~መጀመርያ “አጥፍቻለሁ፣ ተፀፅቻለሁ!” ብለህ ፈርም ተባለ። አላጠፋምና አልፈረመም!  ለሁለተኛ ጊዜ “በ5 አመት ውስጥ አሁን የፈፀምኩትን ወንጀል ብፈፅም የተፈረደብኝ ተግባራዊ ይሁንብኝ” ብለህ ፈርም ተብሏል። እሱ ግን “ወንጀል አልሰራሁም፣ አልፈርምም” ብሏል! ለ3ኛ ጊዜ ምን ብለው እንደሚጠይቁት እየተጠበቁ ነው! ዮናታን ደግሞ ምን እንደሚያደርግ ያውቃል!

– ጌታቸው ሺፈራው

በማህበራዊ ሚዲያዎች ሃሳብን መሰንዘርና ስሜትን መግለጽ እጅግ የተለመደና መንግስታት ቁብ ሰጥተው ለአፈና ክትትል የሚያደርጉበት አይደለም። ሰዎች በባህሪያቸው መተንፈስ ስለሚፈልጉና የሚተነፍሱበት ስለሊላቸው የሚጠቀሙባቸው መድረኮች ናቸው። ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ተቋማት ጥግ ድርስ ይውገዛሉ። የሰደባሉ። መሳለቂያ ተደርገው ይቀርባሉ።

ያደላቸው መሪዎቻቸውን በፌስ ቡክ ፊት ለፊት እያገኙ እኩል ይመላለሳሉ። በእኛ አገር ግን የሚሆነው እጅግ የተለየ ነው። አንድ ሰው በፌስ ቡክ ላይ አስተያየት ጻፈ ተብሎ 20 ዓመት ወይም አስር ዓመት ለመቅጣት አዋጅ ይዘጋጃል። የሚያሳዝነው ግን ይህ ሁሉ ግፍ የሚጠራቀምና አድሮም ቢሆን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑንን አለመረዳት ነው።

ሰላማዊ ዜጎችን የገደሉ፣ የጨፈጨፉ እያሉ፣ አንድ ሰው ተነፈሰ ብሎ እንዲህ ያለ ፍርድ ለመበየን ሌት ከቀን መስራት ችግሩን አይፈታውም። ይልቁኑም ያብሰዋል። አገሪቱን ቂም በቂም ከመላወስ የዘለለ ምንም ፋይዳም አያመጣም። ከጥፋትና ከስህተት ተምሮ እርምት በመወሰድ የትቆለለውን ቂም ማጽዳቱ ላይ ማተኮሩ ይቀላል። ለሁሉም የቪኦኤ ዘገባ እንዲህ ይላል።

የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የቀድሞ ኃላፊ ዮናታን ተስፋዬ በተከሰሰበት የሽብር ወንጀል የጥፋተኛነት ብይን ተላለፈበት፡፡ብይኑን የሰጠው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ጠበቃው በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚሉ አስታውቀዋል። ዮናታን ተስፋዬ ጥፋተኛ የተባለበት ወንጀል ከ10-20 ዓመታት ሊያሳስር ይችላል። የቅጣት ውሳኔውን ለማሰማት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ኢትዮጵያዊው የፖለቲካ ተቃዋሚ ዮናታን ተስፋዬ ሽብርተኛ ተብሎ ሃያ ዓምታት ሊፈረደበት ነው – ቢቢሲ

ቢ ቢ ሲ  እንደዘገበው የተቃዋሚ ፖለቲከኛ ዮናታን ተስፋዬን በሽብርተኛነት ወንጀል በሚል ሃያ ዓመታት ሊፈርድበት ነው። መንግስት ዮናታን ተስፋዬን የከሰሰው በፌስ ቡክ ላይ ህዝብን የሚያነሳሳ “ሽብርተኛነትን” የሚያደፋፍር አስተያየት ሰጥተሃል በሚል ነው። ዮናታን ተስፋዬ በፈረንጆች ዲሴምበር 2015 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል። 2015 ደግሞ በድፍን ኦሮሚያ ታላቅ የህዝብ ተቃውሞ የተነሳበት ወቅት ነበር።

የመንግስት ባለስልጣናት ያስከፋቸው ዮናታን  “መንግስት ከሰላማዊ ውይይት ይልቅ የሀይል እርማጃ ወሰደ” ማለቱ ነው። ይህ አባባሉ እንደ ወንጀል ተወሰደበት ሲል የቢ ቢ ሲ ያትታል ። በኢትዮጵያ ገዢው መንግስትን በጸረ ሽብርተኛ ህጉ ዓለም ኮንኖታል ይላል ቢ ቢ ሲ በዘገባው።

ዮናታን ተስፋዬ ላይ የተመሰረተውን ክስ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል የሰባአዊ መብት ድርጅት “የሃሰት ክሶች” ብሎ በሜይ 2016 ተናግሮ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ገዢው መንግስት የደነገገው “የጸረ ሽብርተኛ” አዋጅ መንግስትን ነክ የሆነ ማንኛውንም አስተያየት የሰጠን ሁሉ “ሽብርተኛ” የሚል ነው።

የዮናታን ተስፋዬን የክስ መስገብ ቢ ቢ ሲ እንዳስተረጎመው “የምነግራችሁ የመንግስትን የጭቆና መንገዶች ሰባብሩ። አሁን ገዳዮቻችሁን ሽባ ማድረግ የምትችሉበት ጊዜ ነው” ብለሃል የሚል ነው። መንግስት ዮናታን ተስፋዬ የመንግስት ተቃዋሚ የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ቃል አቀባይ ነው። በዚህ 20 ዓመት እስራት ሊፈረድበት ነው ይላል ቢ ቢ ሲ አፍሪካ።

ቢ ቢ ስ በ2015 የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ተሰምቶ የማይታወቅ ታላቅ ተቃውሞ ገጥሞት አንደነበር ጨምሯል። ተቃውሞውም ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ክፍሎች መዛመቱንም አመልክቷል። በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች “600 “ሰዎችን መግደላቸው ከዛሬው ዜና ጋር አክሎ ተናግሯል። ይህ ደግሞ የራሱ የመንግስት ተቀጥላ የሆነው “ሰባዊ መብት ኮሚሽን” ያመነው መሆኑንም ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ካለፈው ኦክቶበር 2016 አንስቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳወጅም የተቃዋሚ መሪ ፕሮፈሰር መረራ ጉዲና ይህኑ የመንግስት አዋጅ በመተቸታቸው ዛሬ በእስር እንደሚገኙም አክሎ አስረድቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ለተቃዋሚ መሪዎች በጣም ረጅም ዓመታ የሚፍጁ ብይኖችን በመስጠት ለማስፈራራት መሞከሩ የተለመደ ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች። ሲል አባይ ሚዲያ ዝግቧል

negist yirga

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *