የቀድሞው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የአሁኑ የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አሜሪካ መሆናቸውን ጎልጉል የድረ ገጽ ጋዜጣ ዘግቧል። ጎልጉል ታማኝ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው ባለስልጣኑ አሜሪካ በወቅቱ ጉዳይ ጠበቅ ያለ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ፈቃድና ማስተማመኛ ለማግኘት ነው። የአቶ ሃይለማርያምን ” በቃኝ ” ተከትሎ ወታደራዊ አገዛዝ እንደሚመሰረትም መረጃዎች እየወጡ ነው።

ሰሞኑንን እየተከበረ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት ትዕይንት ከዚህ አጋር በማያያዝ ” የወታደራዊ መንግስት ሽታ ነበር” ሲል አቶ ልደቱ ለጀርመን ሬዲዮ ተናገረዋል። ጎልጉል የመፈንቅለ መንግስት ይዘት ያለው ወታደራዊ መንግስት እንደሚቋቋም፣ ይህም በአስቸኳይ አዋጅ ስም ሊከናወን እንደሚችል ዘግቧል። አቶ ልደቱ እንዳሉት ዛሬና ነገ የሚሰማ ጉዳይ ነው።

ዶክተር በየነ ጴትሮስ በበኩላቸው ህዝብ ኢህአዴግን በቃህ ማለቱን ጠቁመው አስተያየት ለመስጠት ገና መሆኑንን ተናገረዋል። በተለያዩ አቅጣጫዎች እንደሚሰማው ግን የአቶ ሃይለማርያም የስልጣን በቃኝ ዜና የግምገማው ውጤት እንደሆነ ነው። ከመምራት ችግር ጋር ክፉኛ የተገመገሙት አቶ ሃይለማሪያም በዚሁ መሰረት ራሳቸውን እንዲያሰናብቱ ተገደዋል የሚሉት ይበረክታሉ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አቶ ሃይለማሪያምን ማን እንደሚተካቸው ፍንጭ ባይኖርም ኢትዮጵያ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ እንደምትዘዋወር ግን ለህወሃት ቅርብ የሆኑ ሳይቀሩ በማህበራዊ ገጾቻቸው እየጻፉ ነው። ይህ በንዲህ እያለ ተቃዋሚ ድርጅቶች ወሳኔውን ለህዝብ በማስቀመጥ አንድ ትልቅ ህብረት ሊመሰርቱ እንደሚገባ በአሜሪካን በኩል ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩ ተሰምቷል። በሌላ በኩል ጎልጉል እንዳለው ለአሜሪካ ጥቅም ሲባል ህወሃት የሚፈለገውን ያህል ሃይል ተጠቅሞ በስልታን እንዲቀጥል ፍላጎት ያሳዩም አሉ። ለዚህም ሲባል ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እዛ ያሉት። ከታች ሙሉ በሙሉ የጎልጉል ዘገባ ነው

በኢትዮጵያ በተከታታይ የዘለቀውን ሕዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠር የተሳነው ህወሓት በኢትዮጵያ በአስቸኳይ አዋጅ ስም አገሪቷን በወታደራዊ አስተዳደር ስር ለማስተዳደር ኣዋጅ አንደሚያወጣ ተሰማ። የመፈንቅለ መንግሥት ይዘት ያለው አዋጅ ምናልባትም ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

  • ያለፈው የኢህአዴግ ስብሰባ ወቅት ስምምነት ተደርሶበት የነበረው ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ምስረታ ህወሓት ኣልቀበለውም ብሏል፥
  • ይህንን ተከትሎ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣኑ እንዲወርድ በህወሓት ግፊት ሲደረግበት ቆይቷል፤
  • የሃይለማርያም በፈቃዱ ከስልጣን መውረድ ለህወሓት የደኢህዴንን ስጋት እንዲቀንስለት ታስቦ የተደረገ ግፊት ነው፥
  • የኦህዴድ መክዳትና የብአዴን መከተል ላይ ደኢህዴን ከተጨመረ የህወሓትን ህልውና አደጋ ላይ መጣሉ ስላሰጋው ነው ህወሓት ሃይለማርያም በፈቃዱ ለቀቀ ማስባል የፈለገው፥
  • ወታደራዊ አገዛዝ ከታወጀ በኋላ ህወሓት ያለ ርህራሄ ማንኛውንም ተቃውሞ “የመጨረሻ ውሳኔ” በማስተላለፍ ታይቶ የማይታወቅ ደም ማፋሰስ በአገሪታ ላይ በማስከተል ስልጣኑን ለማረጋጋት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፤
  • ይህንን ተፈጻሚ ለማድረግና ከጌቶቹ ፈቃድ ለማግኘት በኦሮሞ ስም ለትግራይ የሚጫወተው ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ/ወልደጻድቅ አሜሪካ ይገኛል፥
  • ጎልጉል የደረሰው መረጃ አንደሚያመለክተው በአሜሪካኖቹ በኩል ሙሉ ስምምነት ባይኖርም አንዳንዶቹ ግን “የአሜሪካንን ጥቅም የሚያስጠብቁት ትግሬዎች ናቸው” በማለት ለህወሓት ሙሉ ስልጣን እንዲሰጠው በግልጽ ይናገራሉ፤
  • ከዚህ ጋር በተያያዘ ወታደራዊው አገዛዝ ዛሬ ሲታወጅ የአሜሪካ ድጋፍ ወደ ህወሓት ማዘመሙን በግልጽ የሚያሳይ ይሆናል፥
  • በግብጽ የፕሬዚዳንት ሙርሲን አስተዳደር አውርዶ የአሜሪካ ወኪል በሆነው አልሲሲ ለመተካት በተደረገው ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚ ዜጎችን የአልሲሲ ኃይል ሲጨፈጭፍ ምዕራባውያን በተለይም አሜሪካ የውስጥ ድጋፏን እንደሰጠችው በኢትዮጵያም በቀጣይ የሚከሰተው ይህ እንደሚሆን ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል
  • የኃይል አገዛዝ የትኛውንም መንግሥት እንዳላጸናው ከታሪክ የማይማረው ህወሓት አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የበቀል ርምጃውንም ለመውሰድ ሰይፉን ስሏል፥ የጌቶቹን ቡራኬም እየተቀበለ ነው።
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

(ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናትማለን)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *