በፌደራል ደረጃ ሃላፊነቱን ኦህዴድ ሲወስድ ሁሉንም የሀገሪቱን ህዝብ በእኩልነት፣ በሀቀኝነት እነ በእውነት ለማገልገል እና የህዝቡን ክብር ለማስጠበቅ በተገቢው መንገድ ተሳትፎ ያደርጋል ሲሉ ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆናቸውን ዜና አጉልተውታል።

በቅርቡ አራት የስራ የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራሮችን ያሰወገደው ኦህዴድ አቶ ወርቅነህ ነገዎን ከድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርነት አነሳ። ዶክተር አብይ አህመድን ሊቀመንበር አደረገ። ወሳኔውን አስመልክቶ ከክልሉ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የኦህዴድ ጥያቄ በክልል ሳይወሰን በሀገሪቱ አመራር ቦታ ላይ ተሳትፎ እንዲኖረው ከህዝቡ ጋር ሰፊ ትግል ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው ሽግሽጉ የታሰበበት መሆኑን ተናግረዋል።

በፌደራል ደረጃ ሃላፊነቱን ኦህዴድ ሲወስድ ሁሉንም የሀገሪቱን ህዝብ በእኩልነት፣ በሀቀኝነት እነ በእውነት ለማገልገል እና የህዝቡን ክብር ለማስጠበቅ በተገቢው መንገድ ተሳትፎ ያደርጋል ሲሉ ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆናቸውን ዜና አጉልተውታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህን ከድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርነት መነሳት አስመልክቶ ምንም ያላሉት አቶ ለማ ” ወሳኔው በጥልቀት የታሰበበት ነው” ሲሉ ደጋግመው ገልጸዋል።

Dr-Abiy-Ahmed

ጎልጉል የተሰኘው የድረገ ገጽ ጋዜጣ ወርቅነህ ነገዎ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ አሜሪካን ደረስ ዘመቻ ማካሄዳቸውን በጠቆመ የቀናት ልዩነት ውስጥ ኦህዴድ ከድርጅቱ መሪነት አንስቷቸዋል። ዶከትር አብይ በሃላፊነት ወደፌት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ በሚያቀርቧቸው የበሰሉ ንግግሮችና ትምህርቶች ሰፊ ተደማጭነት ማግኘታቸው ” ይህ ወጣት እስከዛሬ የት ነበር” የሚል ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል።

ከወጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ሃላፊነት መቀነስ ወይም ዝቅ ማለት ዜና ይልቅ የአቶ ለማ መገርሳ ምክትል ሊቀመንበር መሆን ” ውድቀት” እንደሆነ ተደርጎ በህወሃት ደጋፊዎች ዘንድ የማህበራዊ ገጽ ዜና ሆኖ ውሏል። ይሁን እንጂ አቶ ለማ በኦሮሚያ ሊቀመንበርነታቸውና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርነት መቀተላቸው፣ እንዲሁም ወሳኔውን ” የህዝብና የድርጅታቸው የቆየ ትግል ውጤት ነው” ሲሉ መግለጻቸው ኦህዴድ ምን አልባትም ስትራቴጂካዊ አካሄድ መከተሉን አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

worqenhe

በህወሃት ደጋፊዎች ዘንድ ዶክተር ወርቅነህ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ በስፋት ሲነገር የነበረውን ዜና ፣ የዶክተር አብይ አዲስ ሽመትና የአቶ ለማ መገርሳ ማብራሪያ ወሃ ቸልሶበታል። ” ጽነፈኞችን ተቀላቅለዋል” በሚል ስማቸው የሚነሳው የኦህዴድ አመራሮች በአቋማቸው መጽናታቸውን ያመለከተው ዜና ወደ መቋጫው ባመራበት በአሁኑ ሰዓት የሚጠበቀው የዶክተር አብይ ቃል ሆኗል።

ወኪሉ ያደረጋቸው ኦህዴድ ለመላው አገሪቱ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች፣ ምሁራኖች፣ በውጭ ላሉ የሰብአዊ መበት ተከራካሪዎች ጥሪ ማድረጉን ያስታወሱ አስተያየት ሰጪዎች ፣ ዶክተር አብይም ይህንኑ የድርጅታቸውን አቋም በፌደራል ደረጃ ያውጃሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ይናገራሉ። 

 

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

ዶክተር አብይ በመጀመሪያው ንግግራቸው ምን ይሉ ይሆን? ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የአመራር ሽግሽግ በማድረግ ዶክተር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር እና አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ ከኦቢኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ማዕከላዊ ኮሚቴው ዛሬ ያደረገው ስብሰባ ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የተፈጠረውን ችግር እንዴት መቅረፍ ይቻላል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሲመክር ቆይቶ ያሳለፈውን ውሳኔ መሰረት አድርጎ የተካሄደ ነው ብለዋል።

በክልል እና በሀገር ደረጃ የሚነሱ ጥያቄዎችን በበሰለ እና በሰከነ መንገድ ምላሽ ለመስጠት ሲመከር መቆየቱንም ነው ያመለከቱት። የህዝቡን የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ትግል ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት አቶ ለማ፥ በፌደራል ደረጃ አመራር መውሰድ የህዝቡ እና የድርጅቱን ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል።

በክልል ደረጃ መሰራት ያለባቸውን በመስራት፥ ታሪክ የሚሰጠንን እድል በመጠቀም ለክልሉ ህዝብም ሆነ ለሀገሪቱ ጠቃሚ ስራ መስራት አስፈላጊ ሆኖ ድርጅቱ ስላገኘው የአመራር ሽግሽግ አድርጓል ብለዋል።

በፌደራል ደረጃ የአመራር እድልን የሚያገኝ ሰው ሁሉንም የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድ አይን የሚያይ ይሆናልም ብለዋል። የህዝብ ክብር የሚመጣው እኩልነትን እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሲቻል መሆኑን አቶ ለማ ተናግረዋል።

የህዝቡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄ ሊመለስ ይግባዋል ያሉት አቶ ለማ፥ የኦህዴድ ስራ አስፈፃሚም ይህንን በጥልቀት በማየት የክልሉ አመራር እና ማዕከላዊ ኮሚቴው በመግባባት እና በመተማመን እዚህ ውሳኔ ላይ ደርሷል ነው ያሉት።

የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የኦህዴድ ጥያቄ በክልለ ሳይወሰን በሀገሪቱ አመራር ቦታ ላይ ተሳትፎ እንዲኖረው ከህዝቡ ጋር ሰፊ ትግል ሲደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል።

ከዚህም መነሻነት በፌደራል መንግስት ውስጥ የአመራር ድርሻ ሊኖረን ይገባል ስንል የክልላችንን ጉዳይ በመርሳት ሳይሆን፥ በታሪክ ውስጥ የተገኘውን አድል የሰፊውን ህዝብ ክብር በጠበቀ ሁኔታ እንዴት መስራት ይኖርበታል የሚለውንም በጥልቀት ማዕከላዊ ኮሚቴው መገምገሙን ነው የገለፁት።

ይህ የተገኘው እድል የሚሰጠውን ሀላፊነት የሁሉንም ህዝብ ተጠቃሚነት ባረጋጠ መልኩ ለመወጣት አርቆ ማሰብም ያስፈልጋል ነው ያሉት። የተገኘውን ድል በተገቢው መንገድ መጠቀም ካልተቻለ ወድቆ መሰበርም ስላለ ይህንን በትኩረት ማሰብ እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል።

ይህንንም ሀላፊነት ኦህዴድ ሲይዝ ሁሉንም የሀገሪቱን ህዝብ በእኩልነት፣ በሀቀኝነት እነ በእውነት ለማገልገል እና የህዝቡን ክብር ለማስጠበቅ በተገቢው መንገድ ተሳትፎ ማድረግ

ሲለሚያስፈልግ ማዕከላዊ ኮሚቴው ይህንን ሁሉ ከግምት በማስገባት የግለሰብን ጉዳይ ሳይሆን የድርጅቱን የቡድን አመራር ለማጠናከር ያደረገው ሽግሽግ ነው ብለዋል አቶ ለማ መገርሳ።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *