በጋዛ ሰርጥ መዘጋት ምክንያት ከ1 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ህይወት ማለፉ ተነገረ

እስራዔል የጋዛ ሰርጥን መተላለፊያ በመዝጋቷ ከ1 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ህይወት ማለፉን ሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ተቋማት ገለጹ። ተቋማቱ እስራኤል የጋዛ ሰርጥን የአየርም ሆነ የምድር መተላለፊያዎች በመዝጋቷ ምክንያት በፍልስጤማውያን ላይ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ነው ብለዋል። በዚህ ሳቢያም እስካሁን ከ1 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ህይዎት ማለፉን ነው የተናገሩት።

ባለፉት ቀናቶችም አምስት ህጻናት ከመወለጃ ጊዜያቸው ቀደም ብለው የተወለዱ ህፃናት ህይወት ማለፉንም አስታውቀዋል። በፍልስጤማውያኑ ላይ ለሚደርሰው ሞትም የህክምና እጥረት ዋናዋ ችግር ነው ተብሏል። ከሟቾቹ ውስጥ 450ዎቹ በህክምና እጥረት ሳቢያ መሞታቸውን የእርዳታ ሰጭ ተቋማቱ ሪፖርት አመላክቷል።

ከህክምና እጥረት ባለፈም አሁንም በጋዛ የውሃና የአሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት ከፍተኛ ችግር ሆኗል ነው የተባለው። የሃይል እጥረቱየን ለመፍታት በሚደረግ ጥረትም ህጻናትና አረጋውያን ለህልፈት እየተዳረጉ መሆኑም ነው የተነገረው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በምሽት ወቅት ብርሃን ለማግኘት የተለኮሰ ሻማ ባስከተለው የእሳት አደጋ በርካታ ህጻናት ሞተዋል ተብሏል። – ፋና አልጀዚራን ጠቅሶ እንዳለው

የሶሪያ መንግስት በምስራቃዊ ጎህታ እያካሄደ ባለው የአየር ድብደባ የክሎሪን ጋዝ ቦምብ መጠቀሙ እየተነገረ ነው።

በምስራቃዊ ጎህታ አካባቢ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች፥ የሶሪያ መንግስት ጦር በአካባቢው እያካሄደ ባለው አየር ድብደባ የክሎሪን ጋዝ ቦምብ ተጠቅሟል ሲሉ ወቅሰውታል።

የሶሪያ የሲቪል መብቶች ተከላካይ ቡድንም በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫው፥ መንግስት የክሎሪን ጋዝ ቦምብ ተጠቅሟል፤ እስካሁን የአንድ ህጻን ልጅ ህይወት አልፏል ብሏል። በምስራቃዊ ጎህታ የሚንቀሳቀሰው የተቃዋሚ ቡድን የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ በሰጠው መግለጫ፥ በክሎሪን ጋዝ ቦንቡ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ሰዎች አካባቢው ወደ ሚገኘው የጤና ተቋማት ተወስደው ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን አንስተዋል።በሶሪያ ጎህታ የአየር ድብደባ የክሎሪን ጋዝ ቦምብ ጥቅም ላይ ውሏል እየተባለ ነው

እስካሁንም በትንሹ 18 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተከታተሉ ነው የተባለ ሲሆን፥ በርካታ ህጻናት እና ሴቶች ደግሞ ለመተንፈሻ አካል ችግር መጋለጣቸው ነው የተነገረው። በምስራቃዊ ጎህታ ግዛት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ በአማጽያን ቁጥጥር ስር የምትገኝ አካባቢ ነች።

የሶሪያ መንግስትም አካባቢውን ከታጣቂዎች ነፃ ለማውጣት በሚል ካሳለፍነው ሳምነት ጀምሮ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እያካሄደ ሲሆን፥ በዘመቻውም እስካሁን ከ500 የሚበልጡ ዜጎች ህይወት አልፏል ነው የተባለው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትም ለ30 ቀናት በአካባቢው የተኩስ አቁም እንዲካሄድ በትናንትናው እለት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የተኩስ አቁም ውሳኔ ከተላለፈ ከሰዓታት በኋላ የሶሪያ መንግስት ውሳኔውን በመጣስ የአየር ድብደባ ማካሄዱ ነው እየተነገረ ያለው። የሶሪያ መንግስት የተኩስ አቁም ውሳኔውን ጥሶ የአየር ድብደባ ማካሄድ ከጀመረ ወዲህም በትናንትናው እለት ብቻ የ27 ሰዎች ህይወት አልፏል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ www.aljazeera.com

ትላንት የኢራቅ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ጥፋተኛ ናቸው ባላቸው 16 ቱርካዊያን ሴቶች ላይ የሞት ቅጣት አስተላለፈ። ዳኛ አብዱል ሳታር በኢራክዳር የከፍተኛ ፍርድ ቤት ቃል አቀባይ በመግለጫቸው እንዳሉት፥ ሴቶቹ ከአይኤስ አይኤስ ጋር ግንኑነት እንደነበራቻው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሴቶቹ በምርመራ ወቅት አይኤስ እንደተቀላቀሉ የአሸባሪ ቡድኑ አባላትን እንዳገቡና የሎጂስቲክ ድጋፍ ያደርጉ እንደነበረ መናገራቻን አስታውቀዋል። በአውሮፓውያኑ ታህሳስ ወር 2017 ጀምሮ ኢራቅ ከአይኤስ ነጻ መሆኗን ካወጀችበት ጊዜ ጀምሮ የሀገሪቱ መንግስት የቡድኑን አባላት በፍርድ እየቀጣ ይገኛል።

የአይኤስ ሽንፈትን ተከትሎ የተያዙ ብዙ ሴቶች የሞት ቅጣትና የዕድሜ ልክ እስራት እየተላለፈባቸው ነው። ይህንንም ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ከሽብርተኛ ቡድኑ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ብቻ ሚዛናዊ ያልሆነ ፍርድ እየተላለፈባቸው ነው። የኢራቅ ፍርድ ቤት 16 ኢራቃውያን ሴቶች ይግባኝ ማለት እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ምንጭ፦ሲ.ኤን.ኤን – ፋና

የአፍሪቃዉያን ስደኞች ሞትና እንግልት በየመን

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን /UNCHR/ ሰሞኑን ባወጣዉ ዘገባ ባለፈዉ ጥር ወር መጨረሻ ብቻ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ስደተኞች ወደ የመን ባህረ ሰላጤ ተጉዘዋል። በዚህ የባህር ላይ ጉዞ በደረሰ አደጋም 30 ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል።

«ባለፈዉ ዓመት ብቻ  ወደ 87 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ወደ የመን ተሰደዋል»

በዚህ መንገድ በርካታ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ወደ የመን ጉዞ ያደርጋሉ ።ነገር ግን በሀገሪቱ በሚካሄደዉ የርስበርስ ጦርነት ሳቢያ የደረሰዉ ሰብዓዊ ቀዉስ እነዚህን ስደተኞች በህገ ወጥ የሰዉ አዘዋዋሪወች እጅ እንዲወድቁ እያደረጋቸዉ መሆኑ እየተነገረ ነዉ። የመንንና ሶማሊያን የሚለየዉ የኤደን ባህረ ሰላጤ በዓለማችን ትልቁ የባህር ንግድ መስመር ነዉ።በእስያና በአዉሮጳ መካከልም ትልቁ  መገናኛ  ነዉ።ይህ የንግድ መስመር በአፍሪቃ ቀንድና በአረብ ባህረ ሰላጤ መካከል የሚደረገዉን ስደትም ያስተናግዳል። 
በዚህ  መንገድ በተለይ ወደ ሳዉዲ አረቢያ የሚደረገዉ ስደት የቆየና የተለመደ መሆኑን ከዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ድርጅት ካትሪን ኖርዚንግ ያብራራሉ።
« ይህ በፍጹም አዲስ ልማድ አይደለም።ከጅቡቲና ከሶማሊያ ተነስተዉ ኢትዮጵያዉያንና ሶማሊያዉያን ባህር አቋርጠዉ ወደ የመን መጓዝ የተለመደ ነዉ።በተለይ ወደ ሳዉዲ አረቢያ ለመሸጋገር ።በታሪክ በርካታ ኢትዮጵያዉያንና ሶማሊያዉያን ከጦርነቱ በፊትም የመን ይኖራሉ።ይህ ፍጹም አዲስ ነዉ ብዬ ልናገር አልችልም።ነገር ግን ግጭት በሰፈነባት የመን ስደተኞች አሁንም ድረስ መምጣት መቀጠላቸዉ አስገራሚ ነዉ ብዬ አስባለሁ።»

Jemen afrikanische Migranten in Harad (DW/Alsoofi)

በነዳጅ ዘይት የበለጸጉት ሳዉዲ አረቢያና ሌሎች ሀብታም የባህረ ሰላጤው መንግስታት በአንድ በኩል በአፍሪቃ ቀንድ ለአመታት በዘለቀ የርስበርስ ጦርነት የደቀቀችዉ የዓላማችን ድሃዋ ሀገር ሶማሊያ በሌላ በኩል ፣በመሃል ደግሞ  በጦርነት የምትታመሰዉ የመን ትገኛለች።ይች ሀገር ታዲያ ከ 2014 ጀምሮ በሚካሄደዉ የርስበርስ ጦረነት ሳቢያ በሺ የሚቆጠሩ የሀገሬዉ ዜጎች ለሞት ሚሊዮኖች ደግሞ ለስደት መዳረጋቸዉን መረጃወች ያሳያሉ ።ያም ሆኖ ግን የአፍሪቃ ቀንድ ስደተኞች አሁንም ወደዚች ሀገር መጓዛቸዉን አላቋረጡም።
እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት /IOM/ በዚህ ሁኔታ  ሞትና እንግልት እያጋጥማቸዉም ቢሆንም ባለፈዉ ዓመት ብቻ  ወደ 87 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ባህር አቋርጠዉ ወደ የመን ጉዞ አድርገዋል።በዚህ ጉዞም በርካቶች ህይወታቸዉን አጥተዋል።

«በጀልባዉ ላይ ግርግር ተነሳ »ይላሉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ዊሊያም ስፔንሰር  ባለፈዉ ጥር ወር መጨረሻ  የደረሰዉን የአደጋ ሁኔታዉ ሲገልጹ «በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአብዛኛዉ ከሶማሊያና ከኢትዮጵያ የሆኑ ጀልባዉ ላይ ነበሩ። እናም ጀልባዉን የሸጡት ህገወጥ የሰዉ አዘዋዋሪወች መንገደኖቹን በድንገት ተጨማሪ ገንዘብ መጠየቅ ጀመሩ።የተወሰኑት ሲከፍሉ ሌሎቹ ግን መክፈል አልቻሉም ወይም ተቃወሙ።በዚህ ጊዜ የህገወጥ ደላሎቹ ባልከፈሉ ሰዎች ላይ መተኮስ ጀመሩ።እናም ግርግር ተነሳና ጀልባዋ ወደ አንድ ጎን ማዘንበል ጀመረች።በዚህ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሰጠሙ።ቢያንስ 30 ሰዎች ሞተዋል።»
ይላሉ ስፔንሰር ከአደጋዉ ከተረፉ ሰዎች ሰማሁ ብለዉ እንደገለጹት።እንደእሳቸዉ ገለጻ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ያም ሆኖ ግን ሰዎች ምርጫ ስሌላቸዉ  አሁንም ድረስ ይሰደዳሉ ሲሉ ያክላሉ።ብዙዎቹም ከጦርነትና ከድህነት ሸሽተዉ የመጡ በመሆናቸዉም ወደ ሀገራቸዉ መመለስ አይፈልጉም ሲሉ ያብራራሉ።
«ሰዎች ህይወታቸዉን አደጋ ዉስጥ ከተዉ ወደስደት የሚያመሩበት ምክንያት ምርጫ ስሌለላቸዉ ነዉ ።ምርጫ ካለ ማንም እዚህ አደጋ ዉስጥ አይገባም።በርካታ ሰወች የሚሰደዱት ድህነትን በመሸሽ የተሻለ የኢኮኖሚና የስራ ዕድል ፍለጋ ነዉ።ሌሎች ደግሞ በጦርነት ፣በግጭት፣በስቅይትና በሰብዓዊ መብት ረገጣ የተነሳ ነዉ።»

Jemen afrikanische Migranten in Harad (DW/Saeed Al soofi)

ሶማሊያዉያን በየመን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በኩል  በስደተኝነት መመዝገብ ይችላሉ ።ነገር ግን በሀገሪቱ ያለዉ ጦርነት ሁኔታዉን አስቸጋሪ አድርጎታል።በዚህ የተነሳ በርካታ ስደተኞች ለእንግልት፣ ለጥቃትና  ለእስራት የተጋለጡ መሆናቸዉ ይነጋራል።ሌሎች ደግሞ ለጉዞ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት አደንዛዥ ዕፅ  በሚመረትባቸዉ  ማሳዎች ለመስራት ይገደዳሉ። ከዓለም ዓቀፉ የስደት ድርጅት ካትሪን ኖርዝ እንደሚሉት ሁሉም አልሳካ ሲላቸዉ አንዳንድ ጊዜ ወደ ሀገራቸዉ እንድንመልሳቸዉ ይጠይቃሉ ይላሉ። 

በዚህ ጊዜ ደህንነታቸዉ በተጠበቀ ሁኔታ ለመመለስ እንሞክራለን።ነገር ግን አብዛኛዎቹ የህገ ወጥ ደላሎችን በመተማመን ህይወታቸዉን ለእነሱ አሳልፈዉ ይሰጣሉ ሲሉ ነዉ ኖርዝ የሚናገሩት።
ዊሊያም ስፔንሰር ግን ለስደተኞች ህጋዊ መንገዶችንና አማራጮችን ልናሳያቸዉ ይገባል ሲሉ ይሟገታሉ።

«እናም ለዚህ ነዉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNCR ሰዎች በጥንቃቄ  ደህንነታቸዉ ተጠብቆ እንድጓዙ ስለ ህጋዊ የደህንነት አማራጮች የሚሟገተዉ። ስደተኞችን መልሶ በማስፈር ፣ቤተሰብን እንደገና በማገናኘት፣ለስደተኞች የተማሪዎች ቪዛ መፍቀድ እና ሌሎች ህጋዊ መንገዶችን  በመጠቀም  ሰዎች በዚህ መንገድ ህይወታቸዉን አደጋ ላይ መጣል ሳያስፈልጋቸዉ እንድጓዙ ማድረግ ይቻላል።እነዚህን አሳዛኝ ታሪኮችም በዚህ መግታት ይቻላል።»

 ማሪቲና ሽዋስኮቭሲኪ /ፀሐይ ጫኔ ሂሩት መለሰ የጀርመን ድምጽ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *