰል ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑንም በመግለጫቸው አንስተዋል።

ይህ በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ያሉት ዶክተር አብይ፥ ይህንን እንቅስቃሴ ከለላ በማድረግ ጉዳት እያደረሱ ያሉ አካላት እንዳሉና ጉዳዩ በህግ የበላይነት መስተካከል እንዳለበት አስረድተዋል።

በኦሮሚያ ውስጥ ማንኛውም ሰው ህጋዊ መሆነ መንገድ ሰርቶ የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት እንዳለውም ነው የገለጹት ዶክተር አብይ፥ አሁን እየተነሱ ባሉ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የክልሉ መንግስት ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው፤ ውሳኔ ላይም ተደርሷል” ብለዋል።

ስለዚህ ወጣቶች ሁሉንም ነገር በትእግስት መጠባበቅ እንዳለባቸውና መንገድ መዝጋት እና ሰዎች የንግድ ተቋማቸውን እንዲዘጉ ማስገደድ ትክክል አይደለምም ነው ያሉት ዶክተር አብይ። አሁን አየተካሄደ ያለው ተግባር በአስቸኳይ መቆም እንዳለበትም ዶክተር አብይ አሳስበዋል።

አሁን እየተካሄደ ያለው ተግባር ወዳልተፈለገ አላማ ሊለወጥና የኦሮሞ ህዝብ እና ወጣቶችን ሊጎዳ ስለሚችል፥ የክልሉ ህዝብ እና ወጣቶች ከዛሬ ጀምረው ከስራ ማቆም ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን ማስቆም አለባቸው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *