(ኤድመን ተስፋዬ) – ተወልዶ ያደገው በሃረር ከተማ ቀበሌ ዘጠኝ ልዩ ስሙ ሸንኮር ነው። ሙሉ ስሙም አቤል ሆዜርኖ ይባላል። አቤል ከኢትዮጲያዊ ኧናት ኧና ከኩባዊ አባት ነው የተወለደው።  አቤል ወይም በቅጽል ስሙ ኩባ በሰፈሩም ሆነ በድፍን ሃረር የሚታወቀው  በስፓርት ወዳድነቱ፣ ከማህበረሰቡ ጋር ባለው ተግባቢነቱ ነው። አቤል የራሱን ሆነ የሌላውን መብት ለማስከበር ምንም አይነት ፍርሃት ያልፈጠረበት ነው። ከአካል ብቃት እንቅስቃሴውም ሆነ በመልከ ክልስነቱ በድፍን ሃረር የሚታወቀው አቤል  ለእናቱ የመጀመሪያም የመጨረሻም ልጅ ነው።

ከዛሬ አስር አመት በፊት ከምስራቅ እዝ አስተዳዳሪ ጄነራል አብራሃ የግል ጠባቂዎች ጋር በመዝናኛ ቦታ በተፈጠረ ጠብ እራሱን ለመከላከል ሲል  የቡጢ እና የቴክዋንዶ እርመጃ ልቡ ባበጠው የጄነራሉ ጠባቂ ላይ  በመውሰድ የማቁሰል አደጋ በማድረስ ተሰውሮ ለጥቂት ቀናት ከቆየ በሃላ ፤ በሰፈር እና በሃገር ሽማግሌዎች ምክር እጁን ለሃረሪ ፓሊስ ሊሰጥ ቻለ። የህወሃት-ኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆነው እና በሃረር ከተማ የዘረኝነት አስተዳደር ያሰፈነው የ ሃረሪ ብሄራዊ ሊግ አቤልን ከታሰረበት የሃረር ፓሊስ መምሪያ እስር ቤት ውስጥ ለህወሃት ልዩ ሃይሎች  ለማስረከብ አንድ ቀንም አልፈጀበትም።  በህወሃት ልዩ ሃይሎች ታፍኖ ላለመወሰድ ከፍተኛ ተጋደሎ ካደረግ በሃላ (ጠባባ ኧስር ቤት ላለማስገባት አቤል ከአፋኞቹ ጋር ከፍተኛ ግብ ግብ ኧንዳደረገ በወቅቱ ግቢው ውስጥ የነበሩ የክልሉ ፓሊሶች በቁጭት አጫውተውኛል) በጄነራል አብርሃም ልዩ ትእዛዝ በሃይል ከሃረር ፓሊስ መምሪያ  ታፍኖ የተወሰደው አቤል ይኑር ይሙት ሳይታወቅ ይሀው ከአስር አመት በላይ ሆነው።ኧናቱም የብቸኛ ልጅዋን ኧርም በማውጣት ኧና በይመጣል (ይፈታል) ተስፋ ስትዋልል ኧና ስትንገላታ ከአስር አመት በላይ ሆናት።

ጉምቶዎቹ የሚሊተሪ ሳይንስ ጠበብቶቹ የሃገራችን ጄነራሎች እነ ደምሴ ቡልቶ፣ወርቁ ቸርነት፣ ፋንታ በላይ ወዘተ እንክዋ ያላገኙትን የሙሉ ጄነራልነት ማእረግ በህወሃት ታጋይነትህ የተነሳ  ብቻ  በቅርቡ የጫንከው አብራሃም  ባንተ ትእዛዝ ከሃረር ፓሊስ መምሪያ የተወሰደው  አቤል ተገሎም ከሆነ በነብሱ፤ እስከ አሁንም በእስር ቤት ታስሮም ከሆነ ፍትህን በመነፈጉ አንተም ሆንክ የሽንት ጨርቆችህ የምትጠየቁብት ጊዜ በጣም መቅረቡን በርግጠኝነት እነግርሃለው።በፍትህ አደባባይ እስክንገናኘ ድረስ ግን የቀዬን ልጅ፣ አብሮ አደጌን አቤልን የት አደረሳችሁት? ሞትዋል ወይስ አለ? የሚለውን የነብሴን ጥያቄ ላንተም ሆነ ለሽንት ጨርቆችህ ይድረስልኝ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *